Saturday, 13 August 2011 09:07

አምስቱ ምርጥ የአይዶል ተወዳዳሪዎች የፊታችን ቅዳሜ ይለያሉ

Written by  መታሰቢያ ካሳዬ
Rate this item
(1 Vote)

ከሁለት ዓመት በፊት በተጀመረውና ሊጠናቀቅ በተቃረበው የኢትዮጵያን አይዶል ውድድር ለአምስቱ ምርጥ ተፎካካሪዎች የሚደረገው ውድድር ይካሄዳል፡፡ ውድድሩ ከፍተኛ ፉክክር የሚታይበት ሊሆን እንደሚችል ተገምቷል፡፡በአስሩ የኢትዮጵያን አይዶል ምርጦች መካከል የሚካሄደው ውድድር አምስቱን ምርጦች ለመለየት የሚያስችልና ከፍተኛ ፉክክር የሚጠበቅበት እንደሆነ የኢትዮጵያን አይዶል ፕሮግራም አዘጋጅና የአይ ጂ ኢንተርቴይመንት ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ይስሐቅ ጌቱ ለአዲስ አድማስ ገልዋል፡፡

ከምርጥ አስር ድምፃውያንና ከምርጥ 10 የዘመናዊና ባህላዊ ውዝዋዜ ባለተሰጥኦዎች ውስጥ ምርጥ አምስቱን ለመለየት በሚካሄደው ውድድር ላይ ቀድሞ ከነበሩት ዳኞች በተጨማሪ ሌሎች ዳኞችም እንደሚገኙበት አቶ ይስሐቅ ተናግረዋል፡፡
በዘንድሮው ውድድር ከ1-3 የሚወጡ አሸናፊዎች የተለያዩ ሽልማቶች እንደሚበረከቱላቸው የተናገሩት አቶ ይስሐቅ፤ የሽልማቶቹን ዓይነት ለመናገር ገና ተወስኖ አላለቀም ብለዋል፡፡ ሆኖም እንደከዚህ ቀደሙ የአይዶል ውድድር የመኪና ሽልማት ሊሆን ይችላል የሚል ግምት እንደሌላቸውና በመኪኖች ዋጋ ንረት የተነሳ ይህን ማድረግ እንደማይችሉ ገልፀዋል፡፡
ከ1ኛ-3ኛ የሚወጡ አሸናፊዎች የየራሳቸው አልበም ለማውጣት እንዲችሉ እንደሚያደርግና አስሮቹ ምርጦችም በጋራ አንድ አልበም እንደሚያሳትሙ የተናገሩት አቶ ይስሐቅ፤ ከዚህ ቀደም በሽልማት መዘግየት የሚመጡ ቅሬታዎች በዚህ ውድድር ተግባራዊ እንደማይሆኑና አሸናፊዎች ሽልማቶቻቸውን በወቅቱ እንደሚቀበሉ ጨምረው ገልዋል፡፡
አስሩ የአይዶል ምርጥ ተወዳዳሪዎች ወደ አምስቱ ምርጦች ዙር ለማለፍና በውድድሩ አሸናፊ ለመሆን ከፍተኛ ትንቅንቅ ይዘዋል፡፡ ከተወዳዳሪዎች መሃል በቴዎድሮስ ታደሰና በመሀሙድ አህመድ ዘፈኖች ውድድሮቹን ሲያካሂድ የቆየው ዮናስ ግዛው ለአምስተኛው ዙር ውድድር የማዲንጐ አፈወርቅን ..ማህሌት.. የመረጠ ሲሆን የባህርዳሩ ይርጋ ሁናቸውና የደብረ ማርቆሱ ጳውሎስ ምህረቴ የቴዎድሮስ ታደሰን ..አሳው ተከማችቶ.. የተሰኘ ዜማ ለውድድራቸው መርጠዋል፡፡ የአዲስ አበባው ተወዳዳሪ ዮሐንስ ግርማ በወንድሙ ጅራ ..ውቢት.. ዜማ ውድድሩን የሚያካሂድ ሲሆን በእንግሊዝኛ ዘፈኖች ውድድሯን ታካሂድ የነበረችው ዮሐና በላይ የግርማ በየነን ..መጀመሪያ አንቺን ሳገኝ ተሳስቼ.. የሚለውን ቀደም ያለ ዜማ ለውድድር መርጣዋለች፡፡ የደሴው ተወዳዳሪ ሀሰን አራጋው በጥላሁን ገሰሰ ..ናፍቆቷ ነው ያስቸገረኝ.. ዜማ ውድድሩን ያካሂዳል፡፡ የአዲስ አበባው ይድነቃቸው ገለታ በጥላሁን ገሰሰ ..ስንታየሁ መሰሪ.. ዜማ፣ የመቀሌ ውቅሮው ተወዳዳሪ ዳዊት ዓለማየሁ በሙሉቀን መለሰ ..እኔስ ተሳስቼ.. ዜማ እንዲሁም የከሚሴው ተወዳዳሪ ተመስገን ታፈሰ በጥላሁን ገሰሰ ..የደም ገንቦ.. ዜማና የባህር ዳሩ ማስተዋል እያዩ በቀደምት የጥላሁን ዜማ ..የጠላሽ ይጠላ.. ውድድራቸውን ያደርጋሉ፡፡  
ውድድርን አስመልክቶ አስተያየታቸውን ከሰጡን ሙያተኞች መካከል የኪቦርድ ተጫዋቹ ሰለሞን ተክኤ፤ አብዛኛዎቹ ተወዳዳሪዎች የሚገርም ችሎታ እንዳላቸው ጠቁሞ በእሳት የተፈተኑ ወርቆች ናቸው ብሏል፡፡ ከሦስተኛው ዙር ጀምሮ ተወዳዳሪዎቹን በኪቦርድ እያጀበ የዘለቀው ሰለሞን፤ አብዛኛው ታዋቂ ድምፃውያን በመድረክ ላይ ሥራዎቻቸውን ሲያቀርቡ የሚያጋጥማቸው ከሪትም የመውጣትና መሰል ችግሮች በእነዚህ ልጆች ላይ አለመስተዋሉንና ከባድ አሬንጅመንት ያሏቸውን ሙዚቃዎች ለውድድሩ ቢመርጡም ያለ አንዳች ችግር ለመወጣት የቻሉ ብዙ ተስፋ የሚጣልባቸው ልጆች ናቸው ሲል ተናግ…L””በዳኝነቱ ሥራ ለወራት ከተወዳዳሪዎቹ ጋር የዘለቁት ቴዲ ማክና የሺ ደመላሽም በተወዳዳሪዎቹ  ብቃት ተደንቀዋል፡፡ ከተወዳዳሪዎቹ ብዙ መጠበቅ አይገባም ያለው ቴዲ፤ ልጆቹ ወደ ውድድሩ ሲመጡ ይዘውት የመጡት ሞራላቸውን ብቻ ነው፡፡ ይህን መንገድ ተከትሎ መስመር የማስያዙ ተግባር እንግዲህ የሁላችንም ነው ብሏል፡፡ በዳኝነቱ ሥራ ላይ የተሳተፈችው የሺ ደመላሽም ውደድሩ አቅም ያላቸውን ልጆች ለሙዚቃ ኢንዱስትሪ በማበርከቱ ረገድ ትልቅ ሚና እንደሚኖረው ገልፃለች፡፡

 

Read 4273 times Last modified on Saturday, 13 August 2011 15:34