Saturday, 06 August 2011 16:00

=ፖለቲካና የደራሲ ፖለቲከኞች

Written by  ዓለማየሁ ገላጋይalemayehugelagay@yahoo.com
Rate this item
(0 votes)

..ደበበ ሠይፉ ሚያዝያ 16 ቀን 1992 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞት ሲለይ . . . ከፖለቲካ ያገኛቸው ክብር፣ ተሰሚነት፣ ገላጭነት፣ ግርማ ሞገስ፣ ተከባሪነት. . . ከትከሻው ላይ በረው ጠፍተው ነበር፡፡ የትኛው ባለጊዜ ደራሲ ላይ አርፈው ይሆን?..
ይሄ አንቀጽ ያለፈው ሳምንት ጽሑፌ መዝጊያ ነበር፡፡ ዛሬ ደግሞ ለመክፈቻነት ተጠቀምኩበት፡፡ ደበበ ሠይፉ በፖለቲካ ..ጉብዝናው.. ወራት የሰበሰበው ይሄ ..ሐብት.. የፖለቲካውን እርጅናና ሞት ተከትሎ የትም ተበትኖ አልቀረም፡፡ ወራሽ አግኝቷል፡፡ ደራሲ ተስፋዬ ገብረአብ፡፡

ተስፋዬ ገብረአብ እንደጠቢቡ ሰሎሞን ..በልጅነቱ.. አንጋፋው ፕሬስ ድርጅት ላይ ሲነግስ አንቀጥቅጥ ግርማ እንደነበረው ከራሱ መጽሐፍ (..የጋዜጠኛው ማስታወሻ..) ገለጻ መረዳት እንችላለን፡፡ እንደመወራጨት ባለ የዶሮ ስልት ብዙ ጋዜጠኞችን በየአቅጣጫው እንደተበተነ በየኋላ ፀፀት ጽፏል፡፡ ወደ ፖለቲካው ዓለም የገባው ጋዜጠኝነትን በማሰስ ነበር፡፡ ሐሰሳ ጋዜጠኝነቱ አልሳካ ቢለው የጋዜጠኝነት ..የስርቆሽ በር.. በመሰለው ውትድርና በኩል ገባ፡፡ በሚገርም ጠመዝማዛ የጓሮ መንገድ አልፎ ህልሙ የሆነውን የጋዜጠኝነት ..ቤተ መንግሥት.. ተቆጣጠረ - 1983 ዓ.ም. የደበበ ሰይፉ ..ሐብት.. እንዳለ ገባለት፡፡
ተስፋዬ ገብረአብ በብዕረ-ርቱዕነት ይታወቃል፡፡ በ..ያልተመለሰው ባቡር.. ቀድሶ በ..ደራሲው ማስታወሻ.. (ለጊዜው) እስኪያሳርግ ድረስ ይሄ ..ብዕረ-ርቱዕነቱ.. አልዋዠቀም፡፡ አስር ጊዜ እየዋዠቀ የሚያስቸግረው ፖለቲካዊ አቋሙ ነው፡፡ ለአስር ጌታ ለመገዛት የሚያስችል ደንዳና ጫንቃ ሰጥቶታል፡፡ እንደ ስልጡን የጋሪ ፈረስ የጌታው የአለንጋ ጥላ ካላረፈበት ብዕሩ አይሰግርም፡፡ በ1982 ዓ.ም. ከደርግ ጋር ሆኖ ኢህአዴግን ወጋ፣ በዚያው ዓመት ከኢህአዴግ ጋር ሆኖ ደርግን ወጋ፣ በ1983 ዓ.ም. ከኢህአዴግ ጋር ሆኖ ተቃዋሚዎችን ወጋ፣ በ1993 ዓ.ም. ከተቃዋሚዎች ጋር ሆኖ ኢህአዴግን ወጋ፣ ከ1999 ዓ.ም. ወዲህ ደግሞ ከሻዕቢያ ጋር ሆኖ ኢህአዴግንና አንዳንድ ተቃዋሚዎችን በመውጋት ላይ ይገኛል፡፡
ተስፋዬ ገብረአብ እንደ ጥቢኛ ከመገላበጥ መብሰል ይገኛል ብሎ የሚያምን ደራሲ ነው፡፡ ከፖለቲካ መሰዊያ ላይ የማይጠፋው ብዕሩ ደምም ቢሆን ከመገበር ወደ ኋላ እንደማይል በተደጋጋሚ ታይቷል፡፡ ካንዴም ሁለቴና ሦስቴ አገርና ህዝብ መካከል ብዕሩን በክተት ለማማሰል ሞክሮ አልተሳካለትም፡፡ ..የቡርቃ ዝምታ.. የተሰኘ ልቦለዱ አንዱ የከሸፈ ማማሰያው ነው፡፡ ይሄንን የፈናጅር ታሪክ በኮኮቦች ገትተን ወደቀጣዮቹ ደራሲዎች እንተላለፍ፡፡
* * *
ጣሊያን እንደሴጣን ካሳታቸው ደራሲዎች መካከል ብላታ ወልደጊዮርጊስ ወልደዮሐንስ አንዱ ናቸው፡፡ ..አግአዚ.. በተሰኘ ልቦለዳቸው ይታወቁ እንጂ ከ18 በላይ መጻህፍትን ጽፈዋል፡፡ እንደ ደረመን ሆኖ እርፍት የነሳቸውን የጣሊያን ጊዜ ተግባራቸውን ለማስታገስ ይመስላል ብዙዎቹ ሥራዎቻቸው ከአገርና ከሕዝብ ፍቅር ጋር የተያያዙ ናቸው፡፡ የጥቂቶቹን መጻሕፍት ርዕሶች ብቻ እንመልከት፡፡ ..የወንድ ልጅ ኩራት፣ ለሀገር መሞት..፣ ..ታሪክና ሥራ..፣ ..ሥነ-ምግባር..# ..ታሪክና ስም እስከ ዘለዓለም..፣ ..አግአዚ (ነጻ አውጪ). . ...    
ብላታ ወልደጊዮርጊስ ወደ ፖለቲካው የተቀላቀሉት ገና ልጅ ሳሉ በ1913 ዓ.ም. ነው፡፡ ጎንደር ውስጥ ብላታን ያስተምሩ የነበሩት አለቃ ኃይሉ ይዘዋቸው አዲስ አበባ በመምጣት በላይኛው ቤተ መንግሥት (አሁን አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በሆነው) ሥራ አሰጧቸው፡፡ ሥራቸው የግዕዝን መዛግብት ወደ አማርኛ መመለስ ነበር፡፡ የሥራቸውን ጥራት ያዩት ራስ ተፈሪ በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት የመጽሐፍና የጋዜጣ አራሚ ሆነው እንዲሠሩ አስቀጠሯቸው፡፡ ከ1919 ዓ.ም. ጀምሮ በጡረታ እስኪወጡ ድረስ ከጽሑፍ ጋር የተገናኘ ሥራ ሲሠሩ ቆዩ፡፡ ሥልጣናቸውም በማስታወቂያ ሚኒስቴር ረዳት ሚኒስትር ድረስ አሻቅቧል፡፡
ብላታ ወልደጊዮርጊስ ጣሊያን ሲጠናወታቸው በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት በአራሚነት እየሠሩ ነበር፡፡ ከነ ከበደ ሚካኤል ጋር ተቀላቅለው ..የቄሳር መልዕክተኛን.. እንዲያዘጋጁ ተመደቡ፡፡ ብላታ ወልደጊዮርጊስ ለጣሊያን ካደሩት ሐበሾች በላይ ትጋትና ጥረት በማሳየት በሮማው ገዢ ፊት ግርማ ለማግኘት ሞክረዋል፡፡ ..ዱቼ ሙሶሎኒ ሺህ ዓመት ንገስ! ዘር ማንዘርና ኢትዮጵያን ይግዛ!.. በሚል የጋዜጣ ላይ መፈክራቸው ይታወቃሉ፡፡ ይሁንና ያሉት ሳይዝላቸው ቀርቶ ሺው በአምስት ዓመት ተመንዝሮ አከሰራቸው፡፡ ከስረው አልቀሩም ለአፄ ኃይለ ሥላሴ ያዘጋጁት ..መፈክር.. ያዘላቸው፡፡ ..ሥነ ምግባር.. መጽሐፋቸው ላይ ..ግርማዊ ሆይ.. በሚል ርዕስ ያሰፈሩት ጽሑፍ እንዲህ የሚል አንቀጽ አለበት፡፡
..ቀዳሚሃ ለጥበብ ፈሪሃ ለእግዚአብሔር የተባለውን ቃል ቀዳሚ አድርጐ በሱ መሠረትነት ቀዳሚሃ ለፍቅር ሕይወት ንጉሥ ወሀገር፤ ተከታይ መሆኑን በማወቅ ህዝብና ህዝብ በሰላም እንዲኖር. . . (ተማሪዎች) ወገናቸው ወይም አገራቸው ከፈተና ላይ በወደቀ ጊዜ ፈተናውን ሁሉ አልፈው ባገኙት ሙያ ለሀገራቸውና ለንጉሠ ነገሥታቸው ሲሉ በፈተናው ገብተው በሥጋዊ አርበኝነታቸው ላይ መንፈሳዊ አርበኝነት ጨምረው. . ...
..ብዕረ-ቀላጤዎች.. ለስህተታቸው ማረሚያ ገዢዎች እግር ስር የሚጐዘጉዙት ሕዝቡን ነው፡፡ ስህተት ማረሚያ ብቻ ሳይሆን ሥልጣን ማጠበቂያ ማገር ከማድረግ ወደ ኋላ አይሉም፡፡ ብላታ ወልደጊዮርጊስ እንደ ከበደ ሚካኤል ሁሉ በሥነ-ምግባር ስም የበደሉትን ገዢ ለመካስ ሲጣጣሩ ኖረዋል፡፡ ታማኝነታቸውን የማስመስከር ብርቱ ፍላጐታቸው ጉልበት ሆኗቸው ብዙ መጻሕፍትን አምርተዋል፡፡
ኢትዮጵያ የተገለባባጭ ደራሲ ደሃ አይደለችም፡፡ ከጥቂቶቹ በስተቀር አብዛኞቹ ጉልበታም የፖለቲካ ወጀብ የሚያስጐነብሳቸው መንፈሰ ድውያን ናቸው፡፡ እንደ አፈወርቅ ገብረኢየሱስ፣ ከበደ ሚካኤል፣ ወልደጊዮርጊስ ወልደዮሐንስና ተስፋዬ ገብረአብ ሁሉ የአደባባይ ተገለባባጭ ደራሲዎች አሉን፡፡ መገልበጣቸውን ልብ ሳንለው ድንገት ተለውጠውና ተመሳስለው የሚቀጥሉ ..ፎርመኛ.. ደራሲዎችም አሉን፡፡ በዓሉ ግርማ፣ ብርሃኑ ዘሪሁን፣ ፀጋዬ ገብረመድህን. . .
እንደ በዓሉ ግርማና እንደ ብርሃኑ ዘሪሁን ሁሉ ፀጋዬ ገ/መድህን የአፄው ዘመን ደራሲ ነበር፡፡ የቀዳሚው ኃይለ ሥላሴ ሽልማት ድርጅት ተሸላሚ ሲሆን እርሳቸው ንጉሱ የማበረታቻ ቃል ሰጥተውት ነበር፡፡ ... . .በርታ፤ ይህ የመጀመሪያህ እንጂ የመጨረሻህ አይደለም. . ... ብለውት እንደነበር ..የሾህ አክሊል.. የተሰኘው ተውኔቱ በመሐፍ ሲታተም (በ1952 ዓ.ም.) ከነፍቶግራፉ አስገብቶታል፡፡ የተ ጋ ሸርተት እንዳለ በውል አይታወቅም፡፡ በ1967 ዓ.ም. ..ሀ ሁ በስድስት ወር..ን በመጽሐፍ ሲያሳትም በንጉሡ አስተዳደር ላይ መረር ያለ አስተያየቱን ጠቆም ያደርገናል፡፡
..በትሁት አስተያየቴ ቀድሞ ከነበረው የሕዝባዊ የፖለቲካ ሞት ወደ ሥርየት፤ ከሲቃ ወደ ትንሳኤ፤ ከቅዠት ወደ እውነት የምናንሰራራበት የተስፋ ..ሀ ሁ.. ስለመሰለኝ (ጻፍኩት) ሀሁ በስድስት ወር በዚያው ሳምንት ውስጥ በአጣዳፊ ተጀምሮ በአሥራ ሦስት ቀን በአጣዳፊ ተደረሰ፡፡ ሀሁ ቀዝቅዘው የከረሙ ሌሎች መድረኮች ላይ ማንቃቱንም በፍስሃ አሳየን..
ፀጋዬን ሸርተት ያደረገችው የዘመን ድጥ እዚህ ላይ ተፈጻሚ ሆናለች ማለት ነው፡፡ በዚያው ዘመን የጻፈውንና ያስመደረከውን ..እናት ዓለም ጠኑ.. እንዴት እንደደረሰው ደግሞ እንዲህ YlÂL:-  
..እንደ ሀሁ (በስድስት ወር) በአጣዳፊ ሳይሆን የአብዮቱን ፈለግ ለማጤን ስንልና ጊዜያዊ ትርጉም ለማስገኘት ስንል ይህን ቴአትር ከመተርጐም ወደ ማዳቀል ከዚያም ጠቅላላውን ድርሰት አካቶ እንደገና በመድረስ ረዘም ያለ ጊዜ ወስደናል. . . በአጭሩ እናት ዓለም ጠኑ በችግር የተዋረዱ ፍጡራን የቱን ያህል ውሾች እንደሚሆኑ ይነግራል፡፡ ስለዚህ ያስቆጣል፡፡ ስለዚህ አብዮትን ይጠራል፡፡..
አብዮቱ ተጠርቶ ካለቀ በኋላ በ1967 ዓ.ም. ነው የፀጋዬ ድርሰት አብዮት የሚጠራው ያም ሆነ ይህ የአጥቢያ ጥሪው ከመባቻውና ከዋዜማው የአብዮት ጥሪዎች ጋር ተደበላልቆ ለመለየት በማደናገሩ የቀደምት ለውጥ ፈላጊ ፋኖዎችን ጎራ ለመቀላቀል ችሏል፡፡ ፀጋዬ የሚፈልገውን የባህልና ማስታወቂያ ..ግዛት.. ይዞ ..መድረክ በጁ፣ መድረክ በደጁ.. በመሆን የፀሐፌ ተውኔት ድቅ ወርሷል፡፡ የብሔራዊ ቴአትር ሥራ አስኪያጅ በነበረበት ዘመን ተዋናዮች በውስጠ - ደንብ የማይጋፉት ቢሆንባቸው ሰላማዊ ሠልፍ ወጥተዋል፡፡ ይሄንን ሁኔታ ፀጋዬ ..የሁለተኛው አብዮት.. መንሸራተቻ ጥ አድርጐ በ1984 ዓ.ም ተጠቅሞበታል፡፡
..በደርግ ቅስቀሳ የቴአትር ሙያተኞች ያኔ እንዲሰለፍብኝ ሲደረግ በብሔራዊ ቴአትር በኩል የቴአትር ጥበብ እየመጠቀ፣ ከፍ እያለ የሄደበት ጊዜ መሆኑ ነበር፡፡ ያንን ለመቅጨት፤ ተዋንያኑን ወስደው አሠሩና ካድሬ አደረጓቸው፡፡ ካድሬ ሲሆኑ ነገሡ፡፡ ያ ሁሉ በአንድ ባለቅኔ ህይወት ውስጥ አሰቃቂ ትዝታ ነው፡፡.. (..ሕሊና.. ቅ 1 ቁ.1 ነሐሴ 1984 ዓ.ም)
ከደርግ ጀንበር መጥለቅ ማግስት ሥርዓቱን የሚያሳጣ መረጃ ለማቀበል መሞከር ከምን ፍላጐት እንደመነጨ ለመተንበይ አያዳግትም፡፡ ፀጋዬ በዚህ መሔት ላይ ደርግ ያደረሰበትን በደል ዘርዝሮ የአለፈው የደርግ ሥርዓት ተጐጂ መሆኑን ለማሳየት ብዙ ጥሯል፡፡
... . . ..የጋሞ ቲያትር.. የዛሬ ስምንት አመት ሲታይ የደርግ መንግሥት በጣም ተቆጣ፡፡ በአሣር ነው ያመለጥኩት፡፡ እንዲያውም ለወዳጄ ለፕሬዚዳንት ሴንጐር ቴሌግራም ልኬ ብዙ ጊዜ እሳቸው ስለእኔ ጣልቃ እየገቡልኝ ለአምነስቲ ኢንተርናሽናል ምር ፈው ነው የዳንኩት፡፡ ከዚያ በፊትም ..በአቡጊዳ.. ቴአትርም የተነሣ ታስሬ ነበር፡፡ ..የአቡጊዳን.. ቴአትር ደርግ ፈሞ አልወደደውም፡፡ በዚህ የተነሣ እስር ቤት ስገባ የአፍሪካ ጠቢባን ወዳጆቼ ሕይወቴን ያተረፉት ባደረጉት የአቤቱታ መረባረብ ነው፡፡ ስለዚህ ደርግም እጁን ለዘብ አረገው እንጂ እስር ቤት ሳለሁ እስከ ማጥፋትም ድረስ አስቦ ነበር፡፡.. ፀጋዬ ገብረመድህን ከሸርታታ መግለጫዎቹ ባሻገር ሸርታታ የጥበብ ሥራዎችንም በዚያው ዘመን ጀባ ብሎን ነበር - ..ሀሁ ወይም ፐፑ..
..ሀሁ ወይም ፐፑ.. እንደመጀመሪያው አብዮት ማጠናከሪያ ..ሀሁ . . .በስድስት ወር.. ሁሉ አላማው የዘመኑን ..አፋፍነት.. መለፈፍ ነው፡፡ ታጋይ ነጋ 18ቱን የደርግ ክፉ የፈተና አመታት በመስቀል ተቸንክሮ ያሳየናል፡፡ በአካል ብቻ ሳይበቃ ..ወህኒ ነው እንጂ መድረክማ ላይ የአባቴ ሀሁ ከተጨለመ ቆየ፡፡ 18 ዓመቱ፡፡.. ይለናል፡፡ ታጋይ ነጋን ሆኖ የመጣው የ ..ሀሁ በስድስት ወር.. ስሙ ንጉሥ ጣሴ ነው፡፡ ይሄ ምንን ያመለክታል?
ያም ሆነ ይህ የ1983ቱ የሁለተኛው አብዮት ሙከራ እንደ መጀመሪያው የደርግ አብዮት ለፀጋዬ ውጤት አላስገኘም፡፡ በጡረታ ሰበብ ከሥራ እንዲገለል ተደረገ፡፡ መድረክ እንደ ሰማይ ራቀች፡፡ እራሱ ፀጋዬ እንደሚናገረው አሳብሮ መድረክ ለማግኘት አማተሮችን በማሰባሰብ ..ሀሁ ወይም ፐፑ..ን ለማሳየት ቢሞከርም አዋሳ ላይ ..የወያኔ ካድሬዎች ጥይት ተኩሰው ሕዝብ መካከል መድረክ ላይ ወጥተው ወጣት ተዋንያኑን በዱላ፣ በቆንጨራና በሰይፍ የደበደቧቸው.. ይላል፡፡ (..ጦቢያ.. ሚያዝያ 1996) መድረክ ለፀጋዬ አንዱ የመገናኛ መሣሪያ ብቻ አይደለም፡፡ ሁለመናው ከመድረክ ጋር የተቆራኘ ነው፡፡ ለሥራዎቹ ብቻ ሳይሆን ለህይወቱም አስፈላጊ ነገር እንደሆነ ማሰብ ይቻላል፡፡ ከመድረክ የተናጠበው ኑሮው በንዴት፣ bBST# በተስፋ መቁረጥ፣ በጥላቻ . . . ቢሞላና ጤናው ቢቃወስ አይገርምም፡፡ ከዚህ ሁሉ በኋላ የተከተለው እንደ ጦር የሚፈራው ስደት ብቻ ሆነ፡፡ በደህናው ጊዜ ከኢትዮጵያ W የሥራ ምደባ መጥቶ ቢጠየቅ ..ከሀገሬ መሄድ ሥሩ እንደተነቀለ ዛፍ ዓይነት ስሜት ይፈጥርብኛል.. በማለት እንቢታውን ገልፆ ነበር፡፡ በስተመጨረሻ ግን ሆነ፡፡ የመጨረሻው መጨረሻ እንደ ደበበ ሠይፉ ሁሉ በሞት ሲለየን ከፖለቲካ ያገኛቸው ክብር፣ ተሰሚነት፣ gúnT# ግርማ ሞገስ፣ ተከባሪነት . . . ከሱ ጋር ከሀገር ተሰደው በባዕድ አገር ተወስነው ነበር፡፡ የፀጋዬ መርዶና ቀብሩ የልፋቱን ያህል ደምቆና ከብዶ አለመታየቱ የ..የአደራ በላተኝነት.. ስሜት ሳይፈጥርብን አልቀረም፡፡ ነገር ግን ፖለቲካና የደራሲ ፖለቲከኞች መጨረሻ እንዲያ ነው - ምን ማድረግ ይቻላል???

Read 4616 times Last modified on Saturday, 06 August 2011 16:05