Sunday, 31 July 2011 12:59

ሳይንሳዊ ማስረጃ ወይስ ማወናበጃ

Written by  ደረጀ ፀጋዬ
Rate this item
(0 votes)

ሁለት (ካለፈው የቀጠለ)
አንባብያን እንደምን ሰነበታችሁ፡፡ እንዲያው ለነገሩ ..ላልጀመሩም ላልጨረሱም ልጆች.. አሉ ዶክተሩ?! ይሁና... ገ ሙሉ ውሸትና ስድብ አንድ መስመር እውነት እንደማይወጣው የሚነግራቸው ጠፍቶ ይሆን? ወይስ ቅዱስ ጆሮም እንዳለው በወሬ ብዛት ህዝብን ለማታለል? ዶክተሩ እድሜ ብቸኛው የእውቀት ምንጭ የነበረበት የአበው ዘመን ትዝ እያላቸው ካልሆነ በስተቀር ..እወቅ ያለው በአርባ ቀኑ ያውቃል.. የሚለው ብሂል ሳይገባቸው ቀርቶ አይመስለኝም፡፡
የዛሬ ጨዋታዬ ዋነኛ ጉዳይ ባይሆንም ከልጅነት ጋር የተያያዘች አንዲት ጥቅስ ጣል አድርጌ ልለፍ፡፡

Sophie’s World በሚል ፍልስፍናዊ ልብ-ወለድ መሐፉ ውስጥ ጆስቴይን ጋርደር እንዲህ
..ጥሩ ፈላስፋ ለመሆን የሚያስፈልገን የሚያደንቅ አእምሮ ብቻ ነው፡፡ ይህንን ደግሞ ህፃናት (ልጆች) በሚገባ ታድለውታል፡፡..
ወደ ዋናው የዛሬ ርዕሰ-ጉዳይ ስንመለስ የምንጨዋወተው ፍጥረተ-መለኮታውያን የመሬትን የዕድሜ ለጋነት ያረጋግጥልናል ብለው የሚያቀርቡትን በመሬትና በተለይም ደግሞ በጨረቃ ላይ ለዘመናት ሲከማች ስለኖረ (አሁንም እየተከማቻ ስላለው በፀሐይና ጭፍሮቿ (Solar System) ውስጥ ስለሚገኝ የአቧራ ብናኝ (Meteoritic dust) ነው፡፡
ለዚህ ሑፌ መረጃ ስቃርም ሃሳቤን በሁለት ምንጮች ላይ አደረኩ፡፡ አንደኛው በዴቭ ኢ.ማትሰን የተዘጋጀ ሲሆን ሁለተኛው በዶ/ር አንድሪው ኤ.ስኔሊን እና ዴቪድ ኢ.ረሽ የታተመ ሑፍ ነው፡፡ ጉዳዩን ለአንባብያን በጥሩ መልኩ ይገልፃል ብዬ ስለገመትኩ በ Dr Andrew A. Snelling and David E. Rush “Moon Dust and the age of the solar System” ከሚል ሑፍ ጋር ለአንባብያን እንደሚመች አድርጌ የተወሰነውን ሃሳብ ወደ አማርኛ መልሻለሁ፡፡
ፍጥረተ - መለኮታውያን በዚህ ጉዳይ ዙሪያ አቋማቸውንና ጥያቄያቸውን ሲያቀርቡ እንዲህ ይላሉ (በሌላም ብዙ አባባሎች ሊገልፁት ይችላሉ፡፡)
..እንደሚታወቀው በመሠረታዊነት ቋሚ በሆነና በማያቋርጥ የፍሰት መጠን የህዋ ብናኞች ወደ ምድር ከባቢ አየር በመግባት በሂደት በምድር ገ ላይ ይዘቅጣሉ፡፡ የዚህን የዝቅጠት መጠን ለመለካት ከተደረጉት ሙከራዎች ሁሉ በ1960 ዓ.ም በሃንስ ፔተርሰን የተሰራው ሙከራ ተመራጭና የተሻለ ሲሆን አመታዊ የዝቅጠት መጠኑም 14 ሚሊዮን ቶን የአቧራ ብናኝ ነው፡፡..
አንባብያንን ላለማሰልቸት የተወሰኑ በቁጥር የተሞሉ ዐረፍተ-ነገሮችን ልዝለልና ጥቅሉን ልቀጥል፡፡
..ይህ አመታዊ የአቧራ ብናኝ መጠን ላለፉት 5 ቢሊዮን ዓመታት በመሬት ላይ ቢዘንብ በአሁኑ ጊዜ ጠቅላላው የመሬት ገ 182 ፊት (53.37 ሜትር) ጥልቀት ባለው የአቧራ ክምር ይዋጥ ነበር!..
..ነገር ግን ይህን የሚያሳይ አንዳችም ምልክት የለም፡፡ ይህ የአቧራ ክምር መጠን በጨረቃም ላይ መገኘት ነበረበት፡፡ በመሆኑም ጠፈርተኞች ይህንን በጨረቃ ገ ላይ ማግኘት ይገባቸው ነበር፡፡ ጠፈርተኞች ወደ ጨረቃ ከመጓዛቸው በፊት በሚያርፉበት ጊዜ በአቧራው ውስጥ ሰጥመው ይቀራሉ ተብሎ ይሰጋ ነበር፡፡ ይህ ባልሆነ ጊዜ የናሳ (NASA) ባለስልጣናት ለምን ዝምታን እንደመረጡ አይታወቅም፡፡ መሬትን በተመለከተ እንደሚታወቀው ከህዋ ወደ ምድር የሚዘንበው የአቧራ ብናኝ በንጥረ ነገር (Elements) ይዘቱ በኒኬልና በብረት የዳበረ ነው፡፡ በተቃራኒው ደግሞ የመሬት የኒኬል ይዘት መጠን በጣም አነስተኛ ነው፡፡ ታዲያ ያ ሁሉ በምድር ገ ላይ መከማቸት የነበረበት የኒኬል መጠን በመሸርሸር ፍፁም ከመሬት የላይኛው ቅርፊት (Crust) ጋር ተዋህዷል ካላልን በስተቀር የት ገባ? እስከ አስር ማይል ጥልቀት ያለው የመሬት ቅርፊት (የመሬት የላይኛው ቅርፊት አማካይ ውፍረት 12 ማይል ገደማ ነው) እንዳለ ከአቧራው ጋር ተላውሶ ካልተቦካ በስተቀር ይህ ግል የንጥረ - ነገር ጥንቅር ልዩነት ያለው አቧራ አሁን በምናየው መልኩ ሊሰወር አይችልም፡፡ ይህን ካልን ደግሞ ጠቅላላው የመሬት የኒኬል ይዘት የተገኘው ከህዋ አቧራ ክምችት ነው እንደማለት ይሆናል!.. በማለት ጥያቄ አዘል መከራከሪያቸውን ያቀርባሉ፡፡
በግርድፉ ሲመለከቱት ጥያቄው ተገቢና አሳማኝ ይመስላል፡፡ ለጊዜውም ቢሆን ይህ ነገር ብዙ የዝግመተ - ለውጥ (evolution) አቀንቃኞችን የረበሸ ጉዳይ ነበር፡፡ ለዝግመተ - ለውጥ መሰረቱ ጊዜ ነው፡፡ ዝግመተ - ለውጥ (በተለይም Macro – evolution) ትርጉም ያለው ሳይንሳዊ መላምት (Theory) የሚሆነው በሚሊዮንና ቢሊዮን ዓመታት የግዜ ማዕቀፍ ውስጥ ነው፡፡ የፍጥረተ - መለኮታውያን ጥያቄና የክርክር መስመር ደግሞ ይህን ያህል የጊዜ መጠን እንደሌለ ያሳያል (እውነት ሆኖ ቢሆን ኖሮ እኔም ሆንኩ ሌላኛው ፀሐፊያችን እንዲህ ዓይነቱን ነገር ትተን ምናልባትም በጋራ ቁጭ ብለን አንዳችን ላንዳችን ፍጥረትንና የፈጣሪያቸውን ኃያልነት እየተሰባበክን እንጨዋወት ነበር፡፡)
ለማንኛውም የዝግመተ ለውጥ አቀንቃኞች ዝም ብለው አልተቀመጡም፡፡ የሳይንስ ቆሌ ሹክ ሳትላቸው አልቀረችም መሰለኝ ..እጅ አንሰጥም እኛ.. በማለት ከሦስት አቅጣጫ ጉዳዩን ይመረምሩ ገቡ፡፡
1. እውነት ፍጥረተ-መለኮታውያን የሚጠቅሱት የህዋ አቧራ
የፍሰት መጠኑ ትክክል ነው?
2. ናሳ ጠፈርተኞችን ወደ ጨረታ ሊልክ በተዘጋጀበት ወቅት
እውነት ጠፈርተኞቹን ብዙ የአቧራ ክምር ያጋጥማቸዋል
ብሎ ሰግቶ ነበር? እና
3. በአሁኑ ጊዜ በጨረቃ ላይ ያለው የአቧራ መጠንስ በምን
ያህል ጊዜ ውስጥ የተጠራቀመ ነው? የሚሉት ናቸው፡፡
ተመራማሪዎች የህዋ አቧራ ዝቅጠትን መጠን ለመለካት የተለያዩ ዘዴዎችን ይጠቀማሉ፡፡ ከነዚህም ውስጥ ጥቂቶቹ:- የባህር ስር ደለል የንጥረ-ነገር ትንተና በዋልታዎች አካባቢ በበረዶ ውስጥ የተጠራቀመ የአቧራ ብናኝ የንጥረ-ነገር ትንተና፣ በሳተላይት፣ በራዳርና በአውሮፕላን በመጠቀም ናሙናዎችን መሰብሰብና ከጨረቃ ገ ላይ የተገኘ ናሙናን መጠቀም ናቸው፡፡ ለምሳሌ ያህል ከ1960 ዓ.ም እስከ 1991 ዓ.ም ድረስ (ዓ.ምህረቶቹ በሙሉ እ.ኤ.አ ናቸው) በተለያዩ ተመራማሪዎች ከተደረጉት 14 የናሙና ጥናቶች ለመረዳት እንደሚቻለው ከፍተኛው የፍሰት መጠን በፍጥረተ-መለኮታውያን ለመከራከሪያነት የቀረበውና በ1960 ዓ.ም በፔተርሰን የተመዘገበው 14 ሚሊዮን ሦስት መቶ ሺ ቶን በዓመት ነው፡፡ ለዚህ ከፍተኛ የመጠን ልዩነት ከሚሰጡት ምክንያቶች ውስጥ ተመራማሪዎቹ የተጠቀሙባቸው የምርምር ዘዴዎችና የምርምር አካባቢው (environment ተዕኖ ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ በተለይ ቀደም ያሉት ጥናቶች ላይ የናሙና አሰባሰብ ከፍተኛ ችግር ነበር፡፡ ቴክኖሎጂ እያደገ በሄደ ቁጥር የናሙና አሰባሰብ ጥራቱም የዚያውኑ ያህል እየተሻሻለ ይሄዳል፡፡ በአሁኑ ጊዜ በሞያው ባለቤቶች ከሞላ ጐደል የተደረሰበት ስምምነት የአንድ መቶ ሺ ቶን በዓመት የብናኝ መጠን ነው፡፡ ይህንን የጋራ መግባባት በመከተል ይመስላል ሄንቤስት በ1991 ዓ.ም የኒው ሳይንቲስት መጽሔት እትም ላይ ..ምንም እንኳን የብናኞቹ መጠን ደቂቅ ቢሆንም በጣም ብዙ ከመሆናቸው የተነሳ መሬት በጠፈር ውስጥ በምታደርገው ጉዞ በዓመት እስከ መቶ ሺ ቶን የሚሆን ብናኝ ከህዋው ውስጥ ይዘንብባታል፡፡.. ሲል የገለፀው፡፡
ጨረቃን በተመለከተ አጠቃላይ የቅርብ ጊዜ መረጃዎች እንደ¸ÃmlKtÜT አማካይ የብናኝ የዝቅጠት መጠን ወደ አስር ሺ ቶን ገደማ በዓመት እንደሆነ ይገመታል፡፡ በዚህም ስሌት መሰረት በ4.6 ቢሊዮን ዓመት ውስጥ በጨረቃ ገ ላይ ሊጠራቀም የሚችለው የብናኝ መጠን ከ9.2 ሳንቲ ሜትር ጥልቀት አይበልጥም፡፡
ሁለተኛው ጥያቄ እውን ናሳ (የአሜሪካ የጠፈር ምርምር ተቋም) ሰው የጫነች መንኮራኩር በ1969 ዓ.ም ጨረቃ ላይ ከማረፏ በፊት መንኮራኩሯንና ጠፈረተኞቹን የሚሰለቅጥ የአቧራ ክምር በጨረቃ ገ ላይ ይኖራል ብሎ ሰግቶ ነበር የሚለው ነው፡፡ ጥቂት ሳይንቲስቶች ይህን ግምት (Speculation) ቢያቀርቡም በአብላጫው ሳይንቲስቶች ግን የሚያሰጋ ነገር አለመኖሩ ተተንብዮ ነበር፡፡ ፍራቻው ከነበራቸው ሰዎች ውስጥ ታዋቂው የሳይንስ ፊክሽን ፀሃፊ የነበረው አሲሞቭ ይገኝበታል፡፡ አሲሞቭ sþÂgR:-
..ጨረቃ ላይ ያለው አቧራ ከህዋ ውስጥ የዘቀጠ ከሆነ በእውንም ጥልቀት ያለው አቧራ ሊከማች እንደሚችል ይሰማኛል፡፡.. በመቀጠልም በድርሰቶቹ ውስጥ በሚታየው ማራኪና ድራማዊ የአገላለ ዘዴው ..መንኮራኩሯ ከተመረጠላት የማረፊያ ስፍራ ስትደርስ የታችኛው አካሏን አስተካክላ በሚያስደንቅ ግርማ ለማረፍ ስትቃረብ ከዚያም መርገጫዎቿ መሬት ሲነኩና ቀስ በቀስ በአቧራው ተውጣ ከእይታ ስትጠፋ በእዝነ-ልቦናዬ ይታየኛል.. ብሏል፡፡ በተጨማሪም ሊት ሌተንና የሮያል ግሪንዊች የስነ-ጠፈር ተመራማሪ የሆኑት ቶማስ ጐልድ ተመሳሳይ ፍራቻቸውን ገልፀዋል፡፡ በተቃራኒው ደግሞ ፍራቻው መሰረተ-ቢስ ነው ከሚሉት ውስጥ ሌላኛው የእንግሊዝ የስነ-ጠፈር ተመራማሪ ሙር እና ዊፕል ይገኙበታል፡፡ በወቅቱ የነበረውን የሃሳብ ልዩነት ሙር እንዲህ ሲል ገልፆታል ..የሃሳብ ልዩነቱ ጉልህ ነው፡፡ በአንደኛው ንፍ በጥልቅ የአቧራ ክምችት የሚያምኑት ጐልድ እና ደጋፊዎቹ ሲገኙ በሌላው ወገን ደግሞ እኔና እኔን የመሳሰሉት የአቧራው ክምችት ከጥቂት ሳንቲ ሜትሮች አይበልጥም ብለን የምናምን ሰዎች እንገኛለን፡፡ ጉዳዩን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመፍታት ያለው አማራጭ ሮኬት በመላክ ማረጋገጥ ነው.. ብሏል፡፡
ሙር እንዳለውም ጠፈረተኞች ከመላካቸው በፊት ሰው አልባ መንኮራኩሮች ቀድመው ተልከው በጨረቃ ገ ላይ ያለ አንዳች የመስጠም አደጋ ማረፍ እንደሚቻል አረጋግጠዋል፡፡ ለዚህም በ1966 ዓ.ም በጨረቃ ላይ ያረፈችው ..ሉና 9.. የራሺያ ሰው አልባ መንኮራኩርና አምስት ተከታታይ የአሜሪካ ሰርቬየር መንኮራኩሮች በቂ ምስክሮች ናቸው፡፡ በተለይም የአሜሪካኖቹ መንኮራኩሮች ማረፊያ እግሮች ከአንድ እና ሁለት ኢንች በላይ አለመስመጣቸውን መንኮራኩሮቹ በላኩት ፎቶግራፍ ማየት መቻሉ፣ ጠፈርተኞቹ በሚላኩ ጊዜ ስጋት እንደ¥ÃU_¥cW በግል አሳይቷል፡፡ ስለዚህ ናሳ ዝምታን መርጧል የሚለው ክስ ቀድሞውን መፍትሔ ባገኘ ነገር ላይ በመሆኑ መሰረት የለውም፡፡
የአሜሪካን ጠፈርተኞችም ለመጀመሪያ ጊዜ በጨረቃ ላይ ሲያርፉ የታየውም ነገር የሰው ልጅ የእውቀት ጥማት አሸናፊነት እንጂ በህይወት አልባ አካል ላይ ሰጥሞ የመቅረት ስሜት አልነበረም፡፡ ኒል አርምስትሮንግ ለመጀመሪያ ጊዜ እግሩ ጨረቃን በረገጠ ጊዜ ሁኔታውን እንዲህ ብሎ ገልፆታል፡፡
..ከመሰላሉ እግሮች አጠገብ ነኝ፡፡ የሉናር ሞጁሉ እግሮች አንድ ወይም ሁለት ኢንች ያህል ወደ ውስጥ ገብተዋል፡፡ የወለሉ ገታ የተፈጨ ብናኝ ቢመስልም በጣም ተጠግተው ሲመለከቱት የላመ ዱቄት ይመስላል . . . ከመሰላሉ ልወርድ ነው፡፡ ይህ ለአንድ ሰው ትንሽ እርምጃ ለሰው ልጆች ግን ረጅም ዝላይ ነው፡፡..
ይህ ሁሉ ከሆነም በኋላ ቢሆን አንዳንድ ፍጥረተ መለኮታውያን እጅ የሰጡ አይመስልም፡፡ እንዲያውም በተገላቢጦሽ ውጤቱ የኛን ትክክለኛነት ያረጋገጠ ነው ይላሉ፡፡ ያንኑ የሙጥኝ ያሉትን የፔተርሰንን ዓመታዊ የዝቅጠት መጠን በመጠቀም አሁን በጨረቃ ላይ የተገኘው የአቧራ መጠን በአስር ሺ ዓመታት ውስጥ ሊጠራቀም የሚችል የብናኝ መጠን ነው በማለት ይከራከራሉ፡፡ በርካታ የተሻሻሉ የጥናት ውጤቶች ባሉበት ሁኔታ ባለቤቱ እንኳን በቅጡ ባልተማመነበት የጥናት ውጤት ላይ የሙጥኝ ማለት ..ካፈርኩ አይመልሰኝ.. ይመስላል፡፡ (በነገራችን ላይ ፔተርሰን ራሱ ከ14 ሚሊዮን ይልቅ 5 ሚሊዮን ቶን ዓመታዊ የብናኝ ዝቅጠት የተሻለ ግምት እንደሆነ አስጠንቅቋል፡፡) ማንም የፍጥረተ መለኮታውያንን ህትመቶች የተመለከተ ሰው ይህንኑ የቆየ ተረት ሲደጋገም እንጂ አዲስ መረጃ ሲወጣ አያያም፡፡ ቁጥር ማጭበርበር ጥበብ ቢሆን የፍጥረተ መለኮታውያንን ያህል የተካነበት የለም፡፡ ምሳሌ ልስጣችሁ፡፡
ሄንሪ ሞሪስ (ባለፈው ሑፌ ስለተዋወቃችሁት ማብራሪያ አያስፈልገውም) ከናሳ የ1976 ዓ.ም እትም ላይ አገኘሁ ብሎ አንድ መረጃ ያወጣል፡፡ እንደ ሞሪስ አገላለ ናሳ ባሳተመው የጥናት ውጤት 200 ሚሊዮን ቶን የአቧራ ብናኝ በዓመት በመሬት ላይ ይዘንባል፡፡ ጉድ ፈላ! ያ ሁሉ የሳይንቲስቶች የጥናት ሪፖርት ሃሰት ነበርና! ምነው ናሳስ ቢሆን በ1969 ዓ.ም እና ከዚያም በፊት ያለ ምንም እንከን መንኮራኩሮቼን ጨረቃ ላይ አሳርፌያለሁ አላለንም?
ይብላኝላቸው ቅጥፈትን ለሚያባዙ እንጂ ዋሾን አሳደው ለማጋለጥ የማይቦዝኑ ብዙ ነቄ ተመራማሪዎች አሉ፡፡ አንዱ ፍራንክ ሎቬል ነው፡፡ እሱ ባደረገው ማጣራት ..1976 ዓ.ም.. ተብሎ የተጠቀሰው ህትመት የ1967 ሆኖ አገኘው! ከሰው ስህተት . . . የተባለው ተረት ትዝ ብሎት ሊያልፈው ፈልጐ ነበር፡፡ ግን ሌላም ስህተት ተከሰተለት፡፡ ወንድማችን ሞሪስ የጠቀሰው የ200 ሚሊዮን ዓመታዊ የብናኝ መጠን የለም፡፡ በአንድ |Creationist Physicist´ እንደ ነገሩ የተሰላ ቁጥር ነው፡፡ ነገሩ ግል ሆነ፡፡ የብዕር ወለምታ ሳይሆን የአእምሮ ወለምታ ነው፡፡ ሌላም ይህን የመሰለ አጋጣሚ አለ፡፡ 1985 ዓ.ም ተብሎ የተጠቀሰ የአንድ የስብሰባ ህትመት 1958 ዓ.ም ሆኖ ተገኝቷል፡፡ ይህ ሁሉ መረጃን ዘመናዊ አስመስሎ ተቀባይነት ለማግኘት ነው፡፡
የዛሬ ሑፌን ከማጠናቀቄ በፊት እውነትን ለሚወዱ አንድ መልካም መሳይ ዜና ላሰማችሁ፡፡ አንዳንድ ቅን የፍጥረተ-ml÷T አቀንቃኞች፣ ይህ የመከራከሪያ መንገድ እንደማያዋጣቸው በመገንዘብ እንዲህ ዓይነት ስህተቶችን ከሑፎቻቸው ለመንቀስ እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ፡፡ አረሙን መንቀል መጀመራቸው ጥሩ ነው፤ የምንፈራላቸው ነገር ቢኖር አረሙን ነቅለው በጨረሱ ጊዜ ማሳቸው ባዶ አፈር ብቻ ሆኖ እንዳይቀር ነው፡፡ ለኛዎቹም የሰሙትን ከነግርድፉ ገልባጮች ልቦና ይስጣቸው፡፡

 

Read 4592 times Last modified on Sunday, 31 July 2011 13:06