Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Sunday, 31 July 2011 14:45

የኤሚ ዋይን ሃውስ አሟሟት ግራ አጋብቷል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ባለፈው ሳምንት እሁድ ለንደን በሚገኝ መኖሪያ ቤቷ ሞታ የተገኘችው እንግሊዛዊቷ ድምፃዊት ኤሚ ዋይን ሃውስ አሟሟት ግራ ማጋባቱን የተለያዩ ዘገባዎች አመለከቱ፡፡ አርቲስቷ በህይወት ዘመኗ ያፈራቸውን 10 ሚሊዮን ዶላር ለቤተሰቦች እንዲከፋፈል ተናዛለች፡፡

በኮኬይን ዕና በመጠጥ ሱስ ከፍተኛ ችግር ላይ የነበረችው ኤሚ ዋይን ሃውስ፤ በ27 ዓመቷ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየችው ከዚሁ የጤና ችግር ጋር በተያያዘ መሆኑን የተለያዩ ዘገባዎች ቢገልም የአሟሟቷ ዋና መንስኤ ምን እንደሆነ ከ ሦስት ሳምንት በኋላ ይፋ በሚሆን የህክምና ምርመራ ይረጋገጣል ተብሏል፡፡ በኤሚ ዋይን ሃውስ ሞት ዩ2፣ ሌዲ ጋጋ፣ ኒኪማንጂ፣ ሪሃና የሀዘን መግለጫ በማውጣት ቀዳሚ ሆነዋል፡፡የ27 ዓመቷ ኤሚ ዋይን ሃውስ በሶል፣ አር ኤንድ ቢና ጃዝ የሙዚቃ ስልቶች በመላው ዓለም ከፍተኛ ስኬት የተቀዳጀች እንግሊዛዊት አቀንቃኝ የነበረች ስትሆን በ2003 እ.ኤ.አ. እና በ2006 በሠራቸው ሁለት አልበሞች በተለያዩ የሽልማት ስነ ሥርዓቶች ከ50 ጊዜ በላይ ታጭታ 38 ጊዜ ያሸነፈች ሲሆን 4 የግራሚ ሽልማቶች ናቸው፡፡ የኤሚ ዋይን ሃውስ 2 አልበሞች  በዓለም ዙሪያ ከ23 ሚሊዮን ቅጂ በላይ ተቸብችበዋል፡፡

Read 5854 times