Sunday, 31 July 2011 13:24

አባባጃንሆይ

Written by  ከበደ ደበሌ ሮቢ
Rate this item
(0 votes)

በ መጽሐፉ ቀዳሚ ገፆች ላይ ያለውን የአባባ ጃንሆይፎቶግራፍ ለእምዩ እያሳየሁት እኚህ ሰውዬ አባ ረታን ይመስላሉ አልኩት፡፡     አባ ረታ ከእኛ መንደር ከፍ ብሎ የሚኖሩ ገመቹና ረታ የሚባሉ ልጆች ያሏቸው ድሀ ገበሬ ናቸው፡፡ በ1960ዎቹ መጀመሪያ መሆን አለበት፤ ከዛሬ አርባ ዓመት በፊት፤ ሥፍራው ከአዲስ አበባ ወደ ደቡብ ሁለት መቶ ሃያ ኪሎ ሜትር ኦሮሚያ ክልል፣ አርሲ ዞን ጭላሎ አውራጃ ዲገሉና ጢጆ ወረዳ፤ ዲገሉ በመባል የሚታወቅ ቦታ ነው፡፡

ቢበዛ የአምስት ወይ የስድስት ዓመት ህፃን ልጅ ብሆን ነው፤ እምዩ አርጅቷል ከመባል በላይ ጃጅቷል፡፡ ያሳየሁትን ፎቶግራፍ እያየ ሂድ አንተ ከይሲ አለኝ፡፡ ንጉሱን እንዴት ከአንድ ተራ ገበሬ ጋር ታመሳስላለህ ማለቱ እንደሆን ወዲያውኑ ገባኝ፡፡ ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በወቅቱ የኢትዮጵያ ንጉሥ ወይም ንጉሠ ነገሥት ዘ ኢትዮጵያ ናቸው፡፡፡፡  የእኔ ወላጆች ዲገሉ ውስጥ የታወቁ ገበሬዎች ሲሆኑ፤ ሁለት በሮች ባሉት እና ስድስት ቤቶች በሚገኙበት በሠፊው ግቢያችን ውስጥ ቆርቆሮ ቤትና ራዲዮ ያለን የአካባቢው ነዋሪዎች እኛ ብቻ እንደነበርን አስታውሳለሁ፡፡
አሁን ይሄ ሁኔታ ጨርሶ ተለውጧል፤ ለመጀመሪያ ጊዜ ከአርሲ ስወጣ አንድም አርሶ አደር ጫማ አድርጐ አይቼ አላውቅም፤ ከብዙ ዓመታት በኋላ ተመልሼ ወደ አርሲ ስሄድ ጫማ ያላደረገ አንድም ገበሬ አላየሁም፡፡ እምዩ እኛ ግቢ ውስጥ የሚኖር የቤተዘመድ አካል ወይም አባል በመሆኑ ሁላችንም አንተ እንለዋለን ብዬ ልቀጥል፡፡
አባባ ጃንሆይን በደንብ ማወቅ የጀመርኩት ከዲገሉ ባላገር ወጥተን በግምት ሃያ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ እምትገኘው የወረዳው ዋና ከተማ ሳጉሬ ከገባን በኋላ ነው፡፡ በዚያን ጊዜ ፎቶ ቤት እንኳን ያልነበራት ሳጉሬ ዛሬ የተሟላ የኤሌክትሪክና የዲጂታል ቴሌፎን አገልግሎት ያላት፤ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሚገኝባት፤ ሃያ ኪሎ ሜትር ርቀት (አሰላ) ላይ ዩኒቨርሲቲ የተገነባላት፤ ባለፈው ወር አስፋልት የገባላት ትንሽዬ ከተማ ነች፡፡
በህፃንነቴ በጣም ከሚገርሙኝ ነገሮች አንዱ በማናቸውም መጽሐፍ የመጀመሪያ ቀዳሚ ገፆች ላይ የንጉሡ ፎቶግራፍ መኖሩ ነው፡፡ ጥቅምት 23 ቀን እና ..በመላው ኢትዮጵያ አቆመ ምክር ቤት... . . የሚለው መዝሙር የተያያዙ መሆናቸውን የሚቀጥሉት ገለፃዎች ያሳያሉ፡፡
ይሄንን መዝሙር እየዘመርን ኃምሌ 16 ቀንና ጥቅምት 23 ቀን በያመቱ ንጉሱ ለተማሪዎች ከረሜላ ይሰጣሉ ስለሚባል፣ የሳጉሬ ልጆች ተሰልፈን አባባ ጃንሆይን እንጠብቃለን፡፡ ኃምሌ አሥራ ስድስት ከስመ ጥሩው ኢትዮጵያዊ ዲፕሎማትና የጦር መሪ ከራስ መኮንን ጉግሳ ሀረር ውስጥ ኤጀርሳ ጐሮ የተወለዱበት ቀን ነው፤ ጥቅምት 23 ደግሞ የአገር አመራር በትረ ሥልጣን የያዙበት፡፡
ያለፈው ቅዳሜ ሀምሌ 16 ቀን 2003 ዓ.ም የግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ የልደት ቀን ሆኖ ውሎአል፡፡ በህፃንነት አባባ ጃንሆይ የምንላቸው የቀድሞው የኢትዮጵያ ንጉሥ፤ መስከረም 2 ቀን 1967 ዓ.ም በደርግ ከሥልጣን ከተወገዱ በኋላ አፄ ተብለዋል፡፡ ኃይለ ሥላሴ፡- yእግዚአብሔር ኃይል ማለት ነው፡፡ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በአገር አመራር የሥልጣን ዘመናቸው አርባ ዓመት ወይም ከአርባ ዓመት በላይ አገር ከገዙ ወይ ከመሩ ጥቂት የዓለማችን መሪዎች አንዱ ናቸው፤ በሌላ አነጋገር ለረጅም ጊዜ በሥልጣን ላይ ከቆዩ የአገራት መሪዎች አንዱ፡፡ አፄ ቴዎድሮስ አሥራ ሁለት ዓመት ነው በሥልጣን ላይ የቆዩት፤ ከ1948 እስከ 1960 ዓ.ም፡፡ ዮሐንስ ደግሞ ከዚያ በታች ለሆነ ጊዜ፤ የጐጃሙ ተክለ ጊዮርጊስ ሶስት ዓመት ከመንፈቅ፤ ምኒልክ በሥልጣን ላይ የቆዩበት ጊዜ ደግሞ ከሃያ ዓመት አይበልጥም፤ ያውም እርሳቸው በህይወት ሳይኖሩ በስማቸው አገር የተዳደረበት ሰባት ዓመት ተጨምሮ፡፡ ንግሥት ዘውዲቱና ልጅ ኢያሱ በፊናቸው በአገር አመራር ሥልጣን ላይ የቆዩት በጣም ለጥቂት ጊዜ ነው፡፡
በኢትዮጵያ የነገሥታት ታሪክ ውስጥ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ የመጨረሻው ንጉሥ ናቸው፡፡ በአገራችን የሥርወ መንግሥታት (dynasties)  ታሪክ ኃይለሥላሴ ንጉሥ የሆኑት፤ ከአክሱም ሥርወ መንግሥት Axum dynasty ሠልሦ እና ከዛጉዌ ሥርወ መንግሥት (Zaguwie Dynasty) ቀጥሎ ካለው ሞአ አንበሳ ዘእምነገደ ይሁዳ ነው፡፡ ሥዩመ እግዚአብሔር እዚህ ሊታከል ይችላል፡፡
***
ዓባይን ለመገደብ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሞከረው በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመን ነው፡፡ ሁለት ጊዜ ነው የመገደብ ሙከራው የተደረገው፡- አንዴ በእንግሊዞች፤ አንዴ በአሜሪካኖች፡፡ ይሁንና ሁለቱም ሙከራዎች አልሠመሩም፡፡ አስፈላጊው ጥናት ተደርጐና እቅድ ተነድፎ ካለቀ በኋላ የግብራዊ ክንውኑ ጅማሬ የመከነው በንጉሠ ነገሥቱ የውስጥ የፖለቲካ ችግር ምክንያት መሆኑን ፕሮፌሰር ጆን ሃዛዋይ ስፔንሰር Ethiopia At Bay (ጥርስ የገባች አገር) ላይ ጽፎልናል፡፡ በእርግጥ ከግድቡ በፊት መሠራት የነበረባቸው የፖለቲካ ሥራዎች ነበሩ፡፡ ስፔንሰር የፃፈልን ኢትዮጵያ ውስጥ ሊሠራ ታቅዶ ያልሰመረው ግንባታ ሱዳንና ግብ ውስጥ ስኬታማ መሆኑን ጭምር ነው፡፡ መልካቸው የሚያምረውንና ረጋ ያለ ንግግራቸው ቁም ነገር የመላበትን ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴን ስፔንሰር የሚገልጻቸው፡- ሁለት ተቃራኒ ባህሪ (ድፍረትና ፍርሀት ጭካኔና ርኅራሄ ግልጽነትና ቁጥብነት ቁጣና እርጋታ. . .) የሚታይባቸው ብሎ ነው፡፡
ነጭ ኢትዮጵያዊ  ከምላቸው የኢትዮጵያ የልብ ወዳጅ ፈረንጆች መሀከል ነው ስፔንሰር፡፡ አርባ ዓመት ሙሉ የንጉሱ የህግ አማካሪ ሆኖ ከአንድ ትውልድ ዕድሜ በላይ ከቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ጋር ዕለት ዕለት እየተገናኘ አብሮ ኖሮአል፡፡ ትውልዱ አሜካዊ ሲሆን የህግ ዶክትሬት ዲግሪውን የሠራው ፈረንሳይ አገር ነው፤ ከኢትዮጵያ ጋር እንዲሰራ የታጨውም በፈረንሳዮች፡፡ ፈረንሳይ የአያለ ዘመናት የኢትዮጵያ የልብ ወዳጅ ነች፡፡ በኢጣሊያ ወረራ ወቅት ማይጨው ድረስ ከእኛ ጋር የዘመተው ፕሮፌሰር ጆን ሃዛዋይ ስፔንሰር፤ አሁን በትውልድ አገሩ አሜሪካ አዛውንት ምሁር ሆኖ ይኖራል፡፡ በዛሬ ዘመን ስፔንሰር ወደ ኢትዮጵያ ቢመጣ በተሠራው ሥራ ከመደነቅ አልፎ በመገረም ይደነግጣል ብዬ አስባለሁ፡፡
ፋሺስት ኢጣሊያ ፋቼታ ኔራ (ያቺ ጠይም ቆንጆ ልጅ) የሚለውን የጣሊያንኛ መዝሙር እየዘመሩ በመጡ ወታደሮች ኢትዮጵያን ሲወርሩ ከፍተኛው ውጊያ የተደረገው በማይጨው ጦር ግንባር ነው፡፡ በዚህ ወቅት የአገሪቱ ንጉሥ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ጦር አዛዥ በመሆን ሠራዊታቸውን አሰድረው ወታደራዊ አመራር ሰጥተዋል፡፡ ይሁንና በዚህ የጦር ግንባር ኢትዮጵያ ድል አልቀናትም፡፡ እንደ የብዙ ታሪክ ተመራማሪዎችና የውትድርና ሳይንስ ኤክስፐርቶች ትንታኔ ኢትዮጵያ ድል ያልቀናት በሁለት ምክንያቶች ነው፡፡
ሰራዊቱ በሊግ ኦፍ ኔሽንስ የተከለከለ የመርዝ ጋዝ በጫኑ ተዋጊ ጀቶች በመደብደቡና በዚህም የትጥቅ ኃይል መዛባት በመከሰቱ፤ እና ከውስጥ የፖለቲካ ችግሮች ጋር በተያያዘ በኢትዮጵያ ሠራዊት ውስጥ የወታደራዊ አመራር እንከን በመኖሩ፡፡ የአምስት ዓመታት የነፃነት ተጋድሎ ከተደረገ በኋላ በ1933 ዓ.ም የፋሽስት ጦር በጀግኖች የኢትዮጵያ አርበኞች ተረግጦ ወጥቷል፡፡ በዚህም ከሰባት መቶ ሺህ ዜጐች መስዋዕትነትና ቁጥር ሥፍር ከሌለው ሀብትና ንብረት ውድመት በኋላ በመጨረሻ ኢትዮጵያ አሸንፋለች፡፡
bኢትዮጵያውያን የነፃነት ተጋድሎ ታሪክ፣ አፄ ቴዎድሮስ ከእንግሊዞች ጋር መቅደላ ላይ ሲዋጋ ራሱን ሰውቷል (ሽጉጡን ጠጥቷል)፤ አፄ ዮሐንስ መተማ ላይ ከደርቡሽ ጋር ሲዋጉ ተሰውተዋል፡፡ አፄ ኃይለሥላሴ ከማይጨው ጦርነት በኋላ ወታደራዊና ዲፕሎማሲያዊ ድጋፍ ለማግኘትና የነፃነት ተጋድሎውን ለማጠናከር በሚል ከአገር ለመሰደድ ተገድደዋል፡፡ በጅቡቲ አድርገው ከአገር ለመውጣት በባቡር ሲጓዙ፣ በወቅቱ የሀረር አገረ ገዢ የነበሩት ፊታውራሪ ተክለ ሃዋርያት ተክለማርያም ቴዎድሮስና ዮሐንሰ በጦር ሜዳ በተሰውበት ምድር በሚል ንጉሱ ከአገር እንዳይወጡ በማከላከላቸው፣ በስደት ጅቡቲ ለመኖርና ማዳጋስካር ለአሥራ አንድ ዓመታት በገበሬነት ለማሳለፍ ተገደዋል፡፡ አራት ዓመት በሩሲያ ወታደራዊ ሳይንስ የተማሩትን ፊታውራሪ ተክለ ሀዋሪያት ተክለ ማርያምን በመጨረሻ ከማዳጋስካር ገበሬነት ነፃ ያወጧቸው ልጃቸው አምባሳደር ግርማቸው ተክለ ሃዋርያት መሆናቸውን ፕሮፌሰር ሞልቨር የተባለ አውሮጳዊ ምሁር |Black Lions´ በተሰኘ መጽሐፉ ጽፎአል፡፡
ሞልቨር አክሎ እንደፃፈው፡-
አፄ ኃይለ ሥላሴ ከአገር ከወጡ በኋላ፤ ኢትዮጵያ ዋና ከተማዋን ከአዲስ አበባ ወደ ኢሊባቦር (ኢሉ አባቦራ) ጐሬ ከተማ አዛውራለች እንጂ አልተሸነፈችም በሚል ለሀረር ገበሬዎች ሃምሳ ጋሻ መሬት የሰጡት ራስ እምሩ፤ ጐሬ ላይ አዲስ የመንግስት መዋቅር አቋቁመዋል፤ ለጥቂት ጊዜም ቢሆን፡፡
***
በልጅነት ስማቸው ተፈሪ መኮንን በንጉሥ ስማቸው ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ በፈረስ ስማቸው አባ ጠቅል፤ የአፍሪቃ አንድነት ድርጅትን በመመስረት በተጫወቱት ሚና ለአፍሪቃና ለህዝቦቿ ታላቅ መሪ ናቸው፡፡ ከታዋቂዎቹ የአፍሪቃ መሪዎች ከጋናው ንዋሚ ንኩሩማህ፣ ከታንዛኒያው ጁሊየስ ኔሬሬ፣ ከኬንያው ጆሞ ኬንያታ፣ ከዛምቢያው ኬኔት ካውንዳ እና ከሌሎች አፍሪቃዊ መራሄ መንግሥታት ጋር የአፍሪቃ መንግስታትን ኅብረት በመፍጠር ጉልህ ሚና ተጫውተዋል፡፡ እንዲሁም ጥቁር አፍሪቃና አረብ አፍሪቃ ከአውሮጳ ቅኝ ገዢዎች ነፃ ለመውጣት የነፃነት ተጋድሎ ሲያደርጉ የተቻላቸውን ያህል ወታደራዊና ፖለቲካዊ ድጋፍ በማድረግ የራሳቸውንና የኢትዮጵያን ሥም በአፍሪቃ ህዝቦችና መንግሥታት ዘንድ አስከብረዋል፡፡
ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ በርካታ የውስጥ የፖለቲካ ችግሮች እንደነበሩባቸው መካድ አይቻልም፡፡ ይሁንና ይሄም ሆኖ በአገሪቱ አያሌ የሥልጣኔ ተቋማትን ተክለዋል፡፡ በውስጥ የፖለቲካ ችግሮች ምክንያት በ1953 ዓ.ም በእነጄኔራል መንግሥቱ ንዋይ ገርማሜ ንዋይና ጽጌ ዲቡ ያልተሳካ መፈንቅለ መንግሥት በተደረገባቸው ጊዜ ከመፈንቅለ መንግሥቱ በኋላ፤ ደራሲና ዲፕሎማት የአርበኞች መሪና ትልቅ የመንግሥት ባለሥልጣን ለህዝቡ ጥቅም የተለያዩ አዳዲስ አስተሳሰቦች ባለቤት የሆኑት የክብር ዶክተር ሀዲስ ዓለማየሁ፤ ኢትዮጵያ የአንድ ብሄርና የአንድ ሃይማኖት አገር ሳትሆን የበርካታ ብሔር ብሔረሰባትና የብዙ ሃይማኖቶችና እምነቶች አገር ነች የሚል ደብዳቤ lግርማዊn¬cW ጽፈውላቸዋል፡፡
እነ መንግሥቱ ንዋይ በመፈንቅለ መንግሥቱ ለህዝቡ ያደረጉት ጥሪ ተነስ. . . የሚል ነው፡- ታሪክ ያለህ ሰው ተነሳ ሰውነትህን አትርሳ፤ ባርነትህን ደምስሰው ነፃነትህን አድሰው ክብርህ መብትህ ሊጠበቅ ነው፤ ደስታ ህይወትን ልታገኝ ነው፡፡
ይሁንና ሀዲስ በጻፉላቸው ደብዳቤም ሆነ በመፈንቅለ መንግሥቱ ሙከራ ድንጋጤ ተነሳስተው፡-
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲN የከፈቱት፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድን ያቋቋሙትና ሌሎች በርካታ ኢትዮጵያን ከአፍሪቃ ቀደምት የሚያደርጉ ተግባራት ያከናወኑት ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ የወሠዱት መሠረታዊ እርምጃ ወይም ያመጡት ለውጥ የለም፡፡ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ኢትዮጵያ በመላው ዓለም ፊት ያላትን እውቅናና ክብር የጨመሩም መሪ ናቸው፡፡ የኢትዮጵያ ሠራዊት በኮንጐ እና በኮሪያ ሁለት ዓለም አቀፍ ግዳጆች የተወጣው በንጉሱ ዘመን ነው፡፡ አንዳንድ ሩቅ አገሮች ኢትዮጵያን የሚያውቁትም ሆነ የሚያከብሩት በአበበ ቢቂላና በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዝና መነሻነት ነው፡፡
ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ በአገሪቱ በስማቸው የሽልማት ድርጅት ማቋቋማቸውና በተለያዩ ሙያዎች ችሎታዎችና ተሰጥኦዎች አኩሪ ተግባር ለፈፀሙ ኢትዮጵያውያን መሸለማቸው የመሪነት በጐ ግብር ነው፡፡ እነ ባለ ቅኔ ሎሬት ፀጋዬ ገብረ መድህን ቀዌሳ፣ የክብር ዶክተር የተሰጣቸው ደራሲ ከበደ ሚካኤል የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴን ሽልማት ከተሸለሙት ኢትዮጵያውያን ታላላቆች መሃከል ይወሳሉ፡፡
ከዚህ በተጨማሪ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በራስ ተፈሪያንና በጃማይካውያን ዘንድ የአምልኮ ያህል ታላቅ ክብርና ሥፍራ ያላቸው ኢትዮጵያዊ ንጉሥ ናቸው፡፡
ራስ ተፈሪያንና ጃማይካውያን ኃይለ ሥላሴን የሚያዩዋቸው ከአባታቸውና ከመሪያቸው በላይ አድርገው ነው፡፡ ይሄ መነሻ ሆኖ ኢትዮጵያን እንደ አገራቸው የሚወዱትን ጃማይካውያን ከአገራቸው አምጥተው ሻሸመኔ አካባቢ ያሰፈሩ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ናቸው፡፡
በወጣትነታቸው ራስ ተፈሪ ይባሉ የነበሩት ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ በጃማይካውያንና በራስ ተፈሪያን ዘንድ ..ጃህ ራስ ተፈሪ ነው.. የሚባሉት፡፡
ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ እጅግ የተከበሩና በአህጉር አቀፍና በዓለም አቀፍ ሳይቀር በሥመ ጥርነት የታወቁ ንጉሥ ናቸው፡፡ ይሁን እንጂ እንደ ንጉሥነት ዘመናቸው ርዝማኔ፤ የኢትዮጵያን ትክክለኛና እውነተኛ ሁለንተናዊ ተጨባጭ ሁኔታ በመረዳት፣ ከነፀረ ኢትዮጵያዊ ግንዛቤ በመነጨ ሊሠሯቸው የሚችሉና የሚገቡ መሠረታዊ ተግባራት ነበሩ፤ ይህንን ሊያደርግ የሚችል በኢትዮጵያ ፖለቲካዊና ሁለንተናዊ ሁኔታ አእምሮው የበራለት Enlightened የሆነ መሪ ነው፡፡ ንጉሥ ከሥልጣን ከወረደ ፀሐይ አትጠልቅም በሚባልበት አገር ላይ አንድ ሰው የመቶ ጋሻ መሬት ባለቤት ሆኖ መቶ ሺህ ኢትዮጵያውያን ኩርማን መሬት በሌላቸው ሁኔታ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ቢያንስ ከነጄኔራል መንግሥቱ ንዋይ መፈንቅለ መንግሥት በኋላ መንቃት ነበረባቸው፡፡ እንዲህ መሆን በህዝቡ መብቶች ላይ የተፈፀሙ ስህተቶች እንዳይፈፀሙ ማድረግ ብቻ ሳይሆን፤ የኖሩ ፖለቲካዊ ችግሮች ሠላማዊና ዲሞክራሲያዊ መፍትሔ አግኝተው የአገሪቱ የዕድገትና የልማት ብርሃናዊ ጐዳና እንዲከፈት ያደርጋል፡፡ አባባ ጃንሆይ ይሄንን ቢያደርጉ ኋላ ላይ እኛ ለመሥራት የተገደድናቸውን አገራዊ ተግባራት (Assignment) ለመሥራት ባልተገደድን፤ በዚህ ፋንታ ከዚህ በበለጠ ፍጥነትና ልቀት በገሰገስን ነበር፡፡
ልጅ እያሱ በጥቂት ጊዜ የሥልጣን ዘመናቸው ከህዝቡ አእምሮና ልብ ላይ የነቀሏቸው (ያስወገዷቸው) የኖሩ ሠንኮፎች አሉ፡፡ በሰው ልጆች ታሪክ ውስጥ ታላላቅ ከምላቸው የዓለማችን መሪዎች ጐራ የምመድበው አፄ ቴዎድሮስ ከኢትዮጵያ ሁለንተና ላይ የነቃቀላቸው ፖለቲካዊ ኑባሬዎች አሉ፡፡
የመሳፍንት ዘመንን ማስወገድ፤ ባርነትና ባሪያ ፈንጋይነትን ማገድ፤ በብሔር ይሁን በሃይማኖት በፆታ ይሁን በማኅበረሰብ ክፍል ምክንያት የሚደረግ አድልኦና የሚፈፀም ግፍና በደልን ማክተም፤ ከአክሱም ሥርወመንግሥት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በደሞዝ የሚተዳደር መደበኛ ሠራዊት ማቋቋም እና የመሳሰሉት፡፡
አፄ ዮሐንስን፣ አፄ ምኒልክን፣ ራስ መሸሻ ቴዎድሮስን ያስተማዥው ቴዎድሮስ ነው፡፡ ተማሪዎቹ ሲመረቁ ዮሐንስ ባላንባራስ፤ ምኒልክ እና መሸሻ ደጃዝማች ሆነው ተሾሙ፡፡
ሠላምዎ YB²! bFQR!
Soli. Deo.Gloria!

 

Read 6163 times Last modified on Friday, 05 August 2011 14:05