Saturday, 06 August 2011 14:41

የኢ-አማኒው ኑዛዜ

Written by  ደረጀ ፀጋዬ
Rate this item
(2 votes)
  • Confession of an agnostic atheist

ስነ-ፍጥረትን፣ ታሪክንና ግብረ-ገብነትን በአጠቃላይ ምልዓተ-አለምን በተመለከተ ሳይንስም ሆነ ሀይማኖት መለካት ያለባቸው በእኩል ሚዛን ላይ ነው፡፡ አለበለዚያ አንዱን ማብጠልጠል ሌላውን ያለማጣሪያ የዋንጫ ባለቤት ማድረግ ሚዛናዊነትን ማጓደል (Double Standard መጠቀም) ይሆናል፡፡ በዚህ መስፈርት ነው የአንዱ ልዕልና  የሌላው ኮስማናነት መለየት ያለበት፡፡ የአንዱን ገመና በጓዳ ሸሽጐ የሌላውን በአደባባይ ማብጠልጠል ግፋ ቢል ተብጠልጣዩን ያዋርድ እንደሆነ እንጂ የተሸሸገውን አያነግስም፡፡

ለሐምሌዘጠኙየመጀመሪያጽሑፉዶ/ሩበሐምሌ16 ዕትም የመሰላቸውን መልስ ሰጥተውኛል፡፡
በለመድኩት የአርፋጅ ባህሪዬ ብዘገይም አልቀረሁምና ምላሼ ይሄውና፡፡ ..በሳይንሱም ቢሆን አትደርስብኝም.. በሚል ስሜት ይመስላል ለመረጃነት በተጠቀምኩት ሃሳብ ላይ አከል አድርገው አብራርተዋል፡፡

በምንም ስሜት ያቅርቡት ለአንባብያን የማንበብ መነቃቃት አወንታዊ አስተዋጽኦ ስለሚያበረክት የሚደገፍ ነው፡፡ ሆኖም የቀረው ጽሑፋቸው ተራ ስድብና የተንሻፈፉ የሳይንስ እሳቤዎች ናቸው፡፡ በማጠቃለያቸው ላይ ስብከት መሳይ ነገርም አክለዋል፡፡ ከተነሳሁበት አላማ አንፃር አንዳንዴ ብዕሬን ካላዳለጣት በቀረ ግንብ ተከልለው ድንጋይ እንደሚወራወሩ ህፃናት የስድድብ አዙሪት ውስጥ ለመግባት አልከጅልም፡፡
በጽሑፍዎ ውስጥ ያረፈድኩ ለቀስተኛ እንደሆንኩ ነግረውኛል፡፡ በጊዜ እጦትም ይሁን በቦታ ርቀት ለቅሶ በልቶ ከመቅረት በመንፈቅም ይሁን በዓመት መድረሱ ወግና ባህላችን በመሆኑ እባክዎ ..በብዕር ኩርኩምዎ.. አያስፈራሩኝ፡፡ እስከዛሬ ድረስ የፃፏቸውን ጽሑፎች ባለማንበቤም ተኮንኛለሁ፡፡ ነገሩ ..አውድማ ሙሉ እብቅ ቢያበጥሩት ልብ ውልቅ.. ካልሆነ በቀር እንደተናገርኩት ጽሑፉችዎ የተለመዱት የፍጥረተ መለኮታውያን ጽሑፎች ግልባጭ በመሆናቸው እንደ ዳዊት ልደግማቸው አይጠበቅብኝም፡፡ ከኢ - አማንያንም ሆነ ሳይንስን የሙጥኝ ካሉ አማንያን ጋር ምንም የሚያገናኝዎ ነገር እንደሌለ መግለጽዎት ይታወቃል፡፡ ከኢ - አማንያን ጋር እንዳልሆኑ እማኝ መቁጠር አያሻዎትም፡፡ ነገር ግን ሳይንስን የሙጥኝ ካሉት አማንያን ጋር ካልሆኑ ያን ሁሉ ..የሳይንስ ግድፈት.. እያሉ ሲጽፉ የከረሙትን ጽሑፍ ከየት አመጡት? ያለ ምንም ምንጭ ከአእምሮዎ አመንጭተው ከሆነ ድንቅ መገጣጠም ነው፡፡ አለበለዚያ በመገለጥ (Revelation) መሆን አለበት፡፡
በመጀመሪያ ጽሑፌ እንደገለጽኩት አነሳሴ በዶ/ሩ በኩል ሲቀርቡ የነበሩትን የተሳሳቱና የአንድ ወገን ዘገባዎች ለማስተባበል ነበር፡፡ ቢሆንም የዶ/ሩ ጦረኛ ብዕር እስካሁን በተቆጣጠረችው ግዛት ብቻ ሳትወሰን አዲስ የግጭት ግንባር እንደምትከፍት አልጠፋኝም፡፡ በመሆኑም ለዛሬ ከመጀመሪያ አላማዬ ጊዜያዊ የታክቲክ ለውጥ በማድረግ ትኩረቴን በሐምሌ 16ቱ ምላሻቸው፣ ውስጥ የዋህ መሳይ ግን አሳሳች ..እውነታዎችና እሳቤዎች.. ላይ አደርጋለሁ፡፡ ሃሳቤን ለማደራጀት ይጠቅመኝ ዘንድ ዶ/ሩ በሰጡት ምላሽ ውስጥ ያሰፈሩትን ..እውነታዎችና እሳቤዎች.. እንመልከት
1. ሳይንስ መገልገያ ብቻ ነው፡፡
2. ሳይንስ በስህተቶች የተሞላ ነው፡፡
3. ሳይንስ ስለ ፍጥረት የተመታ መላ - ምት እንጂ ግኝቶች የሏትም ስለዚህ ጉዳይ በተናገረች ጊዜ ሳይንስ መሆኗ ቀርቶ ሃይማኖት ትሆናለች...
ውይይትን/ክርክርን የጨረባ ተዝካር ከሚያደርጉት ነገሮች አንዱ ተወያዮች/ተከራካሪዎች በጋራ ለሚጠቀሟቸው ቃላት የተለያየ ፍቺ (definition) መስጠት ነው፡፡ እንደ ዶ/ሩ በጠባብ መንገድ በመተርጐም እውነታዎቹን ሳይንስ ሳይሆኑ ተራ ወሬ በማስመሰል ያለ ድካም ችግሩን ለመሻገር ታስቦበት የተመታ መላ ነው፡፡
የሳይንስ ጥናት ተፈጥሮን ከመመልከትና ከመመርመር ይጀምራል፡፡ ከዚህም በመነሳት ለሚያጠናው ውጫዊ ነባራዊ አለም አእምሯዊ ምስለ ተምሳሌት (Model) ያቀናብራል ወይም ያበጃል፡፡ ይህንንም ምስለ ተምሳሌት በአመክንዮ፣ በቁሳዊና በሂሳብ ዘዴዎች ማቅረብ ይቻላል፡፡ በጉዳዩ ዙሪያ ሁኔታዎች በፈቀዱትና በተቻለ መጠን መረጃዎች ከተሰበሰቡ በኋላ የመረጃዎቹን ውስጣዊ ትስስርና አሰራር የሚገልጽ ሃሳብ (hypothesis) ይበጃል፡፡ አዲሱ ሃሳብ በተቻለ መጠን ከዚህ ቀደም ከተረጋገጡና ተቀባይነት ካላቸው ሃሳቦች ጋር ቢጣጣም ይመረጣል፡፡ ዋናው ነገር ግን በዚህ መንገድ የተቀናበረው ሃሳብ ተጨማሪ ሳይንሳዊ ትንበያዎችን (Predictions) ማፍለቅ መቻሉና በሙከራ መረጋገጡ ነው፡፡ ይህን የማያሟላ ሃሳብ ከተቻለ ይሻሻላል ካልሆነም ይተዋል፡፡ ይህንን ፈተና ያለፈ ሃሳብ ወደ ሳይንሳዊ መላ ምት (Scientific theory) ደረጃ ከፍ ይላል፡፡ ሳይንሳዊ መላ ምት እንደው በደመነፍስ ተነስተው የሚጽፉት ሃተታ መናፍስት ሳይሆን በጥንቃቄ የተቀመረ ውስጣዊ ትስስር እና ስምምነት (Self consistent) ይዘት ያለው የሚጠናውን ነባራዊ አለም በሁለንተናዊነት ለመግለጽ የምንጠቀምበት ሰፊ ሃሳብ ነው፡፡
ነገር ግን አንዳንድ ሰዎች በማወቅም ይሁን ባለማወቅ የቡና ላይ የባልቴቶች ወሬ ሲያስመስሉት ይታያል፡፡
አንድ የአይዛክ አሲሞቭ ጥቅስ ትዝ አለኝ፡፡ እንዲህ ይላል ..ፍጥረተ - መለኮታውያን እንደ¸ÃSmSlùT መላ - ምት (theory) ሌቱን ሙሉ መጠጥ የጠጣ ሰው የሚቃዠው ህልም ነው፡፡..
ሳይንስና ሳይንሳዊ የአጠናን ዘዴን የሚያጣጥሉ ሰዎች ሳይንስ ይሳሳታል፤ በዚህ ላይ ለሁሉም ነገር መልስ መስጠት አይችልም ይላሉ፡፡ ለዚህ የማያወላዳው መልስ ..አዎ አንዳንዴ ይሳሳታል፡፡ ግን ደግሞ ስህተቶቹን የሚያርምበት ስርዓት ዘርግቷል፡፡ የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ በቀር ስህተቶቹን ያርማል.. ነው፡፡
ጠያቂዎቹ በግልጽ ያልተገነዘቡት ነገር ቢኖር መሳሳቱንስ ቢሆን የነገራቸው ሳይንሱ እራሱ አይደለም? የሚገርመው ነገር ሳይንስ ይሳሳታል ከሚሉት ውስጥ እስቲ አንድ ምሳሌ ጥቀስ ቢሉት ወይ ሳይንስ ገና ዳዴ በሚልበት ዘመን የነበሩ ስህተቶችን አልያም በየመንደሩ የሚታተሙ በስመ ሳይንስ ወሬዎችን ይጠቅሳል፡፡ የሳይንስን መሰረታዊ አቅጣጫ ሊቀለብሱ የሚችሉ ስህተቶች ተፈጽመው ከሆነ ለሚያስተምሩን ምስጋናችን ከፍ ያለ ነው፡፡ ህልም ተፈርቶ ሳይተኛ አይታደርም፡፡ ስህተትንም ፈርቶ ድንቁርናን አሜን ብሎ መቀበል እንደዚያው ነው፡፡ እያንዳንዱ የተፈጥሮ ሚስጢር በተገለጠ ቁጥር ብዙ ጥያቄዎችን ይዞ ይመጣል፡፡ ስለዚህ ያለማወቅ ድንበር (Frontier of ignorance) ይሰፋል፡፡ በያንዳንዱ ተጨማሪ እውቀት አለም በቁሳዊውም ሆነ በመንፈሳዊው መልክ የተሻለች ቦታ ትሆናለች፡፡ በዚህ ስሜት የተቃኙ ሰዎች ሁሌም አለማወቃቸውን አምነው እውነትን በጥረታቸው ይፈልጋሉ፡፡ ሌሎች ደግሞ ያለ ድካም እንዲገለጥላቸው ይሻሉ፡፡
ሳይንስ እንደ አንድ የእውቀት አካል (Body of knowledge) በለውጥ ላይ ያለ (Dynamic)  ነው፡፡ በመሆኑም የተፈጥሮ ምስጢሮችንና ህጐችን በመግለጽ በኩል ምሉዕ ባይሆንም በሂደት ግን በነባራዊው አለምና ሳይንስ በሚያጠናቅራቸው ምስለ ዓለም መካከል ያለው ልዩነት እየጠበበ ይሄዳል፡፡ እያንዳንዱ ሳይንሳዊ እውነታ በየዘመኑ ከሚኖሩ አማራጭ እውነታዎች የተሻለ ነው፡፡ በመሆኑም በየዘመኑ ለሚነሱ ጥያቄዎች መልስ በመስጠት በኩል አገልግሎት ላይ ይውላል፡፡ ሳይንስ በእውነታዎቹ (Scientific truths) አይታበይም፡፡ ለተግባራዊ ጠቀሜታ (For practical Purposes) እንደ እውነት ይቆጥራቸዋል፡፡ እንደ ፍልስፍናዊ አመለካከት ደግሞ በማንኛውም ጊዜ ሊለወጡ የሚችሉ (tentative) አድርጐ ይቆጥራቸዋል፡፡
ማንኛውም እውነተኛ የሳይንስ የምርምር ውጤት በተመሳሳይ የምርምር ዘርፍ ውስጥ ባሉ ባለሞያዎች መገምገምና በተለያዩ ማዕቀፎች (Parameters) ውስጥ ተደጋጋሚ ሙከራዎችን ማለፍ አለበት፡፡ በመሆኑም አጠቃላይ የምርምር ማህበረሰቡን ግልጽነት ይጠይቃል፡፡ ቀደም ብዬ እንደገለጽኩት ሳይንስ እራሱን የሚያይስ የእውቀት ዘርፍ (Self-criticizing and self-correcting system of thought) ነው፡፡
ሳይንስ የተለያዩ የእውቀት ዘርፎች ስብስብ ነው፡፡ ፊዚክስ፣ ኬሚስትሪ፣ ባዮሎጂ፣ ጂኦሎጂ፣ ኮስሞሎጂ... ወዘተ፡፡(ለውይይታችን ከሚያበረክተው አስተዋኦ አንፃር ብዙም አያስፈልጉም ብዬ ከተውኳቸው የማህበራዊ ሳይንስ ውጪ)፡፡ በነዚህ የሳይንስ ዘርፎች ውስጥ ያሉ እውነታዎችና እሳቤዎች እርስ-በርስ የማይጣጣሙ ከሆነ ሁሌም ለጥያቄ ይቀርባሉ፡፡ ሁሉም ዘርፎች አንዱ በአንዱ ላይ ተደራርቦ ሕንፃ እንደሚገነባ ጡቦች ናቸው፡፡ በአንደኛው ዘርፍ የሚድረግ ጥናት ለሌላኛው ብርሃን ይፈነጥቃል፡፡ ለምሳሌ ለዝግመተ-ለውጥ መላምት መረጃዎችና ማረጋገጫዎች ከተለያዩ የእውቀት ዘርፎች ይመዘዛሉ፡፡ ዝግመተ-ለውጥ ተካሂዷል ከተባለ መሬት ረጅም እድሜ አላት የሚለውን አንድምታ (implication) ያስከትላል፡፡ ይህን ደግሞ ከጂኦሎጂ፣ ከኮስሞሎጂ ከፊዚክስና ከኬሚስትሪ ከሚገኙ ወደ አንድ አቅጣጫ ከሚሄዱ መረጃዎች (converging facts) ማረጋገጥ ይቻላል፡፡ ይሄ እውነታ ነው እንግዲህ ከማንኛውም ሌላ ምንጭ ከሚመጣ እውቀት ይልቅ በሳይንሳዊ መንገድ የተገኙ እውቀቶች የተሻሉና አስተማማኝ እንደሆኑ የሚያደርገው፡፡ (በመገለጥ (revealation) የሚገኝ እውቀት መኖሩ እስኪረጋገጥ ድረስ፡፡)
አንድን የተፈጥሮ ባህርይ ለመግለ የተለያዩ መላምቶች ሊቀመሩ ይችላሉ፡፡ እነዚህ መላ ምቶች እርስ-በርስ ተፃራሪ (contradictory)# ተደጋጋፊ (complementary)# ውስንና ጠቅላይ (special and general cases) እና ተፎካካሪ (competing theories) ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ለምሳሌ ያህል spontaneous generation (በቅበት ከግኡዝነት ወደ ህያውነት መምጣት) እና Evolution (ዝግመተ-ለውጥ) ተፃራሪ መላ-ምቶች ናቸው፡፡ ከደረቅ አፈር ውስጥ ዝናብ በዘነበ ጊዜ ድንገት እንቁራሪቶች ብቅ ሲሉ ያዩ ሰዎች በጊዜው የሰጡት መልስ አፈሩ በቅበት ወደ ህያው እንቁራሪቶች ተቀየረ የሚል ነበር፡፡ ለዘመኑ ጥያቄ የተሰጠ የዘመኑ መልስ ነው፡፡ የያዕቆብን የዥንጉርጉር በጐች አፈጣጠር ታሪክ የሚያውቅ አማኝ በዚህ ሃሳብ ይሳለቃል ብዬ አላምንም፡፡ ያዕቆብ የጄኔቲክስ ሳይንስ ባለማወቁ አይፈረድበትም፡፡ ትረካውንም ያመኑ ቀደምት ሰዎችም እንደዚሁ፡፡ ከአሁኑ ዘመን ግን ይህንን በግልቡ  (literally) አምኖ የሚሰብክ ቢገኝ ያሳፍራል፡፡ እንደ spontaneous generation አይነት ገራገር እሳቤዎች የሰው ልጅ ከስሜት ህዋሳቶቹ ውጭ ሌላ የማወቂያ መንገድ በሌለበት ጊዜ የታሰቡ ናቸው፡፡ ቴክኖሎጂ ይህንን ችግር በብዙ መንገድ ቀርፎአል spontaneous generation bEvolution ተተክቷል፡፡ የአይንስታይን የአንፃራዊነት መላ-ምት የኒውተንን ክላሲካል ሜካኒክስ ጠቅልሎታል፡፡ ኒውተን ተሳስቶ ነበር ማለት ግን አልነበረም፡፡ የኒውተን ህጐች የነባራዊው አለም ቁንል ግን ትክክል መግለጫዎች ተደርገው ይወሰዳሉ፡፡ የአይንስታይን አንፃራዊ መላ-ምት ደግሞ አድማሱን ሰፋ አድርጐ የኒውተን ህጐች የማይገልፁትን የግዙፉንና የፈጣኑን አለም ባህርያት በመግለጡ የሰው ልጅ የእውቀት አድማስ እንዲሰፋ አድርጓል፡፡ አለምን በመግለጥ ተደጋጋፊ (complementary) የሆኑ መላ-ምቶች ደግሞ የአንፃራዊነትNÂ የኳንተም ፊዚክስን መጥቀስ ይቻላል፡፡ አንዱ ግዙፉን አለም ምንነት ሲገልጥ ሌላው ደግሞ የደቂቁን ያብራራል፡፡ ሳይንቲስቶች የኳንተምና የአንፃራዊ መላ-ምቶችን አዋህዶ አንድ ወጥ የምልዓተ-አለም መገለጫ የሆነ መላ-ምት ለመቀመር በትግል ላይ ናቸው፡፡ ይህንን ለማሳካት በጅምላ “String theories” የሚባሉ ከ5 በላይ ተፎካካሪ መላ-ምቶች ቀርበዋል፡፡
..ሳይንስ የተመታ መላ-ምት እንጂ ግኝቶች የሏትም ተብሏል.. አባባሉ ቅኔ ብጤም መስሎኝ ነበር፡፡ የተመታ ሲሉ የከሸፈ፣ የተጣለ ማለታቸው ይሆን እንዴ ብዬ አሰብኩ፡፡ ለማንኛውም ቅንነታቸውን አስቤ የዶ/ሩን ስሜት በመገመት ..የቀረበ.. በሚለው ተርጉሜዋለሁ፡፡ ግን እኮ የሳይንስ መላ-ምቶች ምልዓተ-ዓለምን ከመግለ ባሻገር ለቴክኖሎጂ መሰረት ናቸው፡፡ ኳንተም መላ-ምትን ብንወስድ በጥቂቱ lSemi conductor lasars, computational chemistry እና pharmacology በመሳሰሉ ዘርፎች አገልግሎት ላይ ይውላል፡፡ የዝግመተ-ለውጥ መላምት በህክምና፣ በእርሻ በስነልቦና ጥናት ዘርፎች አስተዋኦ ያበረክታል፡፡ (ከከንቱ አምልኮም ያላቅቃል) የአንፃራዊ መላ-ምት bGps መሳሪያ አጠቃቀም ላይ በአገልግሎት ላይ ውሏል፡፡ ይህንን ሁሉ የሳይንስ ትሩፋቶች ወደ ጐን ትተው ነው እንግዲህ ዶ/ሩ ሳይንስ መላ-ምት እንጂ ግኝቶች የሏትም የሚሉት፡፡ ወይስ ቴክኖሎጂ የሳይንስ ውጤት መሆኑ ቀርቶ ድንገት እንደ እንጉዳይ የሚበቅል ነገር ሆነ?
ዶ/ሩ የቃላትን ትርጉም በጅምላ ሆን ብለው በማዛባት በስነ-አመክንዮ ደንብ Equivocation (አሻሚነት) የሚባለውን የክርክር ግድፈት (logical fallacy) ፈመዋል፡፡ እንደው ለነገሩ ይህንን ጠቀስኩ እንጂ ሁፋቸው በጠቅላላ ድንቅ የስነ-አመክንዮ ግድፈት ማስተማሪያ ይወጣዋል፡፡ (ጊዜና ፍላጐቱ ላለው የሚከተሉትን የስነ-አመክንዮ ግድፈት አይነቶች አንብቦ ከዶ/ሩ ሁፎች ጋር እንዲያገናዝብ እጠቁማለሁ፡፡ Fallacies: Personal attack, Argumentum ad populum, Incomplete comparision, Moving the goal post Nirvana fallacy, cherry picking...)
እንደ ፀሐፊው አባባል ሳይንስ ስለ ፍጥረት አመጣጥ ለመናገር ብቃት የላትም፤ መብትም የላትም፡፡ ለዚህ በብቸኝነት መልስ መስጠት ያለባት እምነታቸው ብቻ እንደሆነች አድርገው ያምናሉ፡፡ ሳይንስ አለት ከሰክሶ ቤተ-ሙከራ ቀይሶ የስነፍጥረትን ሚስጢርና አመጣጥ ደረጃ በደረጃ እየፈታ ባለበት በአሁኑ ወቅት ከሁለት ሺህ ዓመታት በፊት የተፃፉ መሐፍት ላይ የሙጥኝ ማለት አሳዛኝ ነው፡፡ ለሳይንስ ከምናውቀው ተፈጥሯዊ ምልዓተ-ዓለም (universe) ውጪ ሌላ ልዕለ-ተፈጥሮ (super natural) ነገር የለም፡፡ ካለም የማረጋገጡ ሸክም (burden of proof) የሚያርፈው አለ በሚሉት ላይ ነው፡፡ በምልዓተ-ዓለም (universe) ውስጥ ያለ ማንኛውም ነገር የሳይንስ የጥናት ምንጭ ነው፡፡ ህይወትንም ጨምሮ፡፡ ስለ ህይወት አመጣጥ ከማንኛውም ምንጭ በተሻለ ሊገል የሚችለው የዝግመተ-ለውጥ መላ-ምት ነው፡፡ ይህንን እውነታ የዓለም ትልቋ ቤተ-ክርስቲያን የሆነችው የካቶሊክ እምነት እንኳን አሳማኝነቱን እንደነገሩም ቢሆን ቀባብታ ተቀብላዋለች፡፡ ዶ/ሩ ይህንን የሚያሽር ጠንካራ መከራከሪያ ከእምነት መሐፋቸው ማቅረብ ከቻሉ ያምጡ፡፡ ያብራሩልን፡፡ ከቻሉ የአንዱን ድክመት ብቻ ሳይሆን የሌላውንም አማራጭ ጥንካሬ በጉልህ ሊያሳዩን ይገባል፡፡ ከዚህ በተረፈ ማጣፊያው ሲያጥር እምነት፣ የእምነት መነር . . .እያሉ ትርጉም አልባ ቃላት በመደርደር የሌለ ቀንዳም ፈረስ (Unicorn) እየፈጠሩ መጋለብ ማጭበርበር ነው፡፡ የሳይንስ ስህተት መስራት የመሐፍ ቅዱስን እውነትነት አያረጋግጥም፡፡ ይህ የሀሰት አማራጭ (False dichotomy) ነው፡፡ እስከሚገባኝ ድረስ የማንኛውም አስተሳሰብ እውነትነት የሚለካው አንድም ሃሳቡ ባለው ውስጣዊ ስምምነት (Internet Consistency) አልያም ከውጫዊው አለም ተሞክሮ ጋር ተመሳክሮ መሆን አለበት፡፡ መሐፍ ቅዱስ  ስለ ፍጥረት አመጣጥ ይተርካል፤ የታሪክ ዘገባዎች አካቷል፤ ስለ ግብረ-ገብ (Ethical Values) መመሪያና ህጐች አስቀምጧል፡፡ እነዚህ ሁሉ ታድያ ለሳይንስ ተገቢ የጥናት መስኮች (Legitimate areas of studies) ናቸው፡፡ እንደ ሳይንሱ ሁሉ ሐይማኖትም የሰው ልጆች የአእምሮ ውጤት ነው፡፡ እያንዳንዱ አማኝ የራሱን እምነት የአምላክ ቃል አድርጐ ይመለከታል፡፡ ከእርሱ እምነት ውጪ ያሉትን እምነቶች በሙሉ የሰው ልጅ ስራ እንደሆኑ አድርጐ ያስባል፡፡ (አልያም ያው የፈረደበት ሰይጣን በምክንያትነት ይቀርባል)፡፡ በአማኝና ኢ-አማኒ መካከል ያለው ልዩነት ከየትኛውም አማኒ አቅጣጫ ሲታይ ኢ-አማኒው አንድ ተጨማሪ አምላክ መካዱ ነው፡፡ አማኒው ..የኔ አምላክ እኩል ይሆናል እውነት.. ይላል፡፡ ኢ-አማኒው ..ያንተ አምላክ ሲደመር የሌላው አምላክ እኩል ይሆናል አልቦ.. ይላል፡፡
ስነ-ፍጥረትን፣ ታሪክንና ግብረ-ገብነትን በአጠቃላይ ምልዓተ-አለምን በተመለከተ ሳይንስም ሆነ ሀይማኖት መለካት ያለባቸው በእኩል ሚዛን ላይ ነው፡፡ አለበለዚያ አንዱን ማብጠልጠል ሌላውን ያለማጣሪያ የዋንጫ ባለቤት ማድረግ ሚዛናዊነትን ማጓደል (Double Standard መጠቀም) ይሆናል፡፡ በዚህ መስፈርት ነው የአንዱ ልዕልና  የሌላው ኮስማናነት መለየት ያለበት፡፡ የአንዱን ገመና በጓዳ ሸሽጐ የሌላውን በአደባባይ ማብጠልጠል ግፋ ቢል ተብጠልጣዩን ያዋርድ እንደሆነ እንጂ የተሸሸገውን አያነግስም፡፡ ይሄ ..ሳይንስ ይሳሳታል.. ወሬ አስቀድሞ ቡጢ ሰንዝሮ ለማደናገጥ ካልሆነ በቀር እምነትም ቢሆን እኮ በተቃርኖ የተሞላ ነው፡፡ የናዚ ጀርመንን የተቀነባበረ የዘር ማጥፋት ዘመቻና የሩዋንዳን ጅምላ ፍጅት የሰማ ጤነኛ ህሊና ያለው ሰው፤ ድርጊቱን እንደሚያወግዝ ጥርጥር የለውም፡፡ በመሐፍ ቅዱስ ውስጥ ይህንን የመሰሉ ብዙ ድርጊቶች ሞገስ ተላብሰው ተከትበዋል፡፡ ሌሎችም ብዙ ብዙ አሉ፡፡ የፈለገ ሰው እነዚህን እውነታዎች ከመረጃ መረብ ላይ ተመልክቶ በእጁ ካለው መሐፍ ጋር ማገናዘብ ይችላል፡፡ ለብዙዎቹ ምክንያት ወይም ሰበብ ማቅረብ ይቻላል፡፡ በምንም ቢያሳብቡ ሰበብ የማያገኙላቸው እንዳሉም እገምታለሁ፡፡ ደረቅ እውነታዎችን (facts) በተመለከተ ግድፈቱ የትዬሌሌ ነው፡፡ (እምነት በየዋህነት ሆነ እንጂ ሃይማኖትን ምን ይውጠው ነበር?)
ከየትም ይምጣ ወዴትም ይሂድ የሰው ልጅ ለአፍታም ቢሆን በዚህች ዓለም ህያው ሆኖ ያልፋል፡፡ ሁሉም ትውልድ የየዘመኑን ጥያቄ ይጠይቃል፡፡ ከዘመኑ ቀድሞ የጠየቀ ደግሞ እብድ ይባላል፡፡ (ጥሩነቱን ጤነኞቹ ሁሉ ሲያልፉና ሲረሱ እርሱ በታሪክ ስሙ ይወሳል፡፡) እያንዳንዱ ትውልድ ከቀደመው ትውልድ የወረሰውን ተመክሮ መሰረት አድርጐ የራሱንም ጨምሮ ለራሱ የማንነት ጥያቄ መልስ ይሰጣል፡፡ ችግሩ የሚመጣው እነኚህኑ የራሱን መልሶች ከራሱ W ባለ ኃይል የተሰጡና የማይነቃነቁ አድርጐ ሲያመልካቸው ነው፡፡ ሳይንስ ይህንን ተመክሮ የሚሰበርና ለሰው ልጆች የአስተሳሰብ ነፃነት የሚያጐናጽፍ የራሱ የሰው ልጆች የጥረት ወጤት ነው፡፡
ማሪ  
ሰሞኑን በአንድ የኖርዌይ ዜግነት ባለው ወጣት በሰላማዊ ሰዎች ላይ የተፈመውን ግድያ ሳታደምጡ አልቀራችሁም፡፡ ወጣቱ ግድያውን የፈመው |m«¤-ሃይማኖት´ በአገሩ ላይ የፈጠረውን ስጋት ለመቋቋም በዚህ መንገድ ..አብዮት.. ለማፈንዳት እንደሆነ በሰጠው ቃል ገልል፡፡ ወጣቱ እንደሚመኘው በዛሬ ዘመን እያንዳንዱ ሃይማኖት የየራሱን ክልል አበጅቶ ..አትድረስብን.. ቢባባል ዓለም ምን ልትመስል እንደምትችል እስቲ አስቡት፡፡ ሰዎች በሃይማኖት ልዩነት ስም የአምሳያቸውን ህይወት ለመቅጠፍ ሲቻኮሉ ስንሰማ ሃይማኖታዊ ደመ-ነፍስ (instinct) ምን ያህል ጠንካራ እንደሆነና ለወደፊቱም ለዓለም ሰላም የሚጋርጠውን አደጋ በጉልህ ያሳያል፡፡
አንዳንድ ሰዎችና ቡድኖች ደግሞ ይህንን ደመ-ነፍስ በመቆስቆሰና ነዳጅ በመነስነሰ ሊያጋግሙት ሲሯሯጡ ይታያል፡፡ ይህ ሁሉ የሚመነጨው ታዲያ ከሃይማኖት ውስጣዊ ባህሪ ነው፡፡ ..ከኛ ያልሆነ የኛ ጠላት ነው.. በሚል ስሜት የሃይማኖት ልዩነትን እያጐሉ መረጋገም፣ ሲቻልም ጦር መማዘዝ የሃይማኖት ገታ መሆኑን አሁን ላይ ሆነን ወደ ኋላ ስንመለስ ታሪክ ያሳየናል፡፡ ሃይማኖት ባይኖርም አለም ፍም ሰላም ትሆናለች ብዬ x§SBM””ሆኖም ግን ሃይማኖት አልባ አለም ቢያንስ በሃይማኖት ምክንያት ከሚነሳ ትርምስ ነጻ ትሆናለች፡፡ ሃይማኖት የቆሰቆሰችው እንጂ ያበረደችው ጦርነት ስለመኖሩ ሰምቼ አላውቅም፡፡
ጽሑፌን ከማጠቃለሌ በፊት ለዶ/ሩ አስተያየት መሰል ጥያቄ ላቅርብ፡፡ እንደሚያውቁት (እርሶ ራስዎ ምሳሌ ይሆኑኛል) በየዋህነት ለማመን የሚሹ እስካሉ ድረስ የቤተ-ክርስቲያን ደጆች አይዘጉም፡፡ እድሜ ለሳይንስና ቴክኖሎጂ ሰበካዎችን ከቤት ሆኖ መከታተል ተችሏል፡፡ ስለዚህ ሳይንስ በሃይማኖት ላይ ከሚያደርሰው አደጋ ይልቅ በሃይማኖቶች ምክንያት የሚነሳ GT እጅጉን አደገኛ ነው፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ በሃይማኖቶች መካከል ሊኖር ስለሚገባ መቻቻል ካለ አንድ ይበሉ፡፡ ወደድንም ጠላን የምንኖረው ሃይማኖት በበረከተባት ምድር ነው፡፡ በሃይማኖት ምክንያት በሚነሳ እሳት የሚለበለበው አማኒውም ኢ-አማኒውም ነው፡፡ መናቆራችን ካልቀረ እየተማማርን ብንናቆር መልካም አይመስልዎትም? የዛሬን አበቃሁ፡፡ ቸር እንሰንብት፡፡

Confession of an agnostic atheist
ስነ-ፍጥረትን፣ ታሪክንና ግብረ-ገብነትን በአጠቃላይ ምልዓተ-አለምን በተመለከተ ሳይንስም ሆነ ሀይማኖት መለካት ያለባቸው በእኩል ሚዛን ላይ ነው፡፡ አለበለዚያ አንዱን ማብጠልጠል ሌላውን ያለማጣሪያ የዋንጫ ባለቤት ማድረግ ሚዛናዊነትን ማጓደል (Double Standard መጠቀም) ይሆናል፡፡ በዚህ መስፈርት ነው የአንዱ ልዕልና  የሌላው ኮስማናነት መለየት ያለበት፡፡ የአንዱን ገመና በጓዳ ሸሽጐ የሌላውን በአደባባይ ማብጠልጠል ግፋ ቢል ተብጠልጣዩን ያዋርድ እንደሆነ እንጂ የተሸሸገውን አያነግስም፡፡
ደረጀ ፀጋዬ
ለሐምሌዘጠኙየመጀመሪያጽሑፉዶ/ሩበሐምሌ16 ዕትም የመሰላቸውን መልስ ሰጥተውኛል፡፡
በለመድኩት የአርፋጅ ባህሪዬ ብዘገይም አልቀረሁምና ምላሼ ይሄውና፡፡ ..በሳይንሱም ቢሆን አትደርስብኝም.. በሚል ስሜት ይመስላል ለመረጃነት በተጠቀምኩት ሃሳብ ላይ አከል አድርገው አብራርተዋል፡፡ በምንም ስሜት ያቅርቡት ለአንባብያን የማንበብ መነቃቃት አወንታዊ አስተዋጽኦ ስለሚያበረክት የሚደገፍ ነው፡፡ ሆኖም የቀረው ጽሑፋቸው ተራ ስድብና የተንሻፈፉ የሳይንስ እሳቤዎች ናቸው፡፡ በማጠቃለያቸው ላይ ስብከት መሳይ ነገርም አክለዋል፡፡ ከተነሳሁበት አላማ አንፃር አንዳንዴ ብዕሬን ካላዳለጣት በቀረ ግንብ ተከልለው ድንጋይ እንደሚወራወሩ ህፃናት የስድድብ አዙሪት ውስጥ ለመግባት አልከጅልም፡፡

Read 4938 times Last modified on Saturday, 06 August 2011 14:50