ጋዜጠኛ መሐመድ ሰልማን በማህበራዊ አምድ ስር በ..አዲስ ነገር.. ጋዜጣና ድረ-ገጽ ላይ ተነባቢ የነበሩ ከ15 በላይ ጽሁፎችን አሰባስቦ ነው ለንባብ ያቀረበው፡፡ ..ማሕሙድ ጋ ጠብቂኝ.. የተሰኘው ተራኪ ወግ የአዲስ አበባዋን ፒያሳ ህይወትና ገጽታ የሚያስቃኝ ጽሁፍ ሲሆን ከዚህ ቀደም በሸገር ሬድዮና በቪኦኤ በከፊል የቀረበ ስራ ነው፡፡ ..ማሕሙድ ጋ ጠብቂኝ.. መጽሐፍ የተዘጋጀው በአሮን አሳታሚ እንደሆነ ታውቋል፡፡