Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Sunday, 24 July 2011 07:50

1/2 ሌሊት - 1001 ትዝታ

Written by 
Rate this item
(6 votes)

አንዴ ራሷን - አንዴ ልቧን - አንዴ ደግሞ እጇን እያመመ ትንሽ ካስጨነቃት በኋላ አሁን ቀለልሳይላት አልቀረም፡፡ ከተኛችበት ተነስታ እግሯን ዘርግታ ተቀምጣለች፡፡ እሷ ህመሟ ሲለቃት እኔ ድካሜ ቁጭ ብዬ እንድቀጥል ስላልፈቀደልኝ ጭኖቿን ተንተርሼ ወገቤን አሳርፌያለሁ፡፡

ዓይኖቼን ወደ እሷ አንጋጥጬ እሷም አንገቷን ዘንበል አድርጋ ለዝምታ በቀረበ ድም እያንሾካሾክን እናወራለን፡፡ ወሬው እሷን ከህመሟ እኔን ከድካሜና ከእንቅልፍ አረሳስቶን የሌሊቱን መግፋት ሳናስብ እንጨዋወታለን፡፡
አንድን የታመመ ሰው ለመርዳት ማድረግ የሚገባኝን ነገር ከማድረግ ባለፈ ፆታዊም ሆነ ወሲባዊ የሆኑ ስሜቶቼን የሚያንፀባርቁ ንክኪዎች ለማድረግ አቅሙም ፍላጐቱም አልነበረኝም፡፡ ምናልባት ግን የእሷ አቅምም ፍላጐትም በተቃራኒው ጫፍ ቢሆን - ምንም አለማድረጌ እኔን ..የሰው ስሜት መረዳት ከማይችሉት.. ወገን እንዳያስቆጥረኝ እየሰጋሁ የእሷን እንቅስቃሴ ሁሉ በጥንቃቄ ነው የምከታተለው፡፡ እያንዳንዷ ንግግርና አካላዊ ንክኪም የሚፈጥርባትን ስሜት የጥርጣሬዬን እውነትነት ለማረጋገጥ ምን ያክል እንደሚረዱኝ ስለምረዳ ክትትሌ ጠለቅ ያለ ነው፡፡
ሁኔታውን እየተነተነ አእምሮዬ ያዘዘኝን ያህል ንግግሬም ንክኪዬም ከአስታማሚነት ወደ ሌላ አይነት ደረጃ ቀስ በቀስ እየተሸጋገረ ነው፡፡ ሽግግሩን በማሳለጥ ረገድ ከጐናችን ሆነው ..አይን ያወጣ.. ሊባል የሚችል መተሻሸት የሚያደርጉት ሃብታይና ደርባባዋ የአፋር ልጃገረድ ያበረከቱት አስተዋዖ ከፍተኝነት ለማንም ..ስሜት ላለው ሰው.. የተሰወረ አይደለም፡፡
ጐረቤቶቻችንN እንዳየቻቸው ካረጋገጥኩ በኋላ ማየቷን እንዳላየሁ ሆኜ እንድታያቸው ጋበዝኳት፡፡ ..አያስጠሉም.. አለችኝ፡፡ ..ኧረ ባክሽ... ገነት የሚያስገባ ስራ ነው የሚሰሩት.. ብዬ ስመልስላት ሳቋ እየተናነቃት ባለጌነቴን ነገረችኝ፡፡ እጆቿ ለባለጌነቴ ቅጣት ለመስጠት ወደ ራሴ እንደተላኩ አልተመለሱም - በፀጉሮቼ መሀል መንሸራሸሩ ሳይመቻቸው አልቀረም፡፡ ይበልጥ ፍላጐቷን ለማወቅ እጆቿን ወደ አንገቴ አስጠግቼ፣ አገጬ ስርጉድ ላይ እንዲቆሙ አደረኳቸው፡፡ ..በጣም ነው የምወዳቸው ወደድሻቸው?.. ጠየኳት፡፡ አዎንታዊ መልስ ሰጥታ እጆቼን እኔ ካደረስኳቸው እሷ ግማሽ መርቃልኝ፣ ደረቴ ላይ እንዲሽከረከሩ አደረገቻቸው፡፡ እኔም አፀፋውን ሆዷ ላይ ቦርጯ ከፈጠሩት አቀበት ቁልቁለቶች ጀምሬ፣ እንደ ግብ ፒራሚድ ተኮፍሰው እስከሚታዩት ጡቶቿ ድረስ አስጐበኘኋቸው፡፡ እንኳን በእጅ ነካክተው ቀርቶ ጨምድደው ይዘው ዥዋዥዌ ቢጫወቱባቸው ነቅነቅ የሚሉ የማይመስሉት ጡቶቿን የቻልኩትን ያህል አፍረጠረጥኳቸው - እንዲህ አይነት ጡት ዳግም መፍጠር የሚችል አምላክ ያለ አልመስል ብሎኝ እንደሆነ አላቅም - ወደ ጡቶቿ ተንጠራርቼ ከልብሷ ውጭ አድርጌ በአፌ አልጐጠጐጥኳቸው፤ በምላሴ አጣጣምኳቸው - እናቱ ገበያ ውላ ረሃብ እንዳሰቃየው ህፃን - እንዲጠባ እንደተለቀቀ ጥጃ - ከጡቷ ተለጥፌ ገተገትኳት፡፡ ከጡቶቿ የተለያየሁት ያንኑ ያክል በሚመስጥ ጣፋጭ ድም ..ቢኒዬ.. ብላ ስትጠራኝ ነው፡፡ የሚቀጥለውን ነገር ለመስማት መጓጓቴን በሚገል መልኩ በፍቅር አይን አየኋት፡፡ ርህራሄን የሚማፀኑ አይኖቿን እኔው ጋር እንደተከለች ..ትወደኛለህ.. አለችኝ፡፡ ከሰዓታት በፊት ያገኘኋት ልጅ እንዲህ አይነት ጥያቄ ታነሳለች ብዬ አልጠበኩም፡፡ እነዚያ ጡቶቿ ባያደነዝዙኝ ኖሮ እንዴት ብዬ እንደምስቅ እኔ ነኝ የማውቀው... ብቻ ላስከፋት አልፈለኩም፡፡ ..እወድሻለሁ.. ብዬ መለስኩላት፡፡ ወዲያው አስከትዬ ..እነዚህ ከጐንሽ የተኙትንም ሁሉንም ሰው እወዳለሁ፡፡ የምጠላው ሰው የለም.. አልኳት፡፡ ፊቷ ወዲያው ሲቀየር አየሁት፡፡ አኮረፈችኝ - ላባብላት ሞከርኩ፤ ወዲያው አልተሳካልኝም፡፡ በጣት ከሚቆጠሩ ደቂቃዎች በኋላ እንደ በፊቱ ሞቅ ያለ ወሬ ማውራት ጀመርን፡፡
በሌላ ሥራ ከተጠመዱት ጐረቤቶቻችን ባሻገር ሌሎች የቤቷ ታዳሚዎች መተኛታቸውና የፋኖሱ መብራትም መጥፋቱ የበለጠ ነፃነት ስለሰጠን ወሬያችንም እንቅስቃሴÃCNM በዚያው ልክ ከፍ እያለ ነበር፡፡ የዚሁ እድል ተቋዳሽ የሆኑት ጐረቤቶቻችን በተደበቁበት ልብስ ውስጥ በስሜት ጡዘት እየተገለባበጡ ያሻቸውን ያደርጋሉ፡፡ የእነዚህ የስሜት ዋናተኞች ግለት ተጋብቶ ሲያብሰከስካት የእኔ እንደ እሷ አለመሆን ገርሟት ነው መሰል፣ ፊቴን ወደ እነሱ እንዳዞር እያመለከተች ..እየተሳሳሙ እኮ ነው.. አለችኝ፡፡ ..ቀናሽ አይደል... ታዲያ ለምን አትስሚኝም.. ለጠየኩት ጥያቄ መልስ ሳልጠብቅ መቼም የምረሳው የማይመስለኝን፣ ልረሳው እንደማልችል በግል የነገርኳትን ተአምራዊ ጡቶቿን እያሻሸሁ አንገቷን - ከዚያም በስሱ ከንፈሯን ሳምኳት፡፡ በመልስ ጉዞዬም ጡቷ ላይ ትንሽ እረፍት ቢጤ ወስጄ ተመልሼ ጋደም ብዬ እያሻሸኋት ጨዋታችንን ቀጠልን፡፡
አነስ ባለችው ቤታችን የመስኮት ቀዳዳዎች መግባት የጀመሩት የሰማይና ምድሩን መላቀቅ የሚያበስሩት ደብዛዛ ብርሃናት፣ እኔን ከደመ ሞቃቷ አሚናት ጉያ ..እንዳይለያዩኝ በስጋት ከተለጠፍኩባት ደረቷ ላይ የባነንኩት የቤታችን መስኮት ሲንኳኳ ነው፡፡ አስጠሊታውን የመንኳኳት ድም ተከትሎ የተላለፈው መልእክት የበለጠ የከፋ ነበር፡፡ ከ..አለቃ.. በኩል የመጣ ..ወደ ሥራ ተሰማሩ ጥሪ!..
***
ቀናት በተቆጠሩ ቁጥር የዚያች ቀን ትዝታዋ እየጠፋ ታሪኩም እየተዘነጋ ነው፡ ለሥራ ጉዳይ የ/ቤታችን ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ቆቦ ላይ ተሰባስበናል፡፡ ቀን ቀን ስልጠና ማታ ማታ ደግሞ ጐሊና ሆቴል እየታደምን አሪፍ ጊዜ ነበር የምናሳልፈው፡፡ ስልጠናው ሲደብረን ከጃቬኖ ጋር ቀልድ ቢጤ በጽሁፍ እንለዋወጣለን፡፡ በመፃፃፍችን መሃል ግን ሳይታሰብ የድሬ ሮቃ ጉዳይ ርእስ ሆኖ ከች አለ፤ ድሬ ሮቃ ሲነሳ አሚናት በአእምሮዬ ድቅን አለችብኝ፡፡ እየረሳኋት እንደመጣሁ ገብቶኛል፡፡ ለአፍታ ናፈቅኋት... በሃሳቤ በእቅፌ ውስጥ አስገባኋት... ጥብቅ አድርጌ አቀፍኳት... ጡቶቿ ደረቴን ወጋጉኝ... በትዝታቸው በአንዴ አቅሌን አሳቱኝ... እስኪርቢቶዬን ሰድሬ የገጠር ለዛዋን ያለቀቀች ግጥም ማስታወሻ ደብተሬ ላይ አሰፈርኩ፡፡
አሚንዬ አሚና የጭፍራዋ ቆንጆ
ካንች ውጭ ከማንም እኔ አልሰራም ጐጆ፡፡
እነዚያ ጡቶችሽ ካስማ ይሆኑኛል፤
የሚያምረው ፈገግታሽ ጣራ ይሆነኛል፤
ማገርም አላጣ ዳሌሽ ይበቃኛል፤
በርም አልፈልግም አንገትሽ መቃ ነው ያገለግለኛል፤
ጭንሽ መስኮቴ ነው ደረትሽ አልጋዬ፤
ግለትሽ ብርድ ልብስ ገላሽ አንሶላዬ፤
አንች የአፋሯ ልጅ አሚን አሚንዬ፤
አትጥፊ ከጐኔ ነይልኝ ጐጆዬ፤
የበረንዳ ልጅ ነኝ አንችን ካጣሁ እኔ፡፡
ቢመወ
ቆቦ

 

Read 16590 times Last modified on Sunday, 24 July 2011 07:54