በሐምሌ 23/2003 ዓ.ም. ዕትም ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ ግቢ ውስጥ ምንነታቸው ያልታወቁ ሳጥኖች በቁፋሮ ተገኙ በሚል የወጣውን ዘገባ ፋብሪካው አስተባበለ፡፡
ፋብሪካው በላከው የማስተባበያ ጽሑፍ፤ ለፋብሪካ ማስፋፊያ ሥራ አጥር ግቢው ውስጥ የነበረን አሮጌ ቤት የማፍረስ ሥራ ከመካሄዱ ውጪ የግንባታ ሥራ እያከናወነ አለመሆኑን ገልጾ ቤቱ ፈርሶ ፍርስራሹ ተጠራርጐ እስኪወገድ ድረስ የተገኙ ሳጥኖች የሉም ብሏል፡፡
ባለፈው አርብ ሐምሌ 22/2003 ዓ.ም. የጋዜጣው ሪፖርተርና ፎቶግራፈር በደረሳቸው ጥቆማ መሠረት ወደፋብሪካው በመሄድ ግቢ ውስጥ ከገቡ በኋላ በፐርሶኔል ኃላፊው እንዲወጡ በመደረጋቸው ከግቢው ውጪ በመሆን በቁፋሮው ተገኙ የተባሉትን ሳጥኖች በምስሉ እንደሚታየው በካሜራ ቀርውታል፡፡
Published in
ዜና