Saturday, 06 August 2011 14:51

..ዝም ብትሉ ጥበብ በሆነላችሁ..

Written by  ጤርጢዮስ - ከቫቲካን
Rate this item
(2 votes)
  • ..ቀን የሚያመጣውን አታውቅምና ዛሬ በሚሆነው አትመካ..

ክርክሩ በእርግጥም ..ሳይንስ የእኛ ብቻ ስለሆነ ሳይንሳችንን አትንኩብኝ!.. የማለት ድርቅና ካልሆነ በቀር የምድርን ዕድሜ አስመልክቶ በአማኞቹም ሆነ ባላማኞቹ ሳይንቲስቶች መካከል እስከዛሬም ድረስ ያላባራው እሰጣ-አገባ (ሀቁ የት እንዳለ የታወቀ ቢሆንም) በአንዱ ወገን አሸናፊነት እንደተጠናቀቀ ማስመሰል በጣም ያስተዛዝባል፡፡
ዛሬብዙስለተወራለትሳይንስጥቅምሣይሆንቅምጥቂትነገርእላለሁ፡፡ሰሞኑን..ከእኛወዲያ    ሊቅ፣ ከእኛ ወዲያ ተመራማሪ ላሣር ነው.. በማለት የአማኝ አሳማኝ ሙግታችንን የ..አሸንፈው - አሸንፋት.. የመንደር ውስጥ ፉክክር ለማስመሰል ብቅ ያሉትን ..ጊዜ - አምላኩ.. ጥቂት ማለት ፈልጊያለሁ፡፡

ሳይንስ ለእምነታውያኑ ማወናበጃ እንጂ ..ማሳመኛ.. እንዳልሆነ በማስመሰል የፃፉትን መልስ ላጣው ክፍተቱ ..ጊዜን ተስፋ አድርጉ.. እያለ ስንቱን ጀግና በከንቱ ለሚያባክነው፣ አባይ ሳይንስ ጥብቅና የቆሙትን ሰው ማለቴ ነው፡፡
ቦታንና ጊዜን ለሰው የሰጠው የ..ጊዜ.. ባለቤት፣ በ..ጊዜ.. መጠቀም እንጂ በራሱ በጊዜ ላይ ተስፋ መጣልን አያበረታታም፡፡ በመሀፍም ..ቀን የሚያመጣውን አታውቅምና ዛሬ በሚሆነው አትመካ፡፡.. በማለት፣ ..ጊዜ.. ላለው ሁሉም ዓይነት የዕውቀት መዳረሻ ዋስትና እንደማይሆን ተፏል፡፡ ስለዚህም ..የእኛ ሳይንስ ነገርን የሚያረጋግጠው በጊዜ ውስጥ በመሆኑ ..መጨረሻውን ጊዜ ያሳየኛል፡፡.. ብሎ ጊዜ ሊሰጠው የማይቻለውን ዕውቀትና እርግጠኝነት መጠባበቅ ምስኪንነት እንጂ ብልህነትን አያመለክትም፡፡ ዳሩ ግን ..ሳይንስ የእኛ ነው.. ለሚሉት ጊዜ ትምክህት እንደሆነላቸው ሁሉ ለእኛ ደግሞ ለምናምን ..ቀኑ በትዕዛዝህ ይኖራል!.. የተባለለትና ሁሉን ..አሁን.. የሚያውቀው የበለጠውን ያስመካናል፡፡ (ይህ ግን ሁሉን እርሱ ስለሚያውቅልኝ እኔ ምንም ማድረግ አያስፈልገኝም ለሚያሰኝ ስንፍና የሚዳርግ አባባል አይደለም፡፡) ይልቁንም የህዋ-ዓለሙን አጀማመር አስመልክቶ እምነታውያኑ በቃሉ ከሰሙት እውነት አፈትልኮ አሳማኞቹን ..አሸናፊ.. የሚያደርግ ልዩ ሣይንሣዊ ዕውቀትና ግኝት ከየትም እንደማይመጣ በእምነት እናውቃለን፡፡
ክርክሩ በእርግጥም ..ሳይንስ የእኛ ብቻ ስለሆነ ሳይንሳችንን አትንኩብኝ!.. የማለት ድርቅና ካልሆነ በቀር የምድርን ዕድሜ አስመልክቶ በአማኞቹም ሆነ ባላማኞቹ ሳይንቲስቶች መካከል እስከዛሬም ድረስ ያላባራው እሰጣ-አገባ (ሀቁ የት እንዳለ የታወቀ ቢሆንም) በአንዱ ወገን አሸናፊነት እንደተጠናቀቀ ማስመሰል በጣም ያስተዛዝባል፡፡ ..ጊዜ.. ለውጦችን ለመገንዘብ የሚያስችል መሣሪያ መሆኑ ባይካድም ..ጊዜ.. ግን በራሱ የማይፈታቸው እንቆቅልሾች መኖራቸውን መካድ የማይቻል ነው፡፡ በዛሬው ዘመን ሳይንቲስቶች ዘንድ ተቀባይነት ያለው የሄይስንበርግ የኢ-እርግጠኝነት ህግ (The Principle of uncertainty) የትኛውንም ሳይንሳዊ ብልሃት በመጠቀም በዩኒቨርስ ውስጥ ስለሚፈጠሩት ጊዜ-ወለድ ክስተቶች በእርግጠኝነት ለመተንበይ ያለመቻሉን መጠቆሙ የሳይንስን አቅም ውሱንነት በሳይንሳዊ ዘዴና መረጃ የነገረን መስሎኝ፡፡   
የሳይንስ ጥቅም ቀላል የሚባል ባይሆንም አቅሙን ያለማወቅ ግን ሰውን ተላላ አድርጐ ያስቀራል፡፡ እስቲ ስለዚህ ጉዳይ አንድ ነገር አንስተን እንጣል፡፡ እንዲያውም አልሆነም ወይም ጨርሶ አይሆንም እንጂ በሳይንሳዊ ዘዴ ለመረጋገጥ ቢሊዮን ዓመታት የጠየቀው የሰው ዘር ምንጭ፤ በቢሊዮናት የሚቆጠር የጊዜ ርዝመትን አቆራርጦ አሁን እኛ ያለንበት የመረጋገጫው ዘመን ላይ ደርሶ ሀቁ ተረጋገጠ እንበል፡፡ ሩቅ ሳንሄድም በቅርቡ ያቺ የሰውን ቅድመ ታሪክ ..ታወራለች.. የተባለችው የእኛይቱ ..ሉሲን.. ዕድሜ የዕጥፍ እጥፍ የምታስከነዳው ..አርዲ.. የተሰኘችው ቅሪተ - አካል ከጦጣነት ተላቃ እንደ ሰው መቀናጣት ከጀመረች (ለዚያውም የፊት ገጽታዋ በቅጡ ሳይስተካከል፣ ፀጉሯም ከሰውነቷ ረግፎ ሳያልቅ ተቻኩላ ማለት ነው፡፡) 4.3 ሚሊዮን ዓመታት ይሆናታል መባላችንን ምሣሌ እንውሰድ፡፡ (ጥናቱ ስንትና ስንት ዓመታትን እንደፈጀና እውነቱን ለማጣራት የፈሰሰውን ዕውቀትና ጉልበት ከግምት ውስጥ ማስገባታችንን አንርሳ፡፡)
ግን...ግን...ሊቃውንቱን ለዘመናት ሲያደክም የኖረው የአርኪዎሎጂ ጥናት የተዘበራረቀ ውጤት እንደተጠበቀ ሆኖ ከጊዜ ማህፀን ውስጥ ተፈልቅቆ ህያው ለመሆን የበቃው የማወቂያ ዘዴ (ሳይንስ) ገና ሁለት መቶ ዓመቱን እንኳ ሳይደፍን ሰው የመሆን ዕጣ ፈንታ በአዝጋሚ ለውጥ ሽግግር ውስጥ ያለፈ ስለመሆኑ ደፍሮ ለመተንበይ መቸኮሉ ከልጅነት ጠባዩ የመነጨ ካልሆነ በቀር መቼምና የትም ቢሆን ለሰው ልጅ አእምሮ አጥጋቢና አርኪ መልስ ሆኖ አያውቅም፡፡ የሰው ልጅ አእምሮ እንዴትም ቢያዘግምና ቢንቀራፈፍ ወደ ዛሬው የቴክኒዮሎጂ ዓለም ለመድረስ ይህን ያህል ቢለዮን ዓመታት ፈጅቶበታል ማለት የማይለጠፍ ስድብ ከመሆን የዘለለ ቁም ነገር የለውም፡፡ ዳሩ ግን ይሄው ..ሳይንሳዊ.. መላምት ቀን እንደመሸበትና ሰማይ እንደተደፋበት ያበሰረን ያው ልጅነቱ ..ሳይንስ.. መስሎኝ፡፡ ይልቁንስ ለ..ጊዜ አምላኩ.. ተሟጋቻችን የምመክራቸው እንዲህ በማለት ነው፡፡
የምድሪቱን ዕድሜ ለመገመትም ሆነ የፍጥረቱ ምንጭ ማን እንደሆነ አውቆ ለማረፍ በጭራሽ ጊዜ አይጠበቅም፡፡ እነሆ እርሱን የማወቂያው ሰዓት ዛሬ ነው፡፡ እንዲያውም አሁን ነው፡፡
በቀረው ግን እንዲህ ዓይነቱ አስተያየት ሳይንስን ከማጣጣል ጋር ጨርሶ ግንኙነት የለውም፡፡ እናንተ ..ድንገቴ ክስተት.. እኛ ደግሞ y|እግዚአብሔር እጅ ሥራ.. የምንለውን ፍጥረተ ዓለም ጅማሬ፤ ደፍሮ ለመናገር ሳይንስ በቂም ብቁም ስላለመሆኑ ግን ከእኔ እጅግ በተሻለ ዕውቀትና ቋንቋ በዚሁ ጋዜጣ ላይ የፃፉትንና የሚጽፉትን እማኞች ሳይጨምር እኔም ጥቂት ጫጭሬያለሁ፡፡
የስሌትንና የስሜትን ግንኙነት መሠረት በማድረግ ብቻም ሳይሆን እግዚአብሔር ለዕውቀት የሰዎችን አእምሮ እንደሚያነቃ ለመግለጽ እንደ አንስታይን ያሉ ታላላቅ የሳይንሳዊ ግኝት ሊቃውንት ወደ ስሌት ከማምራታቸው አስቀድሞ ስለ ነገሩ ተቀራራቢ ግምት ያሳድሩ ዘንድ መንፈሳቸውን ያነሳሳ ኃይል ስለመኖሩ የሰጡትን ምስክርነት ጠቅሻለሁ፡፡ እንደ ሶቅራጦስ ያለውን ስመ ገናና ፈላስፋም የፍልስፍናውን ጭብጥ ያስያዘውም ሆነ የእውነት ፍለጋው ራሱ ከውስጡ በሚጐተጉተው ድምጽ (inner voice) የተመራ ስለመሆኑ ጽፌያለሁ፡፡
በዚህም አንዱ የውጭውን ዓለም ሌላኛው ደግሞ የሰውን ውስጣዊ የአስተሳሰብ ሥርዓት በዕውቀት ያቃኑ ዘንድ ተልዕኮን የሰጠው፣ ዕውቀታቸው ፍፁም ባይሆንም ገና ከጠዋቱ አርስቶትል ስለ ሳር ቅጠሉ፣ ፕሌቶ ደግሞ የፍጥረቱን ምንጭና ማንነት ይመረምሩ ዘንድ ያተጋቸው፣ ለጠቢባን ጥበብን የሚሰጥ አምላክ መኖሩን ለማጽናት ተጠቅሜበታለሁ፡፡
በእርግጥም ደግሞ ሊቃውንቱ ዕውቀታቸውን፣ ጠቢባኑም ጥበባቸውን ከዬትም አላመጡትም፡፡ ምንም ቢያደርጉና ቢያገኙ፣ የፍጥረቱም ሆነ የዕውቀቱ ምንጮች ራሳቸው ሰዎቹ አልነበሩም፤ ዛሬም አይደሉም፡፡ ሆኖም በጥረታቸው ስላገኙት ነገር፣ በድካማቸው ስላመጡት ውጤት ምሥጋና ይገባቸዋል ወይ?  ..አዎን..፣ ሥጦታቸውን ፈልገው ለማግኘት ስላደረጉት ጥረት ምሥጋና፣ ፈቃዱን ለመሙላትም መክሊታቸውን ባለመቅበር ላሳዩት ታማኝነት ሽልማት ይገባቸዋል፣ ከዚህ በላይ ግን ምንም አይደለምና ክብሩ ሁልጊዜም ክብር ለሚገባው መሠጠት አለበት፡፡ የሰው ክቡርነት ከፍታ በነገር ሁሉ ክብርን lእግዚአብሔር በመስጠቱ የሚለካ ሲሆን ..እርሱ ሊልቅ እኔ ግን ላንስ ያስፈልጋል.. የማለት ትህትና፣ ..ላደርግ የሚገባኝን ያደረግሁ ተራ አገልጋይ ነኝ.. የማለት እውነተኝነት ከሰው ሁሉ ይጠበቃል፡፡  
እንግዲህ ትምክህት የለም ..አዋቂ.. ሆኛለሁ የሚለው ጐበዝም ሆነ ..አማኝ.. ነኝ       የሚለው ጀግና ሊለው የሚገባው ይህንኑ ነው፡፡ ተፈጥሯዊው ስጦታም ሆነ መንፈሳዊው ፀጋ የተገኘው ከእርሱ ዘንድ በመሆኑ በሁለቱም ዘንድ ..ክሬዲቱን.. መውሰድ ያለበትና የሚገባው እርሱ ነው፡፡ መመካት ግድ ከሆነም የተፈቀደው በእርሱ መመካት ነው፡፡ መጽሐፍም የሚለው እንዲህ ነው ..ጠቢብ በጥበቡ አይመካ፣ ኃያልም በኃይሉ አይመካ፣ አዋቂም በዕውቀቱ አይመካ...ጽድቅንና ፍርድን በምድር ላይ የሚያደርግ እርሱ መሆኑን በማወቁ በዚያ ይመካ፡፡.. ለነገሩ ከ..ግጭት ዘመዶቻችን.. ጋርም ሆነ ከቲፎዞዎቻቸው ጋር ..ያጋጨን.. ነገር ቢጨመቅ የሚወጣው የነጠረ ነገር የአንደኛው ወገን በራሱ የመመካት ዝንባሌና የሌላኛው bእግዚአብሔር የመመካት ልዩነት እንጂ በዕውቀትም ሆነ በትጋት ከአላማኞቹ አንሶ የተገኘ አማኝ በመኖሩ አልነበረም፡፡ በዚህ ተወዳድሮ መበላለጥ ካለ ግን በላጩ የጥበቡ መጀመሪያ እግዚአብሔርN መፍራት፣ የዕውቀቱም ዳርቻ ቅዱሱን ማወቅ የሆነለት ወገን መሆኑ ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ ብይኑ ግን ነገርን ሁሉ በጊዜው ውብ አድርጐ ከሠራውና ከሚዳኘው የተገኘ እንጂ ከራስ ትምክህት የመነጨ አይደለም፡፡
በቀረው ግን ሳይንስ እግዚአብሔር የሠራውን ፍጥረት እንደምንነቱ ፈትሾ የማወቂያ ዘዴ እንጂ ለአላማኙ yእግዚአብሔርN ያለመኖር ማረጋገጫ፣ ለአማኙም መኖሩን የማሳመኛ መሣሪያ አይደለምና ያልገባችሁን ከመናገር ዝም ብትሉ ጥበብ በሆነላችሁ ነበር፡፡

 

Read 4064 times Last modified on Saturday, 06 August 2011 15:19