Sunday, 24 July 2011 07:23

ማንዴላ - የፍቅርና የይቅርታ አባት

Written by  ከበደ ደበሌ ሮቢ
Rate this item
(1 Vote)

አሁን፤ በመላው ደቡብ አፍሪቃና በአህጉር አፍሪቃ፤ እንዲሁም በሌላው ዓለም በኒልሠን ማንዴላና በነፃነትና ፍትህ ወዳጆች ዘንድ የማንዴላ ልደት እየተከበረ ነው፡፡ ከዘጠና ሶስት ዓመታት በፊት በአህጉር አፍሪቃ ደቡባዊ ክፍል፣ በደቡብ አፍሪቃ ሪፐብሊክ ኒልሠን ማንዴላ የተሠኘ ሠው በተወለደበት ወቅት፣ የአፓርታይድ ሥርዓት መድልኦና ግፍ ያስከተለውን ቁጣና ሠብአዊና ማኅበራዊ ጉሥቁልና በፍቅርና በይቅርታ፤ በምኅረትና በሆደ ሠፊነት የፈወሠ አፍሪቃዊ ልብ ተወለደ፡፡

ከአንድ መቶ ሃያና ከአንድ መቶ ሠላሣ ዓመታት በፊት፤ በ1880ዎቹ መገባደጃ ላይ ዓለም የሠው ልጅ ከአቅሙ በታች በሆነ አስተሣሰብ በመቀየዱ ምክንያት፤ ሠብአዊና ማኅበራዊ ክብርን ያዋረዱ ተፈጥሮአዊና ህጋዊ መብትን የደፈሩ... ከአራት ያላነሡ ፖለቲካዊ ተግዳሮቶችን (Political Challenges) ለመጋፈጥ የተገደደችበት ወቅት ነበር፡፡ tGÄéècÜ:- ባርነት (Slavery)\ አፓርታይድና ዘረኝነት (Apartaied & Racism)\ የመላው ዓለም ላብ አደሮች የስምንት የሥራ ሠዓት ጥያቄና ትግል (Proletarian movement)\ እና ቅኝ ግዛት (Colonialism) ናቸው፡፡
በዚህ ወቅት አራት ሚስቶች ያሉት የኒልሠን ማንዴላ ወላጅ አባት፤  ጋያውን እየማገ አያት ቅድመ አያቶቹ በተወለዱበት ደቡብ አፍሪቃ ስለሰፈነው የነጮች የበላይነት፣  የጥቁሮች የበታችነት ስለፀደቀበት የአፓርታይድ ሥርዓትና ስለ ነፃነት ትግል ያሰላስል ነበር፡፡ በዚሁ ዘመን በሰሜን አሜሪካ በፍትሀዊ አቋማቸው ምክንያት እነፕሬዚዳንት አብርሀም ሊንከንን ለመግደል ያበቃ የነጮች የበላይነትን፣ የጥቁሮች የበታችነትን በህግ ጭምር የደነገገ ዘረኝነት (Racism) ሰፍኖ የነበረ ሲሆን፤ ከዚህ ጥቂት ቀደም ብሎ እዚሁ አሜሪካን ውስጥ ከታላላቅ አእምሮዎች የመነጩ ሁለት ታላላቅ ተግባራት ታይተዋል፡፡ ለዓለም ህዝቦች በሙሉ ሥልጣኔን ከፍ ያደረጉት ሁለቱ ታላላቅ ተግባራት:-  በሃሣበ ትጉሁ የአሜሪካን ሣይንቲስት ልጅ ለፍሬ የበቃው የኤሌክትሪክ ኃይል (ኃይለ ብርሀን) እና የስልክ አገልግሎት ጅማሬ ይፋ መሆን ናቸው፡፡
በ1882 ዓ.ም የህይወት የንብረትና የተለያየ የትግል ስልት መስዋዕትነት የጠየቀው የዓለም አቀፍ የላብ አደሮች ንቅናቄ ሥምንት የሥራ ሠዓት ጥያቄ ምላሽ ያገኘበትን አንደኛ ዓመት አከበረ፡፡ ከዚህች ዓለም የተግዳሮት ትልልቅ ጥርሶች አንዱ ከመላው ዓለም ልብና አእምሮ ላይ ተነቀለ፡፡ የመላው ዓለም ሠርቶ አደሮች መብት ተፈወሰ፡፡   
በ1888 ዓ.ም ኰሎኒያሊዝም አንድ ሺህ ኪሎ ሜትር በባዶ እግሩ በተጓዘ መቶ ሺህ የኢትዮጵያ ገበሬ ሠራዊት ቆራጥ ተጋድሎ አድዋ ላይ ተሸነፈ፤ ከዚህ በኋላ የአድዋ ድል በመላው ዓለም ለተቀጣጠሉ የጥቁር ህዝቦች የነፃነት ተጋድሎዎች ብርቱ የመነሳሳት ጉልበት ሰጠ፡፡ እንግሊዞች የዓለም ታሪክ ተገለበጠ አሉ፡፡ ምኒሊክ በሌሉበት የጥቁር ህዝቦች የነፃነት ትግል መሪ ሆነው ተመረጡ፡፡ ጥቁር ትልቅ ትል ነው፤ ቅንቡርስ ነው እንጂ ነፍስ ያለው ሰው አይደለም ብሎ የመጣው የቅኝ ገዢ ሠራዊት አ²? ጄኔራል ባራቴሪ፤ ጦር ፍርድ ቤት ቀርቦ ማዕረጉ ተገፈፈ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ክሪስፒ በፈቃዱ ሥልጣኑን ለቀቀ፡፡ የንጉሡ የልደት ቀን የሀዘን ቀን እንዲሆን ተወሠነ፡፡ ሚላን ፍሎረንስ éM:- ምኒሊክ ለዘላለም ይኑር በሚሉ ሠልፈኞች ተጥለቀለቁ፡፡
እውነትና ጀግንነት ፍትህና ርትዕ አሸነፉ፤ ኮሎኒያሊዝም በአፍሪቃ ምድር ድል ተመታ፡፡ አሸናፊው የኢትዮጵያ ገበሬ ሠራዊት የካቲት ሃያ ሶስት ከምሽቱ አራት ሠዓት ላይ ማርያም ቤተ ክርስቲያን (እንዳ ማርያም) ተሠባስቦ በአንዱ እግሩ ቆሞ ቀኙን የሰጠውን አምላኩን አመሰገነ፡፡
በዚህም በዚህች ዓለም ልብና አእምሮ ላይ ከተሰኩ ጥርሶች አንዱ ተነቀለ፡፡ ማንዴላ ሀምሌ 11 ቀን 1910 ዓ.ም ልክ የዛሬ ዘጠና ሶስት ዓመት ተወለደ፡፡ መሉ oÑ:- ኔልሠን ሮሊህላህላ ማንዴላ ሲሆን፤ የተወለደበት ሥፍራ:- ምቬዞ ነው፡፡ ከወላጅ አባቱ ሶስተኛ ሚስት የተወለደው ማንዴላ የዘጠኝ ዓመት ልጅ እያለ አባትየው ወደ ጐረቤት ወዳጆች ሄዶ፣ ጋያ በመሣብ ላይ እያለ የማይቋረጥ ሣል በመቀስቀሱ በሣንባ በሽታ በዚያው አርፎአል፡፡
የአፍሪቃውያን ብሄራዊ ጉባኤ አባል የሆነው ማንዴላ፤ በ1986 ዓ.ም ከአሥራ ሰባት ዓመታት በፊት የመጀመሪያው ጥቁር የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ሲሆን፤ እርሱም ነፃይቱ ደቡብ አፍሪቃም እንደገና ከነፃነት መንፈሥ ተወልደዋል፡፡ ማንዴላ በአገሪቱ ትልቅ የፖለቲካ ሥልጣን የአገሪቱ መሪ እንዲሆን በሙሉ ድም ከመመረጡ አስቀድሞ ንቁ የፀረ አፓርታይድ ትግል አራማጅ ነበር፡፡ እንዲሁም የአፍሪቃውያን ብሄራዊ ጉባኤ ወታደራዊ ክንፍ ኡምኩሆንቶ ዊሲዝዊ መሪ በመሆን የነፃነት ተጋድሎውን መርቷል፡፡ በ1954 ዓ.ም ከአርባ ዘጠኝ ዓመታት በፊት በአሻጥርና በሌሎች ተንኮል በተመላባቸው ክሶች ተከሥሦ፣ ለሃያ ሰባት ዓመታት በሮቢን ደሴት (Robben Island) በአፓርታይድ የግዞት እሥር ቤት እንዲቆይ ተደርጓል፡፡ የካቲት መጀመሪያ 1982 ዓ.ም ከሃያ አንድ ዓመታት በፊት ከግዞት እሥር ቤት ወጣ፡፡
በ1986 ዓ.ም ከግዞት እሥር ቤት ከወጣ በኋላ ፓርቲውን መርቷል፡፡ ከ1986 እስከ 1991 ዓ.ም አገሪቱን በፕሬዚዳንትነት በመራባቸው አምሥት ዓመታት ውስጥ ከሁሉም በላይ ለሠላምና ለእርቅ፤ ለይቅርታና ለምኅረት ተሥፋ ለመላበት አዲስ አገርና ህዝብ ግንባታ ቅድሚያ ሰጥቷል፡፡ ከአፍሪቃ ኢግዞሣ ከሚሰኘው ጐሣ የሚወለደው ማንዴላ በተለምዶ በአገሬው ዘንድ ማዲባ በመባል ይታወቃል፡፡
ከ250 በላይ ሽልማቶችን አግኝቷል፡፡ ከአሥራ ሥምንት ዓመታት በፊት በ1985 ዓ.ም ታላቁን ዓለም አቀፍ የሠላም ሽልማት (Nobel Peace Prize)\ ተቀብሏል፡፡የአያት የቅድመ አያቶቹ ዝርያ ሥረ መሠረት፣ ከጥንት የደቡብ አፍሪቃ ንጉሣውያን ቤተሠቦች ደም ይዋረሣል፡፡ አባትየው አራት ወንድና ዘጠኝ ሴቶች ልጆች ሲኖራቸው፤ ለማንዴላ የሠጡት መጠሪያ ሥም:- ሮሊህላህላህ (Rolihlahlah) የሚል ነው፡፡ ትርጓሜWM:- የዛፉን ቅርንጫፍ መሣብ የሚል ነው To Pull a branch of a tree. በህፃንነቱ መምህሩ የሆነችው ሴት አስተማሪ ኔልሠን (Nelson) የሚል የእንግሊዝኛ ሥም አወጣችለት፡፡
በዘጠኝ ዓመቱ ነው አባቱ ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት፡፡ ማንዴላ በአሥራ ስድስት ዓመቱ አዳሪ ትምህርት ቤት ገባ፡፡ ወደ ሂልድታዋን ሄዶ ኮሌጅ ከገባ በኋላ፤ በአሥራ ዘጠኝ ዓመቱ ለትምህርት ተቋሙ ሩጫ የመሮጥና የቦክስ ስፖርት የማዘውተር ፍላጐት አደረበት፡፡
ማንዴላ በፎርት ሄር ዩኒቨርሲቲ ከኦሊቨር ታምቦ ጋር ተገናኘ፡፡ ማንዴላና ታምቦ የረጅም ዘመን ባልንጀሮችና ባልደረቦች ለመሆን የቻሉት ከዚህ በኋላ ነው፡፡ ከተማሪዎች የመማክርት ጉባኤ ጋር yዩኒቨርሢቲWN ፖሊሲ በመቃወሙ ከዩኒቨርሲቲW ለመልቀቅ ተገድዷል፡፡ በለንደን ዩኒቨርሢቲ ህግ ያጠናው ማንዴላ ዘበኛ ሆኖ ሠርቷል፡፡ እንዲሁም በጆሀንስበርግ የህግ ተቋም በፀሀፊነት በመሥራት ላይ እያለ በተልዕኮ ትምህርት የመጀመሪያ ዲግሪውን ከደቡብ አፍሪቃ ዩኒቨርሲቲ አግኝቷል፡፡
ከ1940 ዓ.ም በኋላ ማንዴላ ሠላሣ ዓመት እንደሞላው የአፓርታይድን ፖሊሲ የሚደግፍ ምርጫ መደረጉን እንዳወቀ በፖለቲካው ዓለም በንቃት መሣተፍ ጀመረ፡፡ በ1944 ዓ.ም የአፍሪቃውያንን ብሄራዊ ጉባኤ (African National Congress) መራ፤ እንዲሁም በ1947 የህዝቡ ጉባኤ (Congress of the people) የተሠኘውን ፀረ አፓርታይድ አቋም ያለውንና የነፃነት ድንጋጌ Freedom Charter የቀረፀውን የፖለቲካ ተቋም መራ፡፡ በዚህ ወቅት ማንዴላ ዕድሜው ሠላሣ ሠባት ዓመት ነበር፡፡
ማንዴላና ሌሎች 150 አጋሮቹ በ1948 ዓ.ም December 5 ቀን ተከሰሱ፡፡ በወቅቱ በደቡብ አፍሪቃ ሶስት ቀለም ያላቸው ህዝቦች ይኖሩ ነበር፡፡ አብላጫ ጥቁሮች ጥቂት ነጮች እና ህንዶች፡፡ ይሁንና የመንግሥት አመራሩ የአፓርታይድ ዘረኛና አድሎአዊ ፖሊሲ በሚያራምድ በጥቂት ዘረኛ ነጮች አመራር ሥር የወደቀ ነው፡፡ የሚደረጉ ምርጫዎች  ሁሉ ለጥቂት ነጮች የፖለቲካ ፓርቲዎች ያደሉና ያጋደሉ ናቸው፡፡
በመሠረቱ ተፈጥሮአዊ ሊሠኝ በሚችል የብዙ መቶ ዓመታት ታሪኩ ይህ የጥቁሮች ምድር ነው፡፡ ነጮችም ሆኑ ህንዶች ከአውሮፓና ከኤዢያ መጥተው የሠፈሩ ናቸው፡፡ በዚህ ውስጥ የህንዶች ሚና ኢምንት ነው፡፡ ብቸኛው የነፃነት ተጋድሎ መሪ ፓርቲ ANC ከ Pan Africanist Congress ከተከፈለው የጋና የነፃነት ንቅናቄ እና ከሌሎች የገንዘብ ድጋፍ ቢያገኝም የዘር መድልኦ የሌለበት ፍትሀዊ ሥርዓት ለማስፈን ትግሉ የሚጠይቀው መስዋዕትነት ቀላል አልነበረም፡፡
በ1953 ዓ.ም ማንዴላ የአርባ ሶስት ዓመት ጐልማሣ እንደሆነ  የህዝቡ ተዋጊ ጦር Spear of the nation የሚል ትርጓሜ ያለውንና የፓርቲው ወታደራዊ ክንፍ የሆነውን ..ኡምክሆንቶ ዊስዝዊ.. መምራት ጀመረ፡፡ የነፃነት ተዋጊውን ለሽምቅ ውጊያ guerrilla fighting ማሠናዳት እና አሻጥሮችንና የተንኮል ተግባራትን ማምከን የማንዴላ ዋነኛ ሥራዎች ነበሩ፡፡ ማንዴላ ራሱም እንደሚያወሳው፤ ANC ለአያሌ ዘመናት ያደረጋቸው ፀረ አፓርታይድ ሠላማዊ ትግሎች እምብዛም ውጤት ያመጡ ስላልነበሩ፤ የትጥቅ ትግል ማድረግ የግድ አስፈላጊ ሆኖአል፡፡
በነሀሴ ወር 1954 ዓ.ም በጆሀንስበርግ ፎርት ማንዴላ ታሠረ፡፡ በሥውር እንዲታሰር የተደረገበትን ሥፍራ የአሜሪካው የስለላ ተቋም US Central Intelligence Agency (CIA) ያውቅ ነበር፡፡ ከአንድ ዓመት በኋላ በ July 11th 1963 የኤ ኤን ሲ ታዋቂ መሪዎች በፖሊስ ተይዘው ታሠሩ፡፡
ለአፍሪካ ህዝቦች ለመታገል መላ ህይወቴን በቆራጥነት አሣልፌ የሰጠሁ ሰው ነኝ፡፡ የነጮችን ተዕኖ እዋጋለሁ፤ እንዲሁም የነጮች ተዕኖ በጥቁሮች ተዕኖ እንዳይተካ እዋጋለሁ፤ ሁሉም ሰው በህብርና በፍቅር ዲሞክራሲያዊ ነፃ ህብረተሰብ ፈጥሮ እኩል መብትና ዕድል ኖሮት በአንድነት የሚኖርባትን ደቡብ አፍሪቃ እሻለሁ፤ ይሄ እንደሚሆንም ተስፋ አለኝ . . . ለዚህ ዓላማ ለመሠዋት ተሠናድቻለሁ . . .
የኒልሠን ማንዴላ ድም:- ከእሥር ቤት |During my lifetime I have dedicated myself to the struggle of the African people. I have fought against white domination, & I have fought against Black domination. I have cherished the Ideal of a democratic & the free Society in which all Persons live together in harmony & with equal opportunities. It is an ideal which I hope to live for & to achieve. But if needs be, it is an ideal for which I am Prepared to die...
ኔልሠን ማንዴላ በሮቢን ደሴት ለሃያ ሠባት ዓመታት ሲታሰር፤ እሥረኞች ከባድ የጉልበት ሥራ መሥራትና የእሥር ቤቱን ሁናቴዎች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡ በዘር ልዩነት ሣቢያ በእስረኞች ላይ ከፍተኛ ተዕኖ ይደረጋል፡፡ የፖለቲካ እስረኞች ከሌሎች እሥረኞች በተለየ ሥፍራ ነው ያሉት፡፡ ማንዴላ አንድ ሰው እንዲጐበኘውና በስድስት ወር አንድ ደብዳቤ እንዲፍ ተፈቅዶለታል፡፡ ደብዳቤው በእስር ቤቱ ኃላፊ ሴንሰር ይደረጋል፡፡ ማንዴላ ከለንደን ዩኒቨርሢቲ በተልዕኮ ትምህርት የህግ ዲግሪውን ያገኘው በዚህ ወቅት ነው፡፡
በ1974 ዓ.ም ከሮቢን ደሴት እስር ቤት ወደ ፓልስሙር እስር ቤት ተዛወረ፡፡ ሌሎች የፓርቲው (ANC) መሪዎች ዋልተር ሢሢሉ አንድሪው ምላንጌኒ እና አህመድ ካትራዳ ሬይመንድ ምሀላባ አብረውት አሉ፡፡
በ1980 ማንዴላ ወደ ቪክቶር ቬርስተር እስር ቤት ተወሰደ፡፡ ከእስር ቤት እስኪለቀቅ ድረስ የቆየውም በቪክቶር ቬርስተር እስር ቤት ነው፡፡ በዚህ እሥር ቤት ብዙዎች ጐብኝተውታል፡፡ እንዲፈታም አለም አቀፍ ጥሪዎች qRbêL:- Free Nelson Mandela የሚሉ፡፡ በ1982 ፕሬዚዳንት ዴክላርክ ማንዴላ መፈታቱን አወጁ፡፡  
ፌብሩዋሪ 11 1990 ዓ.ም ማንዴላ ከግዞት ከእሥር ቤት ሲፈታ፤ ለመላው ዓለም በቀጥታ የተለቀቀ ንግግር አደረገ፡፡ ይህ ሰው አሁን የሠባ ሁለት ዓመት አዛውንት ሆኖአል፡፡ ዘመኑ በ1982 የካቲት ወር መጀመሪያ ላይ ነው፡፡ ማንዴላ እንደተፈታ ከሁሉም በላይ ለሠላምና ለእርቅ ሁሉም እኩል ሆኖ ለሚኖርባት አገር መፈጠር ቅድሚያ እንደሚሰጥ ግል አደረገ፤ ጥላቻና በጭፍን ፍርድ መታወር ለሌለባት አዲሲቱ ደቡብ አፍሪቃ በነፃነት ብቅ ማለት . . .   
African National Congress ማንዴላን የፓርቲው መሪ አድርጐ የመረጠው ከእሥር ቤት እንደተፈታ ነው፡፡ የአገሪቱ የመጀመሪያው ጥቁር ፕሬዚዳንት እስከሚሆን ድረስ ያሉትን አራት ተከታታይ ዓመታት ፓርቲውን መርቷል፡፡ በፓርቲ አመራሩም ሆነ በፕሬዚዳንትነት የአመራር ዘመኑ፤ በቀለም ልዩነት ሣቢያ ለሚከሰት አድልኦና ጥላቻ መወገድ፤ ለዜጐችና ለሠው ልጆች ሁሉ ነፃና እኩል መሆን ታግሏል፡፡ በእሥራት ዘመኑ በእርሡና በወገኖቹ ላይ የተፈፀመው ግፍና ጉሥቁልና የአእምሮውን ሚዛን ሳያስተው ትክክለኛና እውነተኛ፤ ነፃና ፍትሀዊ አቋም ካላቸው ነጮች ጋር በአንድነት በፍቅር ለመሥራት ያለውን ቁርጠኛነት አሣይቷል፡፡  
Long Walk to Freedom ወደ ነፃነት የተደረገ ረጅም ጉዞ ወይም ረጅም የነፃነት ጉዞ በሚል ርዕስ በእንግሊዝኛ ቋንቋ የፃፈው መሀፍ አሥራ አንድ ምዕራፎችና ከሰባት መቶ ሠባ በላይ ገፆች አሉት፡፡
ትግል ህይወቴ ነው:- The Struggle is my life የሚለው ማንዴላ፤ በመሀፉ ላይ የነፃነት ተዋጊው መወለድ ይለናል፤ Birth of a Freedom Fighter
ነፃነት (Freedom) :- የመሀፉ የመጨረሻ ምዕራፍ ንዑሥ ርዕሥ ነው፡፡ ምዕራፍ ስምንት የሮቢን ደሴት እሥር ቤትን የጨለማ ዓመታት ÃœÃL:- The dark Years. ምዕራፍ ዘጠኝ ደግሞ ከእስር ቤት የመውጣቱን ተስፋ Yfn_ÝL:- Beginning to Hope
አብዛኞቹ የአፍሪቃ አገራት ከአውሮጳ ቅኝ አገዛዝ ነፃ የወጡት እ.ኤ.አ በ1960 በእኛ 1952 ዓ.ም ከሃምሣ ዓመታት በፊት ነው፡፡ የቀድሞይቱ ሮዴዢያ የአሁኒቱ ዚምባብዌ ከሌሎች የአፍሪቃ ሃገሮች አንፃር ነፃ ለመውጣት ትንሽ ዘግይታለች፡፡ ደቡብ አፍሪቃ ከአረብ አፍሪቃና ከጥቁር አፍሪቃ (African Contnent) ነፃ ለመውጣት የመጨረሻዋ አገር ነች፡፡ ማንዴላ ከሃያ ሠባት ዓመታት የግዞት እሥር ቤት በተፈታበት እና ከጥቂት ዓመታት በኋላ የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ለመሆን በቻለበት ወቅት:- አዲሲቱና ነፃይቱ ሪፐብሊክ ከነፃነት መንፈሥ ተወለደች፡፡
ደቡብ አፍሪቃ:- ሥሟ እንደ¸ÃmlKtW በአህጉር አፍሪቃ ደቡባዊ ክፍል የምትገኝ አገር ነች፡፡ በዚህች አገር የቆዳ ሥፋት ውስጥ ስዋዚላንድ እና ሌሤቶ የተሠኙ ዓለም አቀፍ ልዕልና ያላቸው ራሣቸውን የቻሉ ሁለት አገሮች እንደ ደሴት ይገኙባታል፡፡ ስዋዚላንድ በስተምሥራቅ ከህንድ ውቅያኖስ ጋር ትዋሰናለች፡፡
ማንዴላ የአገሪቱ መሪ ከሆነ በኋላ ሃያኛው የአፍሪቃ እግር ኳስ ዋንጫ በደቡብ አፍሪቃ መካሄዱ ውድድሩ ስፖርታዊ ባህሪ ብቻ ሣይሆን፤ የብርሃንና የነፃነት ለዛ የሚፈነጥቅ ፖለቲካዊ ገታም ነበረው፡፡ ከስድሣ ዓመታት በፊት የአፍሪቃ ዋንጫ ሲጀመር ኢትዮጵያ ሱዳንና ግብ ደቡብ አፍሪቃን ገሸሽ ያደረጉት በምታራምድው የአፓርታይድ ፖሊሲ ምክንያት ነው፡፡ ሁለቱን ኮሪያዎች ሰሜንና ደቡብ በሚል ለሁለት ለመከፈል ያበቃው ጦርነት፣ በቦታው አንድ ሚሊየን ሠራዊት በነበራት አሜሪካ አጋፋሪነት ዓለም አቀፍ ኅብረ ብሄር ሠራዊት በዘመቻው ሲካፈል፤ ከአህጉር አፍሪቃ በኮሪያ ዘመቻ ላይ የተሣተፉት ኢትዮጵያና ደቡብ አፍሪቃ ናቸው፡፡ ከአንድ ዓመት በፊት:- የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ በደቡብ አፍሪቃ መካሄዱም ለአገሪቱም ሆነ ለአህጉሩ ስፖርታዊ ድምቀት ብቻ ሣይሆን፤ ፖለቲካዊ ገታም ነበረው፡፡ የኦባማ በአሜሪካ ፕሬዚዳንት ሆኖ መመረጥ፣ የዓለም ዋንጫ በደቡብ አፍሪቃ መካሄድ የዘረኝነትና የአፓርታይድ የባርነትና የቅኝ አገዛዝ አስተሣሰቦች ሥር ጨርሶ መነቀሉን ወይ መጠውለግ መድረቁን y¸ÃWJ:- የመላው ዓለም ታላላቅ ድል መታያ ወይ ማሣያዎች ናቸው፡፡ ማንዴላ ዓለም አቀፉን የሠላም ኖቤል ሽልማት በ1985 የተሸለመው፤ ከነጩ ፍትሀዊ የአገሬው ዜጋ ዴ ክለርክ ጋር ነው፡፡ ይሄም ለደቡብ አፍሪቃ የነፃነት አየር ግሩም መአዛ ሆኖ አውዶአል፡፡  
የአራት ልጆች አባት የበርካታ የልጅ ልጆች አያት የሆነው የዕድሜ ባለፀጋ ኔልሠን ማንዴላ፤ ሠኞ ዕለት ልደቱን አክብሯል፤ የዚህ የዘጠና ሶስተኛ ዓመት ልደት መንፈሥ እንደረበበ እነሆ ማንዴላ ለማለት፡፡ ኢትዮጵያ ለደቡብ አፍሪቃ ባለውለታ ነች፡፡ ፀረ አፓርታይድ ታጋዮችን አሠልጥና አስታጥቃለች፡፡ ለማንዴላ ፖለቲካዊና ወታደራዊ ድጋፍ አድርጋለች፡፡
ሠላምዎ ይብዛ በፍቅር
Soli.Deo.Gloria!

 

Read 5393 times Last modified on Sunday, 24 July 2011 07:26