Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Monday, 08 August 2011 09:53

የ2003 የሩጫና እግር ኳስ ድሎች መታሰቢያነት ለአሰፋ ጐሳዬ ሆነ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

addis admassበ1ኛው የሚዲያና የኪነጥበብ ባለሙያዎች የእግር ኳስ ውድድር አዲስ አድማስ ከኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዚን ድርጅት ጋር ለዋንጫ ተጋጥሞ 1ለ0 በማሸነፍ ሻምፒዮን ሆነ፡፡ የአዲስ አድማስ ቡድን ተጨዋቾች የዋንጫው መታሰቢያነት ለአሰፋ ጐሳዬ ይሁን ብለዋል፡፡ አዲስ አድማስ በዚሁ ዓመት በታላቁ ሩጫ ተዘጋጅቶ በነበረው የ12 ኪሎሜትር የዱላ ቅብብል ሩጫ ከስምንት ሚዲያዎች መካከል አሸናፊ እንደነበር ሲታወስ፤ በ2003 በሩጫና በእግር ኳስ ከአገሪቱ ሚዲያዎች የላቀ ውጤት በማስመዝገብ አድናቆት አትርፏል፡፡

ከላይ ብርቱካናማ ቀለም ያለው ሹራብና ጥቁር ቁምጣ የታጠቀው የአዲስ አድማስ ቡድን በውድድር ላይ በተሟሟቀ ዝግጅት፤ በማራኪ የድጋፍ አሰጣጥና በአስገራሚ የተሳትፎ ትኩረት ውድድሩን ካዘጋጀው አካል አድናቆት አግኝቷል፡፡
በእግር ኳስ ውድድሩ ሻምፒዮና የሆነው የአዲስ አድማስ ቡድን ልዩ ዋንጫ፤ የአምስት ሺህ ብር ሽልማትና የወርቅ ሜዳልያ አግኝቷል፡፡ በ2ኛ ደረጃ ያጠናቀቀው የኢትዮጵያ ሬድዮና ቴሌቭዠን ድርጅት 3ሺ ብርና የብር ሜዳልያ እንዲሁም ሶስተኛ ደረጃ ያገኘው የ2003 ጋዜጠኞች ቡድን የ2ሺ ብርና የነሀስ ሜዳልያ ተሸላሚ ሆነዋል፡፡ የአዲስ አድማስ ቡድን  እስከ ዋንጫ ድሉ ባደረገው ግስጋሴ ሽንፈት አላስተናገደም፡፡ በእግር ኳስ ውድድሩ በአጠቃላይ 6 ጨዋታዎች አድርጐ 5 ሲያሸንፍ አንድ አቻ ተለያይቷል፡፡ በተጋጣሚዎቹ ላይ 21 ጐል አስመዝግቦ 4 ብቻ ተቆጥሮበታል፡፡
በውድድሩ የመክፈቻ ጨዋታ ከሪፖርተር ጋር የተገናኘው የአዲስ አድማስ ቡድን 11 ለ1 በሆነ ሰፊ ውጤት ቢያሸንፍም በተጨዋች ተገቢነት በሪፖርተር በቀረበ ክስ ጨዋታው ተደግሟል፡፡ ከዚያም በምድቡ ሁለተኛ ጨዋታውን ከአዲስ አበባ መገናኛ ብዙሐን ጋር አድርጐ አዲስ አድማስ 2ለ0 አሸንፏል፡፡  በአዘጋጆቹ ውሳኔ በድጋሚ በተደረገ ጨዋታ ደግሞ ሪፖርተርን 2ለ1 ማሸነፍ የቻለ ሲሆን የመጨረሻ የምድብ ጨዋታውን ከኢትዮጵያ ሬድዮና ቴሌቭዠን ድርጅት ጋር በማድረግ 2 እኩል አቻ ተለያይቷል፡፡ የአዲስ አድማስ ቡድን በነበረበት ምድብ በ7 ነጥብ በኢሬቴድ በግብ ክፍያ ተበልጦ 2ኛ ደረጃ በመያዝ ግማሽ ፍጻሜ ገባ፡፡ በግማሽ ፍጻሜው ከአርቲስቶች ቡድን ጋር የተገናኘው ቡድኑ በፍፁም የጨዋታ ብልጫ 3ለ0 በማሸነፍ ለፍፃሜው ጨዋታ ደርሷል፡፡ በፍፃሜው ጨዋታ አዲስ አድማስ ከኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዚን ድርጅት ለዋንጫ የተፋለመ ሲሆን በአስደናቂ ብቃት 1ለ0 በማሸነፍ የአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽን ከዜድኬ ፕሮሞሽን ጋር በመተባበር ያዘጋጀውን 1ኛው የሚዲያና የኪነጥበብ ባለሙያዎች የእግር ኳስ ውድድር በሻምፒዮናነት  አጠናቅቋል””

 

Read 5400 times Last modified on Tuesday, 09 August 2011 02:37