Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Monday, 08 August 2011 09:30

ሻጊ የሬጌ ሙዚቃ ገበያ እንደሌለው ገለፀ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ሻጊ የሬጌ ሙዚቃ የዓለም የሙዚቃ  ገበያን ሰብሮ ለመግባት አልቻለም ሲል ተናገረ፡፡ ..ሰመር ኪንግስተን.. የተባለ አዲስ የሙዚቃ አልበሙን ከወር በፊት ለገበያ ያበቃው ሻጊ፤ ለሬጌ የሙዚቃ አልበሞች ገቢ ማነስ የስፖንሰሮች እጥረት ዋንኛው ምክንያት መሆኑን ለኤምቲቪ ኒውስ ተናግሯል፡፡

ያለፉትን 20 ዓመታት በሙዚቃ ሥራ ያሳለፈው እና በሙሉ ስሙ ኦሪቪል ሪቻርድ ቢሬል ተብሎ የሚታወቀው ሻጊ፤ ያሳተማቸው የአልበም ስራዎች 10 ሚሊዮን ቅጂ በዓለም ዙሪያ ተሸጠውለታል፡፡ ኮኮኮላ፣ ኖኪያ እና ብላክ ቤሪ የመሳሰሉ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች የሬጌ ሙዚቃ አልበሞችን ስፖንሰር አያደርጉም ያለው ሻጊ፤ በሙዚቃ ዘርፉ ያሉ አርቲስቶች በግጥም ስራዎቻቸው ስብከት ማብዛታቸው ገበያቸው እንዳይሟሟቅ ተጽእኖ መፍጠሩንም ጨምሮ ገልጿል፡፡

Read 5610 times