Saturday, 06 August 2011 15:51

ከበለፀጉት እንማር!

Written by  ትዕግስቱ በለጠ
Rate this item
(0 votes)

እውነቱን እንነጋገር ከተባለ ማናቸውንም ነገር ልንማረውና ልናውቀው ከፈለግን ከትክክለኛው ባለቤቱ ብናገኘው ይመረጣል፡፡ ግብርናን ከገበሬው፣ የወጥ ቤት ሙያን ከወጥ ቤቷ ወይም ከምግብ አብሳዩ፣ ሹፍርናን ከሹፌሩ፣ ጋዜጠኝነትን ከጋዜጠኛው ወዘተ ሁሉንም ከባለቤቱ ወይም ከባለሙያው (ከሚያውቀው እንደማለት) ስንማረው ነው ጉዳዩ በቀላሉ የሚገባን፡፡ ሃብትና ንብረት ያላፈራ ሰው የብልግና መንገድ ላሳያችሁ ቢላችሁ እሱ ሃሳዊ መምህር ነው፡፡

ብልግናን የት ያውቀውና ነው የብልግናን መንገድ የሚመራችሁ፡፡ ሚሊዬነር ለመሆን የሚሻም ከሚሊዬነሮች ጋር ይዋል አልያም የህይወት ዘይቤያቸውን እና -  የተጓዙበትን የስኬት ጐዳና ይመርምር . . የገንዘብ አያያዛቸውንም ያስተውል፡፡
ከዚያም ከሚሊዬነሮች የቀሰመውን በትክክል በራሱ ህይወት ላይ ይድገመው፡፡ ምስጢራቸውን የህይወቱ ምስጢር ያድርገው፡፡ የብልግና ትምህርቱን በትክክል ተምሮ እንደሆነ ማረጋገጫው ታዲያ የእሱ ሚሊዬነር መሆን ብቻ ነው፡፡ ሚሊዬነር ካልሆነ ግን ትምህርቱ ወይም ምስጢሩ አልገባውም ማለት ነው፡፡ ብልግናን መማር የሚቻለው ከበለፀጉት ብቻ ነው ሲባል ግን የግድ ሚሊዬነሮችን ፍለጋ ስንባዝን መክረም የለብንም፡፡ የሚሊዬነሮችን ህይወት የሚተርኩ መፃህፍት፣ ግለ ታሪኮች ወዘተ ማንበብ ነው አንደኛው አቋራ መንገድ - ጥሩ ተደርጐ የተፃፈ መሃፍ ካገኘን ከባለፀጐቹ ጋር የተገናኘን ያህል ነውና፡፡ በዚህ ሁፌ የማስቃኛችሁ የሚሊዬነሮችን የስኬት ጉዞ የሚተርክ በቅርቡ ለንባብ የበቃ አነስ ያለ መሃፍ ነው - ..ታላላቅ ህልሞች.. ይላል ርዕሱ፡፡
መሃፉ ከ20 በላይ የሚሆኑ የዓለማችንን ሚሊዬነሮችና ቢሊዬነሮች የስኬት ጉዞ የሚዳስስ ሲሆን ከእያንዳንዱ ታሪክ በመለጠቅ xÅR የስኬት መመሪያዎች ቀርበዋል - ከራሳቸው ከሚሊዬነሮቹ ተመክሮ የተወሰደ፡፡ የሁፌ ዓላማ ይሄን የስኬት መሃፍ ለናንተ ማስተዋወቅ ነውና አለፍ አለፍ እያልኩ ሳነብ ያስደመመኝን ላጋራችሁ፡፡  
አሜሪካዊቷ ዴብር ጄ ፊልድስ (ዴቢ) በ20 ዓመቷ ወደ ቢዝነስ ለመግባት ስታቅድ በእጇ ላይ ሰባራ ሳንቲም አልነበራትም፡፡ በእርግጥ ኩኪስ አፍቃሪ ነበረች፡፡ አፍቃሪ ብቻ ግን አይደለችም፡፡ ÈÍ ኩኪስ እቤቷ እየሰራችም ቤተሰቧን ታስደምም ነበር፡፡ አንድ ቀን ግን የቅዠት የሚመስል ሃሳብ BL አለላት፡፡ ከቸኮላት የተቀመመ ልዩ ኩኪስ ሰርታ ለገበያ የማቅረብ ፍላጐት አደረባት፡፡ በችሎታዋ እርግጠኛ ብትሆንም ቢዝነስ ለመጀመር የሚያስችል ምንም ካፒታል አልነበራትም፡፡ ከዚህ ቀደም ተሞክሮ ባያውቅም የኩኪስ ቢዝነስ ፕሮጀክቷን ይዛ ወደ ባንክ አመራች - ገንዘብ ለመደበር፡፡ ታዲያ የቢዝነሱን xênT የባንኩ ሃላፊዎች መተንበይ ስላቃታቸው ትንሽ መጉላላቷ አልቀረም፡፡ የማታ ማታ ግን አሳመነቻቸውና ብድሩ ተፈቀደላት፡፡ እናም የመጀመሪያዋን የኩኪስ መደብሯን |Mr. Fields Chocolate Chippery´ በሚል ስያሜ ካሊፎርኒያ ውስጥ ከፈተች - እ.ኤ.አ በ1997 ዓ.ም፡፡ የዴቢ ኩኪስ ተወዳጅነትን ለማትረፍ ብዙ ጊዜ xLfj?Tም፡፡ በአሜሪካ ብቻ ሳይሆን በተለያዩ የዓለም አገራት? ዝናዋ እየናኘ መጣ? ከ20 ዓመት በኋላ ከፍተኛ የስኬት ጣራ ላይ ደረሰች፡፡ ያኔ በአሜሪካ ብቻ ከ600 በላይ የኩኪስ ማምረቻ መሸጫ መደብሮች ነበሯት፡፡
የስኬትዋ ምስጢር ከደንበኞችዋ ጋር ያላት የመግባባትና የመቀራረብ ችሎታዋ እንደሆነ የምትናገረው ዴቢ፤ ይሄ ደግሞ የደንበኞቿን የዕድሜ ልክ ታማኝነት እንዳስገኘላት ትገልፃለች፡፡
..ሲዲ አዟሪው ሚሊዬነር.. በሚል ርዕስ የቀረበው የጥቁር አሜሪካዊው የክሪስ ሌቲ የስኬት ገድል ደግሞ በአስደሳች የልብወለድ ታሪኮች መድበል ውስጥ የምናገኘውን ዓይነት ይመስላል በማለት ይጀምራል - መሃፉ፡፡ ክሪስ ሌቲ የሲዲ አዟሪነት ሥራውን የጀመረው የአጐቱን መኪና አጥቦ ለማክዶናልድ በርገር መግዣ በተሰጠው 9 ዶላር እንደሆነ በታሪኩ ውስጥ ተገልል፡፡ በኒውዮርክ ጐዳና የሙዚቃ ካሴቶችና ሲዲዎችን እያዞረ ይሸጥ የነበረው ሌቲ፤ የራሱን የቢዝነስ ኩባንያ የመክፈትና የታላላቅ አርቲስቶችን ሥራዎች የማሳተምና የማከፋፈል ትልቅ ህልም እንደነበረው ይናገራል፡፡ ዛሬ የጠገበ ሚሊዬነር ለመሆን ቢበቃም የመጀመርያውን ቢዝነስ ሲያቋቁም ከፍራሹ ሥር ቆጥቦ ያስቀመጣት ገንዘብ አንድ ሺ ዶላር እንኳን አትሞላም ነበር፡፡ እ.ኤ.አ በ1990 ..ቫዮሌተር.. የተባለውን የሙዚቃ አሳታሚና አከፋፋይ ቢዝነሱን የጀመረው ክሪስ ሌቲ፤ በኒውዮርክ ጐዳና አልበሞቻቸውን እየዞረ ሲሸጥላቸው የነበሩትን ዕውቆቹን የእነ ማሲ ግሬይና የእነ ኤል ኤል ኩል ጄን የሙዚቃ ሥራዎች በራሱ ኩባንያ ለማሳተምና ለማከፋፈል በቃ፡፡ መሃፉ የዚህን የጥቁር አሜሪካዊ የስኬት ታሪክ የሚቋጨው በአገራችን በሲዲ አዟሪነት የተሰማሩ ወጣቶችን ለጥረት በሚያነቃቃ ዓረፍተ ነገር ነው፡፡
..በሃገራችንም ካሴትና ሲዲ አዙሮ በመሸጥ ንግድ ከተሰማሩት በርካታ ወጣቶች መካከል እንደ ክሪስ ሌቲ የራሳቸውን ትላልቅ ኩባንያ በማቋቋም ስኬታማ የሚሆኑ ወጣቶችን የማናይበት አንዳችም ምክንያት የለም.. በሚል፡፡
በዚህ የበርካታ ሚሊዬነሮችን ታሪክ በሚተርክ መሃፍ ውስጥ ከተካተቱት ባለታሪኮች አብዛኞቹ የበለፀጉት ከባዶ ተነስተው ነው፡፡ ባዶ ሲባል የምር ባዶ ማለት ነው፡፡
መነሻ ገንዘብ ያወረሳቸው፣ ወይም ያገዛቸው የለም፡፡ ለምሳሌ ያህል የአሜሪካዊውን የዌይን ሁይዚንጋ ታሪክ እንመልከት - ከስኬቱ ጀምረን ወደ ኋላ የድሮ ህይወቱ በመመለስ፡፡ በአሜሪካ ለሚገኙ የቢዝነስ ሰዎች ..ፋይናንሺያል ዎርልድ.. በተሰኘ መሄት ..የዓመቱ ምርጥ ዋና ሥራ አስፈፃሚ.. ተብሎ መመረጥ የዕድሜ ልክ ህልማቸው ሊሆን ይችላል፤ ሁይዚንጋ ግን ለአምስት ዓመታት ይሄን ማዕረግ ደጋግሞ ተጐናፏል፡፡
..ደንበኛ ንጉስ ነው.. የሚለውን የቢዝነስ መርህ እንደ ሃይማኖት አጥብቆ የሚከተለው ሁይዚንጋ፤ የደከሙ ቢዝነሶችን በመግዛት ነፍስ እንዲዘሩ እያደረገ ወደ ስኬታማ የንግድ ተቋምነት በመለወጥ ይታወቃል፡፡ ከሁለት ጓደኞቹ ጋር በ1987 እ.ኤ.አ ..ብሎክስተር.. የተሰኘውን የመዝናኛ (ኢንተርቴይንመንት) ቢዝነስ ሲገዙ ድርጅቱ 19 መደብሮችና 7ሚ. ዶላር ካፒታል ነበረው፡፡ በሁለት ዓመታት ውስጥ ግን በ11 አገራት ቅርንጫፎች ያሉት 3700 መደብሮችና 4ሚ. ዶላር ካፒታል ያለው ኩባንያ አደረጉት፡፡ ኩባንያውን በ1994 ዓ.ም እ.ኤ.አ ..ቫያኮም.. ለተባለ ድርጅት የሸጠው በ8.4 ቢ.ዶላር ነበር፡፡ ተዓምር ነው
ከዚህም በላይ ተዓምር የሚያሰኘው ግን ሁይዚንጋ ከምን ተነስቶ እዚህ እንደደረሰ ስንሰማ ነው፡፡ በልጅነቱ እናትና አባቱ በመለያየታቸው ከእናቱ ጋር ይኖር የነበረው ሁይዚንጋ፤ እናቱን በገቢ ለማገዝ ከት/ቤት መልስ በነዳጅ ማደያ ነዳጅ በመቅዳትና በከባድ መኪና ሾፌርነት ይሰራ እንደነበር ይናገራል፡፡ በአሜሪካ የጦር ሃይል ውስጥም ለጥቂት ጊዜ አገልግሏል፡፡ የኮሌጅ ትምህርቱን ለማጠናቀቅ ሳይሆን የአንድ ሴሚስተር ክፍያ እንኳ ለመሸፈን አቅም እንዳልነበረው የሚያስታውሰው ዌይን ሁይዚንጋ፤ ኑሮዬን ለማሸነፍ ስል የኮሌጅ ትምህርቴን አቋርጬ ወጣሁ ይላል፡፡ ከኮሌጅ ሲወጣ የጀመረው ሥራ ቆሼ ሰብሳቢነት ነበር - ቆሻሻ በሚሰበስብ ኩባንያ ውስጥ፡፡ ከሁለት ዓመት በኋላ ግን የራሱን ቆሻሻ ሰብሳቢ ኩባንያ አቋቋመ፡፡ ታዲያ ከዚህ በላይ ለስኬት የሚያነሳሳ አስደማሚ ታሪክ ይኖራል? ከቆሼ ሰብሳቢነት ተነስቶ ቢሊዬነር ለመሆን በቅቷል - የቺካጐው ተወላጅ ዌይን ሁይዚንጋ፡፡ ሌላው የሃርቫርድ ዩኒቨርስቲ ተማሪ ዴቭ ኬም ደግሞ ቤት ለቤት ልጆች በማስጠናት ጀምሮ የ10 ሚ.ዶላር ባለሃብት ሆኗል ይለናል - ..ታላላቅ ህልሞች.. የተሰኘው የስኬት መሃፍ፡፡ ትንሽዬ ግሮሰሪ ከፍቶ ቢራ ሲነግድ የነበረው አሜሪካዊው ጆን ዊላርድ ማርዮት፤ ዛሬ በመላው ዓለም 143 ሆቴሎችና 6 ሪዞርቶች ሲኖሩት 1ሺ 400 ሬስቶራንቶች በስሙ አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ፡፡
በመሃፉ ውስጥ ከምንም ተነስተው የስኬት ማማ ላይ የወጡ የዓለማችን ባለፀጐች ተብለው ገድላቸው የተተረከላቸው የተለያዩ አገራት ሚሊዬነሮች ሲሆኑ የቻይና፣ የቱርክ፣ የህንድ፣ የኪርጊስታንና የሌሎች አገር ዜጐችም ይገኙባቸዋል፡፡
የኢንተርኔት ጨረታ ጀማሪዎች፣ የዴል ኮምፒውተር መስራች፣ የጉጉል ፈጣሪዎች እና የሌሎችም የስኬት ታሪክ በመሃፉ ውስጥ ተካትቷል፡፡
የ..ታላላቅ ህልሞች..ን አR ቅኝት ከመቋጨቴ በፊት በመሃፉ ውስጥ የስኬት መመሪያ ተብለው ከታሪኮቹ ጋር ተሰናስለው ከቀረቡት መካከል ..የሥራ ሱሰኝነት.. የሚለውን ላቅምሳችሁ፡፡ በአሁኑ ዘመን አማካዩ የሥራ ሰዓት በሳምንት 35 ሰዓታት መሆኑን የሚጠቁመው መመሪያው፤ በሳምንት 40 ሰዓት ከሰራችሁ ለመኖር ያህል በቂ ነው ይለናል፡፡ በአሜሪካ አንድ አማካይ ሚሊዬነር በሳምንት ለ59 ሰዓታት የሚሰራ ሲሆን አንዳንዶቹ ግን 70 እና 80 ሰዓታት ይሰራሉ ይላል - የስኬት መመሪያው፡፡ በጥረትና በትጋት የከበሩ ሰዎች ሲሰሩ ለነገ አይሉም የሚለው መመሪያው፤ ሚሊዬነር ለመሆን ከተለመደው የሥራ ሰዓት በላይ ለመስራት አታቅማሙ ሲል የስኬታማ ሰዎችን ተመክሮ እማኝ አድርጐ ያቀርባል፡፡ እኔ ደግሞ ብልግናን የምትሹ ከሆነ ከበለፀጉት ተማሩ እላለሁ፡፡ በነገራችን ላይ ..ታላላቅ ህልሞች.. በዚሁ ጋዜጣ ላይ በሚታወቁ ፀሃፍትና አምደኞች የተሰናዳ መሃፍ ሲሆን በ20 ብር በመሸጥ ላይ ይገኛል፡፡ ለስኬት ያነሳሳልና እንድታነቡት ተጋብዛችኋል፡፡

 

Read 7311 times Last modified on Saturday, 06 August 2011 15:58