Sunday, 31 July 2011 13:47

በአእምሮ የሚታዘዝ ብስክሌት

Written by  ዮናስ ብርሐኔ
Rate this item
(0 votes)

ከአዕምሯችን በሚላክለት ትእዛዝ መሠረት የሚንቀሳቀስ በዓለማችን የመጀመሪያው ብስክሌት ተሠርቶ ለእይታ መቅረቡን ዴሊ ሜል አስታወቀ፡፡ የቶዮታ ፕራየስ ፕሮጀክት የፈጠራ ውጤት የሆነው “parlee PXP” ብስክሌት ከአዕምሮ የሚተላለፍለትን መልእክት ተቀብሎ የሚሠራ ማርሽ ያለው ሲሆን አሽከርካሪው እና ብስክሌቱ እየተናበቡ በተቀነባበረ ሁኔታ እንዲሠሩ የሚያደርጋቸው ደግሞ አሽከርካሪዎቹ የሚያደርጉት ልዩ ሄልሜት ነው፡፡

ሄልሜቱ የአዕምሮ ሞገድን ወይም በአዕምሮ ውስጥ የሚፈጠረውን ’ እንቅስቃሴ በመከተል የሚቀነባበረውን መረጃ ተቀብሎ መልእክቱን በብስክሌቱ መቀመጫ አካባቢ ለሚገኘው ኤ ማርሽ ያስተላልፋል፡፡ መልእክቱን የሚያስተላልፈው ያለ መገናኛ ገመድ በአየር ሲሆን ለዚህ ሁሉ ነገር ወሳኟ ደግሞ የአዕምሮ ሞገድን ተቀብላ የምታነበዋ ከኋላ በኩል የምትደረገው አነስተኛ መጠን ያላት መሳሪያ ነች፡፡
አድናቆት የተቸረው አዲሱ ብስክሌት በውስጣችን እያሰብን በአዕምሯችን የምንለው ነገር ተከትሎ ለመሥራት ከአዕምሮ ማንበቢያው ጋር በቁርኝት የሚሠራ የሶፍትዌር ፕሮግራም ያለ ሲሆን በአጠቃላይ በአሽከርካሪው አዕምሮ እና በብስክሌቷ መካከል የሚኖረው መናበብ እንዲፈጠር የሚያደርገውም እነዚህን ነገሮች የሚያስተሳስረው እጅግ የተራቀቀው ሲስተም ነው፡፡ በዚህም ብስክሌቱን የሚነዳ ሰው ለምሳሌ ማርሽ ለመጨመር ሲፈልግ ከሱ የሚጠበቅበት ያንን የፈለገውን ነገር በአዕምሮው እያሰላሰለ ማለት ብቻ ነው፡፡ ከዚያም በጭንቅላቱ ያጠለቀው ሄልሜት የአዕምሮውን |nþWé-ኤl¤KT¶µL´ እንቅስቃሴ ተቀብሎ ያንን ለምታነበው አነስተኛ መሳሪያ ካስተላለፈና በልዩ ሁኔታ በተበጀው ሶፍትዌር አማካኝነት እንዲተረጐም ከተደረገ በኋላ (መቀነስም ሆነ መጨመር) ማርሹ የተባለውን ነገር ይፈጽማል ማለት ነው፡፡አሽከርካሪዎች ይህን አስደናቂ ብስክሌት በአዕምሯቸው እንቅስቃሴ ብቻ እንደፈለጉት ለማዘዝ ትንሽ ሥልጠና እንደ¸ÃSfLUcW የተጠቆመ ሲሆን ከሲስተሙ ጋር በደንብ ከተዋሃዱ በኋላ ግን የብስክሌቱን ፍጥነት ለመጨመር ወይም ለመቀነስ ሲያስቡ መልእክታቸውን በቀላሉ ማስተላለፍ እንደሚችሉ ነው የተገለው፡፡ የአዕምሮን እንቅስቃሴ ተከትሎ የሚሠራው ይህ ብስክሌት አሁን ባለበት የሙከራ ደረጃ ማርሹን በአዕምሮ ትእዛዝ መቀያየር እንደተቻለ የጠቀሰው የዜናው ምንጭ፤ ብስክሌቱ በስፋት ተመርቶ ለገበያ ይቀርባል ተብሎ እንደሚጠበቅ አመልክቷል፡፡

 

Read 2371 times Last modified on Sunday, 31 July 2011 13:51