Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Sunday, 24 July 2011 07:13

ከሃዲ..

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ለመሆን በቂ ምክንያት አለን?
..ስሜት.. እና ..ስሌት.. ሁለቱም ከአንዱ ናቸው
ቀደም ባሉት ሣምንታት እምነቴ የምክንያት ጥገኛ ባይሆንም ምክንያት አልቦ ያለመሆኑን አውርቻለሁ፡፡ የእምነቴ ማስረጃ በእጄ ያለው ቅዱስ መጽሐፍና በልቤ ውስጥ የሚላወሰው የባለታሪኩ መንፈስ እንደሆነ ገልጫለሁ፡፡

በሥጋ ዓይን የሚታይና የሚነበብ፣ በእጅ የሚያዝና እንደ ሁሉም መጽሐፍ በመደርደሪያዬ ላይ ሲሆን ሌላኛው ግን ታሪኩ የከሰተልኝ ስውር ግን ተጨባጭ ምስል ነው፡፡ ..መገለጥ.. የምለውም እሱ ነው፡፡ ስለዚህ ደግሞ በዚያው መጽሐፍ ..ዓለም አያውቀውም.. እናንተ ግን በውስጣችሁ ስለሚኖር ታውቁታላችሁ.. ተብሎ ተጽፏል፡፡
እምነት ተፈጥሯዊ ቢሆንም ወደ እግዚአብሔር የሚያደርሰው እምነት ግን ከ..መገለጥ.. እንደሚጀመር፤ መገለጡም kእግዚአብሔር መናገር ጋር የተያያዘ ስለመሆኑ አውስቻለሁ፡፡ ከዚህ ቀደም yእግዚአብሔር ለሰው የመናገሪያው ወይም የመገለጫ መንገዶቹ ልዩ ልዩ የነበሩ ቢሆንም በዚህ ዘመን የሚነገርበት ወይም የሚገለጥበት ..ቃል.. ግን ለየት ባለ መልኩ ዓለማት የተፈጠሩበትና የፀኑበት ..ቃል.. ወይም ..ምክንያት.. ስለመሆኑና ይኸው ቃልም ሥጋ ለብሶ በምድር ላይ ስለመመላለሱ ጽፌያለሁ፡፡ በመጽሐፍ ለዓለም ሁሉ የተላለፈው መልዕክት ..ህይወት ተገለጠ አይተንማል፤ አስቀድሞ የነበረውን ለእኛም የተገለጠውን የዘለዓለምን ህይወት እናወራላችኋለን፡፡.. የሚል ነው፡፡ ለእኔ የእምነቴ ግርምት ምንጩም በመጽሐፉ የተፃፈውና ያንኑም ባመንኩበት ወቅት ወደ ልቤ የመጣው መንፈስ ፍፁም መመሳሰል ነው፡፡
ይህኛው የእምነቴ ስሜታዊ መግለጫ ሲሆን ምክንያታዊው አእምሮዬም ቢሆን በምክንያት ሊገለጽ የሚችለውን የዓለም ሁኔታ ብቻ ሳይሆን ነቢዩ ዳዊት ..ሰማያት.. yእግዚአብሔርN ክብር ይናገራሉ፣ የሰማይ ጠፈር የእጁን ሥራ ያወራል፡፡ (መዝ 18.1) እንዳለው የተፈጠረ ያልሆነውን ፈጣሪ ተግባራት በሥነ አመክንዮ ዘዴ ማብራራት እንደሚቻል ገልጫለሁ፡፡ ዛሬም ደግሞ በሥርዓት ከተቀናጀው ዓለም በስተጀርባ ..ስሌት.. ብቻ ሳይሆን ..ስሜት.. የሚባልም መግለጫ እንዳለ፣ ዓለም አዋቂ ፈጣሪ ብቻ ሳይሆን አፍቃሪ ሠሪም እንዳላት መካድ ምክንያት የሌለው ክህደት ስለመሆኑ መፃፍ ፈልጊያለሁ፡፡ ስለ እግዚአብሔር ለማወቅ ፈቃደኛ የሆነ ሰውም በዕውቀት (Rational mind) በኩል እውነትነቱን፣ በስሜቱ (emotional mind) በሚባለው ተፈጥሮው በኩል ደግሞ ውበቱን፣ በድርጊቶቹ በኩልም መልካምነቱን ሊያይ እንደሚችልና የነዚህን ስምምነቶች ምንጭ ማጣራት እንደሚገባው ጥቂት ነገር እላለሁ፡፡
ይህንን ዓለም የምንገነዘብበት ተፈጥሯዊ መሣሪያ አንድ ብቻ ሳይሆን ሁለት ነው፡፡ ስሜትና ስሌት (Sense and Reason) የማንኛውም ሰው የጋራ ተፈጥሮ ሲሆን በአግባቡ ሲጠቀሙበት ደግሞ አንዱ የሌላው ተቃራኒ አይሆንም፡፡ ዶክተር ጆን ላውንስን ስለዚህ ስምምነት የሚገልፁት እንዲህ በማለት ነው፡፡ “We know through reason and our sense that something is true we when see that it is proven logically and is consistent with life facts”  በሥነ ዓዕምሮ ጥናትም ቢሆን ሰው “Rational” ብቻ ሳይሆን “Irrational” እንደሆነ፣ የቀኙ ክፍል ..ምክንያታዊ.. የግራው ደግሞ ..ኢ- ምክንያታዊ.. ስለመሆኑ ይወሳል፡፡ ይሁንና እኔ ነገሩን እንዲህ ከፋፍዬ ለማሰብ የበቃሁ አይደለሁም፡፡ በስሜትና ስሌት የታጠረ ስለመሆኑ ካልሆነ በቀር ቀኝ እና ግራ ተብሎ መደምደም ስለተቻለበት ዕውቀት Sceptic (ተጠራጣሪ) ነኝ፡፡ ሰውን እንዲህ ከፋፍሎ ለማስቀመጥ የሚችል የታመነ የዘረሰብ ምርምር ውጤት እንዳለ አላውቅም፡፡ ከ..ሳይኮ - አናሊስቱ.. ፍሮይድ ..ኢድ..፣ ..ኢጐ.. እና ..ሱፐር ኢጐ.. ትንታኔ ይልቅ ሰው የነፍሱ፣ የመንፈሱና፣ የአካሉ የሦስትዮሽ ልምድ መሆኑን መቀበል ይቀለኛል፡፡ በሥጋው (በስሜት ህዋሳቱ) በኩል በውጭ ካለው ዓለም ጋር፣ በነፍሱ (በሃሳቡና በጥልቅ ስሜቱ) በኩል ከራሱ፣ በመንፈሱ በኩል ደግሞ ከፈጣሪው ጋር ዕውቂያ ማድረግ መቻሉ ያስማማኛል፡፡ በመጽሐፍም እነዚህ የሰው ልዩ ልዩ ክፍሎች እንደየምንነታቸው በጤና ተጠብቀው ይኖሩ ዘንድ የተሰጠ የባርኮት ቃል በመኖሩ በዚህ ላይ ያለኝ እርግጠኝነት የበዛ ነው፡፡
የምሥራቁ ዓለም ትኩረት ስለሚያደርግበት ውስጣዊ ስሜትም ሆነ የምዕራቡ ዓለም ስለሚመካበት አእምሯዊ ስሌት (Sense and Reason) ተፈጥሯዊ ግብር ስናወራም የአንድን ነገር ህልውናና ምንነት የምናረጋግጥበት ከፍተኛው ብርሃን አሁንም ..እምነት.. ብቻ ነው፡፡ ለምን ከተባለም ሰው በስሌቱም ሆነ በስሜቱ ያልጨበጣቸው ብዙ ጉዳዮች ያሉ በመሆኑ ነው፡፡ አንስታይን በአንድ ወቅት ..ከህይወት የተማርኩት ነገር የተፈጥሮን መሠረታዊ አካሄድ ለማወቅ ብዙ እንደሚቀረን ነው፣ በየጊዜው በሣይንሳዊ ግኝቶች ማግስት የሚታዩት ድግሦች እውነታውን አያንፀባርቁም፡፡.. ማለቱ ከዚህ የመነጨ ነው፡፡ ከዚህ ቀደም በሣይንሳዊ ዘዴ ካልተብራራልኝ በስተቀር የቱንም ነገር እውነት አድርጌ አልቀበልም ይል ለነበረው ..ሞደርኒዝም.. ለተሰኘው ሰብዓዊ አመለካከት፣ ተቃራኒ ሆኖ የመጣው ..ፖስት - ሞደርኒዝም.. መፈጠር ሰበቡም ይኸው ሲሆን የዚህ ዕይታ ምንጭም ከዛሬ አርባና ሃምሣ ዓመታት በፊት ..ናሽናል ጆግራፊክ.. የተሰኘው ድርጅት የጥናት ውጤት እንደሆነ ይገመታል፡፡
በወቅቱ ይኼ ድርጅት የሰዎችን ማህበራዊ አኗኗርና ጂኦግራፊያዊ አሠፋፈር እንዲያጠኑ ወደተለያዩ አገሮች በላካቸው ሙያተኞች በኩል ያገኘውን የጥናት ዝርዝር በመጽሐፍ መልክ ያሳተመ ሲሆን የጥናቱ ውጤት ያሳየውም በየትኛውም ማህበረሰብ ውስጥ (የሠለጠኑትም ይሁኑ አይሁኑ) አንድ ፈጣሪ እንዳለ የሚገለጽበት የጋራ ስሜት ይዘው መገኘታቸው ነው፡፡ ዛሬም እኔ በጥቂቱ የማወሳው በዚህ ስሜት በኩል ስለሚንፀባረቀው ህላዌ ነው፡፡ ከዚህ ቀደም ስለ እምነትና ስለ ተፈጥሮ ስምምነት ሳወራ በአመዛኙ ያነሳኋቸው ጉዳዮች ከዚህ በሥርዓት ከተቀናበረው ፍጥረት ጀርባ አንድ አዋቂ መሃንዲስ መኖሩን የሚመለከት ነበር፡፡ ሆኖም ለክህደቱ በቂ ምክንያት ለሌለው ሰው እስካሁንም ምንም ስሜት እንዳልሰጠው ለመገንዘብ ችያለሁና ስሌትህን ከስሜትህ አፋተህ ካልመጣህ በቀር ጨዋታህ አይጥመኝም ለሚለኝ ..ስሜትም.. እንደ ..ስሌት.. ዋጋ እንዳለው ልነግረው እወዳለሁ፡፡ አሊያስ ..ማሽን.. መሆኔም አይደል፡፡
ስሜታዊው አእምሮ (emotional mind) እንደ ስሌታዊው አእምሮ (emotional mind) ያለ ማብራሪያ ባያቀርብም ነፀብራቆቹ ግን ስለ ኑባሬ ይመሰክራሉ፡፡ የፍቅርም ሆነ የደስታ ስሜቶች መኖራቸው ቢታወቅም የፍቅርን ክብደትም ሆነ በሳቅ የተገለጠውን የደስታ መጠን የምንለካበት ፖለ ሜትር የለም፡፡ ..ስሜታዊ መግለጫህን ወዲያ ጣለው.. ለሚለኝ ሰው ይህንን የጂ ማርቼንኮን የሙግት ሀሳብ ያጤነው ዘንድ እጋብዘዋለሁ፡፡
ፍጥረት ውበቱን የሚቀዳጀው ዲዳ በሆነው የሜካኒክሱ ህግ ብቻ እንዳልሆነ ይታወቅ ዘንድ ማርቼንኮ የሚሉት ይህንን ነው፡፡ ..አንድ የሥነ ፍጥረት ሊቅ የሁለት ፍቅረኛሞችን ከንፈር ለከንፈር መሣሣም በከንፈር አካባቢ የሚገኙ በቁጥር የበዙ ጀርሞችን ከመለዋወጥ ሂደት የበለጠ ትርጉም ካልሰጠው ሰውዬው ጤነኛ አይደለም ማለት ነው.. እምነት ስለ አዋቂው ፈጣሪ ብቻ ሳይሆን ፍቅርን የሚገድለውን እኩይ ሃሳብና ምግባር የሚዳኝበትን ..ህሊና.. የተባለን ስውር ዳኛ በሁላችን ውስጥ ስለማኖሩም ሆነ ሰዎች የሚተዳደሩበት የሞራል ህግ እንደሰጠ ተገልጿል፡፡
ይሄም ውድና ውብ ነገር (ethical objectivity) የጥንቱ  ፍልስፍና አካል ቢሆንም ምንጩ እግዚአብሔር ስለመሆኑ ግን ተፃራሪ አላጣውም፡፡ ..ፕራክቲካል ፊሎሶፊ.. ከሚባሉቱ ውስጥ ከሎጂክ (ሥነ - አመክንዮ)፣ ኢስቴቲክስ (ሥነ - ውበት) ቀጥሎ የሚመጣው ..ኤቲክስ.. የተሰኘው ስለ ሰው ልጆች ሞራላዊ ህይወት የሚያጠናው ዘርፍ ነው፡፡ ለህይወት ውበትን ከሚያጐናጽፏት ውድና ክቡር ነገሮች መካከል ሞራል ከፍተኛው ሲሆን የዕውቀት ማጠንጠኛዎችም አሉት፡፡ ..መልካም.. እና ..ክፉ.. ብለን የምንበይንበት የሞራል ሃሳብ ከዬት መነጨ? ከማለት ተነስቶ ሃሳቦቹን ያጠመድንባቸውም የግንዛቤ ስልቶች ይዳስሱበታል፡፡
What is our perception of right and wrong?
What is our perception of Beauty and deformity?
How do we experess when we say that action are
good or ill desert? በማለት ተጠይቆ ይተነተናል፡፡
yA¼ùØ ዓላማ ስለዚህ ነገር ዝርዝር መግለጫ መስጠት ባይሆንም ጉዳዩን ለማብራራት የሚያስችል የመተንተኛ ዘዴ (Rational method) እንደተበጀለት መጠቆሜ ነው፡፡ yእግዚአብሔር ህላዌ ሲፈተሽ በኖረበት የአዋቂ አእምሮ ..በኦንቶሎጂ አፍ ሞራል..፣ ..እውን ሞራል የሚባል ነገር አለን?.. መባሉንም ሆነ፤ በ..ኢስትቲሞሎጂ ኦፍ ሞራል.. በኩልም ..እንዴት ልናውቀው እንችላለን?.. ተብሎ ተጠይቆ ስላቀረቡት ምሁራዊ ትንታኔዎች ማስታወሴ ነው፡፡ ሆኖም እንደ እግዚአብሔር ህላዌ ሁሉ የሞራልን ፍፁማዊ ዋጋ የካዱት ብዙ መሆናቸውን ታዝቤያለሁ፡፡ ከነዚህም መካከል ሞራል የሰብዓዊ ስምምነቶችና ልምዶች ውጤት እንጂ በራሱ ተጨባጭ ለመሆን የሚያስችለው ተፈጥሯዊ መሠረት እንደሌለው ለመግለጽ Pyrrho የተባለው ሊቅ ያለው እንዲህ ነው፡፡ “Nothing was honorable or dishonorable, Just or Unjust, And so universally, he held that there is nothing really existent, But custom and convention governs human action”
ለእኔ ግን ይሄ አስተያየት ስለ እግዚአብሔር አለመኖር ከሚነግረኝ ከሃዲ ሃሳብ የተለየ ትርጉም አይሰጠኝም፡፡ ጥርጣሬው ሎጂካዊም ይሁን ሳይኮሎጂካዊ (ስሌታዊና ስሜታዊ) አልቀበለውም፡፡ ምክንያቱም በሃሳቤም ይሁን በድርጊቴ ልክ መሆን ያለመሆኔን የሚነግረኝ ዳኛ በዋነኝነት የሚገኘው በምኖርበት ማህበረሰብ ባህል ውስጥ ሳይሆን ስውር ሆኖ በውስጤ ከተቀመጠው ተፈጥሯዊ ህሊና ውስጥ ነው፡፡ ድርጊቴ ጠማማ ወይም ቀና ስለመሆኑ አስቀድሞ የሚነግረኝ ይህ የፍጥረቴ አካል እንጂ ማንም አይደለም፡፡ በመጽሐፍም የተፃፈ ህግ የሌላቸው ህዝቦች እንኳ ህሊናቸው እርስ በእርሱ ሲካሰስ የህግን ሥራ ስለመፈፀማቸው የተፃፈ ነው፡፡ ማህበረሰባዊም ሆነ ሃይማኖታዊውም ህግ የግለሰብን የሞራል አቅጣጫ የመግራት ኃይል ቢኖረውም የሞራል ዓይነተኛ ምንጩ ግን መንፈሳዊ እንጂ ማህበራዊ አይደለም፡፡ የሰው ልጅ ህሊና እኩዩን የመውቀስ፣ ሰናዩን የማወደስ ተፈጥሮን kእግዚአብሔር የተቸረው ቢሆንም በዚያ ብቻ በመደገፍ ግን ተፈላጊውን ውበትም ሆነ የፍቅር ዓለም መመሥረት አይቻልም፡፡ ከዚህ በክፉና ደግ በታጠረ ስብዕና በላይ ለመንገሥም yእግዚአብሔር ምህረትና እምነት ያስፈልጋል፡፡ ፍቅር፣ የዋህነት፣ ትህትና ያለበትን ህይወት አጥብቆ መሻት ይጠይቃል፡፡ ከዚህ የሚሸሹ ሁሉ kእግዚአብሔር ሃሳብ ጋር ይተላለፋሉ፡፡ ለሽሽታቸው የትኛውንም ምክንያት ቢደረድሩም ሀቁ ግን ምን እንደሆነ ያውቃሉ፡፡ ያም ..እኔ.. ባይነት ነው፡፡
ጀርመናዊው ዝነኛ ፈላስፋ ፍሬድሪክ ኒቼ በአእምሮው የላቀ ችሎታ የነበረው ቢሆንም ስለ ራሱ የነበረው ግምት ግን የጉድ ነበር፡፡ ኒቼ ራሱን ከሰቀለበት ከፍታ የተነሳ ማንንም ከመጤፍ የማይቆጥር ሲሆን ፍልስፍናው ራሱ ልዕለ ሰብ (Superman)  በመፍጠር ላይ ያተኮረ ስለነበር እንደ ጌታ ሳይሆን እንደ ሎሌ ሆኖ ወደዚህች ምድር የመጣውን ክርስቶስ ክርስቶስ ኢየሱስ አምርሮ ይጠላው ነበር፡፡
ሆኖም የኒቼ ፍፃሜ እጅግ የሚያሳዝን ሲሆን ከምኞቱ ፍፁም ተቃራኒ የሆነን ህይወት ለመግፋት ተገድዶ ነበር፡፡ ከሁሉም የላቀ ሰው መሆኑ ቀርቶ እንደ ልጅ ጠባቂና ተንከባካቢ የሚያሻው፣ ግራ የገባው ሰው ሆኖ በመገኘቱ ኑሮው የእህቱን ከአጠገቡ ያለመለየት መስዋዕትነት የጠየቀ ነበር፡፡ በጣም አስገራሚው የታሪኩ ክፍል ግን ኒቼ ጥቂት ቆይቶ በማበዱ ምክንያት ፍልስፍናውን ሁሉ የረሳ ቢሆንም ከቶም ያልረሳው ነገር ፀረ ክርስቶስ አቋም ያለው መሆኑን ነበር ይባላል፡፡ ግና ኒቼ ከ..እኔ.. ባይነቱ ውጪ ይህንን ለማድረግ የሚያበቃ ከቶም በቂ ምክንያት አልነበረውም፡፡
ዶክተር ጆን ላውንሰን እንደዚህ ስላሉ ሰዎች የሚገልፁት እንዲህ በማለት ነው [Pagans have no value beyond the self...they finally understand the great god “ME” is and idol with feet of clay…those who kneel before him are crying inside.”  ግርድፉ ትርጓሜውም እንዲህ የሚል ነው ..ሃይማኖት የለሾች ከራሳቸው አብልጠው ዋጋ የሚሰጡት ነገር የለም፡፡ ቆይተውም እግዜር ያደረጉት ትልቁ ..እኔ.. እግሮቹ ሸክላ የሆነ ጣዖት መሆኑን ይረዳሉ፡፡ ...በእሱ ፊት የሚንበረከኩም ሁሉ ውስጣቸው ያለቅሳል፡፡..
ከስሌትም ይሁን ከስሜት አንፃር እግዚአብሔርN ለመካድ የሚያስችል በቂ ምክንያት የለም እያልኩ ነው፡፡ በአዲስ አድማሷ የአማኝ አላማኝ ክርክርም ላይ እስካሁንም ላለማመን ሰበብ እንጂ በቂ ምክንያት አልቀረበም፡፡ እንዲያውም ከክርክሩ ይልቅ ዘለፋው መግነኑ ሌላም ጥያቄ እንድጠይቅ እያስገደደኝ ነው፡፡ እስካሁንም ዳር ዳር የምለው እሱኑ ለመጠየቅ ነው፡፡ ..ዳግመኛ በእግሬ ስራመድ ላታዩኝ በክንፍ ወደ ላይ ወጥቻለሁ..ያሉን ሰው ከወጡበት ..ከፍታ.. ወርደው ዳግመኛ እርግጫ የመጀመራቸውን፣ ጨዋነት በጐደላቸው ቃላት ሃሳባቸውን የመግለፃቸውን ምስጢር ምንነት ለማወቅ እንድሻ ተገድጃለሁ፡፡ ይህን በፈለግሁበት ሰዓትም የክህደትን ሦስት ምክንያቶች የሚነግረኝን ሰው አገኘሁ፡፡ ዎች ማ ኒን፡፡
ይህ ሰው ከሃዲነትን ሦስት ቦታ ከፍሎ የሚመለከት ሲሆን የመጀመሪያዎቹን ..ድርቅ ያሉ.. ከሃዲዎች ይላቸዋል፡፡ እነዚህ ስለ እግዚአብሔር መኖርም ሆነ ያለመኖር ግድ የማይሰጣቸው፤ ለመኖሩም ሆነ ላለመኖሩ የሚያቀርቡት ምክንያት የሌላቸው ናቸው፡፡ ሁለተኞቹን ..ምሁራዊ ክህደት.. ሲለው በዓለማችን እንደነዚህ ዓይነት ሰዎች ቁጥር ጥቂት ሲሆን ስለ እግዚአብሔር መኖር የሚገልጡ የትኛውንም ምክንያታዊ ማሳመኛ ለመቀበል ክፍት የሆኑ ስለመሆናቸው ይገልፃል፡፡
ሦስተኛውና ረድፍ ደግሞ በከንቱ ..ምክንያት ደርዳሪነት.. የተያዘ መሆኑን ጠቁሞ ክህደታቸው ከምክንያት ጋር ሳይሆን ከባህሪያቸው ጋር የተቆራኘ ስለመሆኑ ይገልፃል፡፡ እንደዚህ ዓይነት ሰዎች ምክንያት ቢያቀርቡም እንኳ ቀማኞች ህግ እንደሌለ፣ ሰነፍ ተማሪ ዕውቀት እንደሌለ፣ እኩያና ጠማማ ሰዎችም ፍትህ እንደሌለ ለማሳመን እንደሚፈጥሩት ዓይነት መሆኑን ያስረዳል፡፡ በዚህ ዓይነት ሁነታ ውስጥ ያለ ግለሰብ |እግዚአብሔር የለም.. ካላችሁ ..እሱስ ይሁን ምግባርህ ግን እንዴት ነው.. ብላችሁ ጠይቁት፡፡ ..ይህ ደግሞ ስለ እግዚአብሔር የለም.. ካላችሁ ..እሱስ ይሁን ምግባርህ ግን እንዴት ነው.. ብላችሁ ጠይቁት፡፡ ..ይህ ደግሞ ስለ እግዚአብሔር መኖር ተከራክሮ ለማሳመን ከሚደረግ ብዙ ጥረት የተሻለው አቋራጭ ነው፡፡.. ይላል፡፡ ..በዚህች አጭር የህይወት ዘመኔ ከሃዲነታቸውን ከማውቅላቸው ሰዎች መካከል ዘጠና ዘጠኝ ከመቶ የሚሆኑቱ የሥነ ምግባር ሁኔታ አጠያያቂ ሆኖ ተመልክቼያለሁ.. በማለት ነገሩን ይቋጫል፡፡ እኔም ሌሊሣን እንዲህ ብዬ እጠይቃቸዋለሁ፡፡ (ዳግመኛ በዚሁ ጉዳይ ላላወራ በፍራንሲስ ኤ ሸፈር “Escape from Reason”´ የሥልጣን ቃል ተገዝቼ ራሴን ሰብስቤያለሁ ያሉ ቢሆንም) ..በቃ ያሉት ሁሉ ይሁን.. ብዬ ስቀበል፣ መንፈሳዊው ዓለምም የቅዠት፣ እምነትም የቂሎች ጐዳና ተደርጐ ይቆጠር፣ ግን ሥነ ምግባርዎ እንዴት ነው? ባይመልሱልኝም እርሶ የጠሉትን የ..ማግለል.. ፍልስፍና ባህሪ ችግር እንጂ የዕውቀት የማይመስለኝ ክቡሩን ሰው ማዋረድን ሥራዬ ብለው በመያዝዎ ነው፡፡ እርሶ ዝቅ ዝቅ ያደረጓቸው ሰዎች ክቡርነት ግን ኢንጂነርና ዶክተር ስለመሆናቸው አይደለም፡፡ ክቡር ለመሆን ሰው መሆናቸው ብቻ በቂ ነው፡፡ ይህንን የተሳተ ህሊናም በሁሉ የሳተ ነው፡፡
በአሜሪካን አገር ታዋቂና ዝነኛ ከነበሩት ሰባኪዎች መካከል አር. ኤ. ቶሪ የተባሉትን ሰው ስብከት የሰማ አንድ የኮሌጅ ተማሪ ወደ እርሳቸው ቀርቦ ..ቀድሞ bእግዚአብሔር አምን ነበር፣ ኮሌጅ ከገባሁ በኋላ ግን ባነበብኳቸው መፃሕፍት ምክንያት ጥርጣሬዬ ስለበዛ ..የለም.. ወደ ሚል መደምደሚያ መጥቻለሁ.. ባላቸው ጊዜ ቶሪ ፈጠን ብለው የመለሱለት እንዲህ ነው ..እኔም በወጣትነት ዘመኔ የኮሌጅ ተማሪ ነበርኩ፣ ብዙ መፃሕፍትንም አንብቢያለሁ፣ የዶክትሬት ዲግሪም አለኝ፣ ነገር ግን እኔን kእግዚአብሔር የሚያርቅ መጽሐፍ አላገኘሁም፤ ምናልባት አንዳች የተደበቀ ምክንያት ካልኖረህ በቀር አንተም ቢሆን እግዚአብሔር ስላለመኖሩ የሚያረጋግጥ አንድም መጽሐፍ አላነበብክም፡፡ የሆነውስ ይሁን የምግባርህ ጉዳይ እንዴት ነው?.. ወጣቱም መለሰላቸው ..በእርግጥ ምግባሬ ድሮ እንደነበርኩት ጥሩ አይደለም፡፡..
ሌሊሣ ፈላስፋው ኪርካርድ (Kierkegaard) ..የላይኛውና የታችኛው (መንፈሳዊው እና ገሃዳዊው) ዓለም የሚግባቡበት የጋራ ቋንቋ የለም.. ብሎ ስለነገረኝ፣ ..ተስፋ፣ ፈጣሪ፣ ጥቅል እውነትና ገነት የማይጨበጡ እውነቶች ናቸው.. ስላለኝ ራሴን ከጫወታው አግልያለሁ በማለት ከንቱ ሰበብ ቢደረድሩም “A critical History of Greek philosophy” ፀሐፊ ደብሊው ቲ ስቴት ግን ጨዋነት ስላረበበበት ምሁራዊ ክርክር ተግባቦታዊ ስልት ሲገልፁ፤ የትኛውም ፈላስፋ የራሱን ቀመር ሲያወጣ የሌላውን አጣጥሎ እንዳልሆነ ይጠቁማሉ፡፡ ..የአርስቶትል ቀመር የፕሌቶን፣ የስፔኖዛ ቀመርም የዴካርትን ጨርሶ የደመሰሰ አልነበረም፡፡.. ይላሉ፡፡ ይልቁንም አርስቶትል የፕሌቶን ዕይታ እንደ ግብአት የተጠቀመ ሲሆን ስፔኖዛም ስለ ዴካርት የተከተለው ያንኑ መንገድ እንደሆነ ያሳስባሉ፡፡
ሌሊሣ ሆይ ፍልስፍናን እንደ ሃይማኖት እከተላለሁ ካሉስ ይህንን ሥርዓት መከተል ይገባል፡፡ ፕሌቶ በአስተሳሰቡ ከዚህ ከሚታየውና ከሚጨበጠው ዓለም ተሻግሮ የሄደ ..እምነታዊ.. ቢሆንም በዚያ ደረጃ ያስብ ባልነበረው ተማሪውና ደቀመዝሙሩ አስተሳሰቡ የተናቀ አልነበረም፡፡ አርስቶትል ከፕሌቶ ..ዕውቀት.. አልጨበጥ ያለውና ያልተዋጠለት ሃሳብ ቢኖርም እንደ እርሶ አላንጓጠጠውም፡፡ ፍልስፍና ..ጐርምሻለሁና ራሴን መቻል ይገባኛል.. ከማለቱ አስቀድሞ መነሻው ሥነ መለኮት እንደነበር መዘንጋትም ሆነ እስከዛሬም ቢሆን yእግዚአብሔርN ግዛት የፍልስፍናው ማነፃፀሪያ የማያደርግ ፈላስፋ እንደሌለ ሁሉም ይገነዘበዋል፡፡
ነገሬን እየቋጨሁ ነው፡፡ ጽሑፌን የጀመርኩት በእምነቴ በኩል ስላገኘሁት የስሜትና ስሌት ተፈጥሯዊ ተገንዝቦ ፍንጭ በመስጠት ነው፡፡ ቋንቋው ሃይማኖታዊ ቢመስልም ስሜታዊ መግለጫው ግን በሁሉም ሠፈር ያለ ነው፡፡ ከጥንቱ የሞራል ፍልስፍና አራማጆች መካከል የአንበሳውን ድርሻ የሚወስደው ሶቅራጦስ ትኩረቱን በውበት፣ በመልካምነትና እውነትን በመፈለግ ላይ ያደረገ ፈላስፋ ሲሆን ራሱን እንደ ፈላስፋ ከመቁጠር ይልቅ ግን እነዚህን የህይወት ቅመሞች ምንነት ያብራራ ዘንድ kእግዚአብሔር ዘንድ ተልዕኮ እንደተሰጠው አገልጋይ መቁጠር ይቀለው ነበር፡፡ ሰውየው ሁሉን የሚያብራራው በምክንያት እያስደገፈ ቢሆንም ያንን ያደርግ ዘንድ ይገፋፋው የነበረው ውስጣዊ ድምጽ (inner voice) ምንነት መተንተን አይደለም፡፡ ዛሬ፣ ዛሬ ስለዚህ አይነት ድምጽ ተቀባብተው የሚቀርቡ ልብ ቀስቃሽ ምሥራቃዊ አስተምህሮቶች በመኖራቸው ልምምዶቹ ሰው ረቂቅ ሃሳብን የሚያስተናግድበት ጥልቅ ስሜት እንዳለው ከመጠቆሙ በቀር፣ የአካሄዱን ጤናማነት ሳያጤን ማንም ይለማመዳቸው ዘንድ አልመክርም፡፡ ድምጽ ሁሉ አንድ ምንጭ የለውም፡፡ ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል፡፡ ሞራልን በተመለከተ ግን ከሰው አዋቂነት በላይ ግምት ሊሰጠው የሚገባ ሲሆን አዋቂ የሆነ አንድ ግለሰብ ፍቅር፣ ትህትናና ርህራሄ የጐደለው ከሆነ ..ሚሽን.. ማለት እሱ ነው፡፡ የዛሬው ዘመን ሰዎች ..ከክርስትና በፊት ክርስቲያን የነበረው.. የሚሉት ሶቅራጦስ ግን ተማሪው ፕሌቶ እስኪደነቅበት ድረስ ራሱን ልዩ ሰው አድርጐ ያልቆረጠበት ምስጢር፣ ብዙ እያወቀ ምንም እንደማያውቅ የሆነበት ..የማውቀው ያለማወቄን ነው.. የማለት ትህትና ምንጩ እግዚአብሔር አልነበረም ለማለት አልችልም፡፡

 

Read 6375 times Last modified on Sunday, 24 July 2011 07:21