Saturday, 13 August 2011 09:54

የአደንዛዥ እጽ ጦርነት በሜክሲኮ

Written by  ጥላሁን አክሊሉ
Rate this item
(0 votes)

በዓለማችን የአደንዛዥ ዕጽን በከፍተኛ ደረጃ በማምረት የሚታወቁት የደቡብ አሜሪካ አገሮች ሲሆኑ፣ በተመሳሳይ አደንዛዥ እጽን በሕገወጥ መንገድ፣ ወደተለያዩ የዓለም ክፍሎችበማስገባትም ይጠቀሳሉ፡፡ አደንዛዥ እጽን በመነገድ የሚታወቁት ግለሰቦችም የናጠጡ ከበርቴዎች ናቸው፡፡ የተለያዩ መንግስታት አደንዛዥ እጽ ወደ አገራቸው እንዳይገባ በማገድና ጥብቅ ቁጥጥር በማድረግ ጥረት ቢያደርጉም በየትኛውም አገር በድብቅ መግባቱ አልቀረም፡፡ ኒውስዊክ መጽሔት ስለዚህ ጉዳይ ሲገልጽ፤ ..የተለያዩ መንግስታት በሕገወጥ መንገድ የሚገቡትን አደንዛዥ እጽ ለመቆጣጠር ከአቅም በላይ ሆኖባቸዋል.. ብሏል፡፡ የደቡብ አፍሪካው ..ዘ ስታር.. ጋዜጣ በበኩሉ፤ ከደቡብ አሜሪካ ወደ ደቡብ አፍሪካ በሚጓዝ መርከብ ውስጥ 180 ኪሎ ግራም ኮኬይን በ11.600 ጠርሙስ ውስጥ ከወይን ጠጅ ጋር ተደባልቆ ጆሃንስበርግ ሊገባ ሲል በፖሊሶች ጥርጣሬ መያዙን ዘግቧል፡፡

ጋዜጣው  አክሎም በደቡብ አፍሪካ ከአራት ሰዎች ውስጥ አንዱ የአደንዛዥ እጽ ተጠቃሚ ነው ብሏል፡፡
ይሁን እንጂ በዓለም ዙሪያ በሕገወጥ መንገድ ከሚገቡት አደንዛዥ ዕጾች ውስጥ በፖሊሶች የሚያዘው ከ10 እስከ 15 በመቶ ብቻ ሲሆን፣ ከ80 በመቶ በላይ ግን በድብቅ እንደሚገባ ጥናቶች ያስረዳሉ፡፡ በተባበሩት መንግስታት የማህበራዊ እድገት የጥናት ዘርፍ፣ የአደንዛዥ ዕጽ ዝውውርን ለመቆጣጠር አስቸጋሪ የሆነበትን ሁኔታ ሲገልጽ. ..የአደንዛዥ ዕጽ አምራቾችና አዘዋዋሪዎች ራሳቸውን ያደራጁ ከመሆን አልፈው በዓለም አቀፍ ደረጃ ሰፊ መረብ አላቸው፡፡ ከአደንዛዥ ዕ በሚያገኙት ትርፍ ከፍተኛ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ የሚያደርጉ ሲሆን ከኢንቨስትመንት የሚያገኙትን ብር በሕገወጥ መንገድ ወደፈለጉት አገር bኤl¤KTénþKS መሳሪያዎች ያዘዋውራሉ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ባንኮች ምንም እንኳን የገንዘቡን ምንጭ ባያውቁም በአደንዛዥ ዕጽ ሽያጭ የተገኙ ገንዘቦችን በካዝናቸው አጭቀው ይዘዋል፡፡.. ..ዲስከቨሪ.. የተባለ የአሜሪካ መጽሔት ደግሞ ..በርካታ የአሜሪካ ባንኮች ከአደንዛዥ ዕጽ የተገኙ ገንዘቦችን በየጊዜው ይጠቀማሉ.. በማለት ጽፏል፡፡
ወደ አሜሪካና አውሮፓ በሚገቡ አደንዛዥ ዕጾች አዘዋዋሪዎቹ በየዓመቱ በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር ያጋብሳሉ፡፡ አደንዛዥ እጾች አብዛኛውን ጊዜ በድብቅ ይግቡ እንጂ፣ ከአንዳንድ ፖሊሶችና ባለስልጣናት ጋር በመመሳጠርና ለእነርሱ ዳጐስ ያለ ክፍያ በመስጠት የሚገቡበት በርካታ አጋጣሚዎች እንዳሉ ይታወቃል፡፡ በብዙ አገሮች ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ሳይቀሩ ከአደንዛዥ እጽ ጋር በተያያዘ ሙስና ውስጥ ተዘፍቀዋል፡፡
“The Gurdian” የተባለው በእንግሊዝ የሚታተም ታዋቂ ጋዜጣ፣ በብራዚል ያለውን ሁኔታ ሲገል፣ ሶስት የኮንግረስ አባላት፣ አስራ ሁለት የክፍላተ አገር አስተዳዳሪዎች እንዲሁም ሶስት ከንቲባዎችን ስማቸውን በመጥቀስ ከአደንዛዥ እጽ ንግድ ጋር በተያያዘ እጃቸው እንዳለበት ገልጿል፡፡ ጋዜጣው ሲቀጥል ከ800 በላይ የሚሆኑ ሰዎች ደግሞ፣ ከአደንዛዥ ዕጽ ዝውውርና ከተደራጀ የወንጀል ተቋም ጋር ንክኪ ያላቸው ሲሆን፣ ከእነዚህም ውስጥ ፖሊሶች፣ ጠበቆች፣ የንግድ ሰዎችና ዕጽ አምራች ገበሬዎች ይገኙበታል ሲል ዘግቧል፡፡
በብራዚሊያ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ፕሮፌሰር የሆኑ አንድ ግለሰብ ደግሞ ሲናገሩ፤ ..አደንዛዥ ዕጽ በሁሉም ቦታ እየተስፋፋ ነው፤ yxdN²? ዕ በገበያ ውስጥ በገፍ መግባትና ተጠቃሚውም ያን ያህል መጨመሩ ደግሞ ችግሩን ለመቆጣጠር አስቸጋሪ አድርጐታል.. ብለዋል፡፡ ከብራዚል ውጪ በፔሩ፣ በቬኑዙዌላ፣ በቦሊቪያ፣ በኮሎምቢያ፣ በፓራጓይ፣ በኡራጋይና በሜክሲኮ እንደ ኮኬይን፣ ማሪዋና እና ሄሮይን የመሳሰሉ አደገኛ ዕፆች እየተመረቱ በሕገወጥ መንገድ ወደተለያዩ አገሮች ይዘዋወራሉ፡፡ በተለይ በሜክሲኮ የአደንዛዥ እጽ ንግድ የተጧጧፈበትን የአገሪቱን መዲና “Cocaine capital” በሚል ሰፊ ዘገባ ቀርቦበት ነበር፡፡
በሜክሲኮ ከአደንዛዥ እጽ ጋር በተያያዘ እ.ኤ.አ በ2007 ዓ.ም ወደ 2500 ያህል ሰዎች የሞቱ ሲሆን፣ በ2008 ደግሞ ዓ.ም 2000 ሰዎች ተገድለዋል፡፡
በተጨማሪም የአደንዛዥ እጽ አዘዋዋሪዎችን ለመያዝ የተንቀሳቀሱ በርካታ ፖሊሶች፣ ከእጽ አዘዋዋሪዎች በተተኮሰ ጥይት የተገደሉ ሲሆን፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ ደግሞ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡
የሜክሲኮ ፌዴራል ፖሊስ ዋና ኃላፊም በ2008 ዓ.ም ከተገደሉት ውስጥ ይጠቀሳሉ፡፡ የፌዴራል ፖሊስ አዛዥ ከተገደሉ በኋላ ሌሎች የፌዴራል ፖሊስ ባለስልጣናት ቁጣቸውን በማሰማት፣ በአደንዛዥ ዕጽ አዘዋዋሪዎች ላይ የተጠናከረ እርምጃ እንደሚወስዱ ገለ፡፡ የአገሪቱ መሪ ፕሬዚዳንት ፊሊፕ ካልዴሮም ..የሜክሲኮ መንግስት ከማንኛውም የተደራጀ የወንጀል ቡድን ይበልጣል.. በማለት በእልህና በቁጭት ተናገሩ፡፡
ይሁን እንጂ ከአንድ ሳምንት በኋላ በተሰበሰበ የሕዝብ ድምጽ 53 በመቶ የሚጠጉት ሜክሲኮxêEÃN የአደንዛዥ እጽ ጦርነት ቢነሳ የአደንዛዥ እጽ አዘዋዋሪዎች የመንግስትን ጦር ያሸንፋሉ የሚል እምነት እንዳላቸው የሚጠቁም ውጤት ይፋ ሆነ፡፡ በሜክሲኮ የተደራጁ የአደንዛዥ እጽ አዘዋዋሪዎችን ..ናርኮ ጋንግ..  በሚል ስያሜ የሚጠሩ ሲሆን ለፕሬዚዳንት ካልዴሮ አስተዳደር እጅግ ፈታኝ እንደሆኑም ይገለፃል፡፡ አሜሪካ በሜክሲኮ የተቀሰቀሰው ሁከት ወደ ሌሎች የላቲን አሜሪካ አገሮችና ወደራሷም እንዳይዛመት በመስጋት “Merdia Initative”  በተባለ ኦፕሬሽን የፕሬዚዳንት ካልዴሮ አስተዳደር ለሶስት ተከታታይ አመታት ..ናርኮ ጋንጐች..ን እንዲዋጋ የ400 ሚሊዮን ዶላር እርዳታ ለግሳለች፡፡
ሜክሲኮም ከአሜሪካ ባገኘችው እርዳታ ሄሊኮፕተሮችንና የድንበር መቆጣጠሪያ ዘመናዊ ባለራዳር መሣሪያዎችን በመግዛት ከ..ናርኮ ጋንጐች.. ጋር በዚያው ዓመት ግብግብ በመጀመር የተወሰኑትን ማደን ቢችሉም፣ አብዛኞቹ ጥቅጥቅ ባሉት የሜክሲኮ ጫካዎችና በተለያዩ ስፍራዎች በመሸሸግ አምልጠዋል፡፡
ሜክሲኮ በደቡብ አሜሪካ ካሉ አገሮች ኢኮኖሚዋ በአራተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ ለፀጥታ ጥበቃ የምታወጣው ወጪ ግን ከላቲን አሜሪካ አገሮች ሁሉ ይበልጣል፡፡ በየዓመቱ ፀጥታ ለማስጠበቅ በሚል 7 ቢሊዮን ዶላር ለፌዴራል የፀጥታ ኃይል ትመድባለች፡፡ ይሁንና ይህንን ያህል ገንዘብ ለፀጥታ ጉዳይ እያወጣች የአደንዛዥ እጽ ዝውውርን መቆጣጠር አልቻለችም፡፡ አንድ ከፍተኛ የሜክሲኮ የፖሊስ ኤክስፐርት ሲናገሩ፣ ..ሜክሲኮ እጅግ በተደራጀና ዘመናዊ በሆነ መንገድ ናርኮ ጋንጐችን ለመቆጣጠር እንድትችል ፖሊሶቻችንና የፀጥታ ኃይሎች በአሜሪካዊያን መሰልጠን ይኖርባቸዋል፡፡.. ብለዋል፡፡ በሌላ በኩል አንዳንድ የሜክሲኮ ፖሊሶች ከእጽ አዘዋዋሪዎች ጋር መሻረካቸው ቁጥጥሩን በጣም አስቸጋሪ እንዳደረገው ይነገራል፡፡
የፕሬዚዳንት ካልዴሮ ተቃዋሚዎች ደግሞ ሲናገሩ፣ ..ችግሩ ለፖሊሶች የሚከፈለው ደመወዝ አነስተኛ በመሆኑ ፖሊሶች ተጨማሪ ገንዘብ ለማግኘት ሲሉ ወደ ሙስና እንዲገቡ ይገደዳሉ፡፡ በሜክሲኮ አንድ ተራ ፖሊስ በአመት 5000 ዶላር ብቻ ነው የሚከፈለው፡፡ ይህ ደግሞ በጣም አነስተኛ ነው፡፡ ፖሊሶች በዓመት የሚያገኙትን ክፍያ፣ ከአንድ እጽ አዘዋዋሪ ጋር በመሻረክ በአንድ ቀን ያገኙታል፡፡.. ብለዋል፡፡
ተደጋግሞ በሚሰማ ሙሰኝነት የተማረሩት ፕሬዝዳንት ካልዴሮ 25.000 አዳዲስ የጦር ሠራዊት አባላት ሰልጠነው ..ናርኮ ጋንጐች..ን እንዲያድኑ አድርገዋል፡፡ የተሠማራውም ሠራዊት ..ናርኮ ጋንጐች.. ይገኙበታል በተባሉ ቦታዎች ሁሉ በመሠማራትና ከፍተኛ አሰሳ በማድረግ በርካቶችን በቁጥጥር ስር አድርገዋል፡፡ ይሁን እንጂ አዲስ የተመለመለው ጦር ሠራዊት ..ናርኮ ጋንጐች..ን በቁጥጥር ስር ካደረጉ በኋላ፣ ሁለት እጆቻቸውን የኋሊዮሽ ጠፍረውና ጭንቅላታቸውን ወደ መሬት ዘቅዝቀው በጠመንጃ አፈሙዝ እያዳፏቸው ሲሄዱ የሚመለከተው በርካታ የሜክሲኮ ነዋሪ ቁጣውን በሠራዊቱ ላይ ገልጿል፡፡ በሌላም በኩል ሁኔታውን የሚከታተሉት ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተቋማት፤ የካልዴሮን አስተዳደር የሰብዓዊ መብት እንደጣሰ በመግለ ተቃውሟቸውን አሰምተዋል፡፡ በ..ናርኮ ጋንጐች.. ላይ የሚፈፀመው ኢ-ሰብአዊ ድርጊት ትክክል አለመሆኑን የሚገልፁት የሜክሲኮ ፖሊስ ከፍተኛ ኤክስፐርት ኦርቱሮ አልቫራዶ፤ ..ሜክሲኮ በጣም ዘመናዊ የፖሊስ ኃይል እና የተጠናከረ የምርመራ ተቋም ያስፈልጋታል፡፡ ምክንያቱም ናርኮ ጋንጐች ከፖለቲካና ከቢዝነስ ሰዎች ጋር ግንኙነት ያላቸው በመሆኑ ጥንቃቄ በተሞላበት የምርመራ ዘዴ አጠቃላይ የአደንዛዥ እ መረቦችን መበጣጠስ ይቻላል፡፡ በአሜሪካ የታቀደው ሜሪዲያ ኢንሼቲቭ ፕላን ግን እኛ ላለፉት 20 ዓመታት ናርኮ ጋንጐችን ለማጥፋት ሞክረን ካቃተን ስትራቴጂካዊ እቅድ ጋር ብዙም የሚለይ አይደለም.. በማለት ገልፀዋል፡፡
ሜክሲኮ ..ናርኮ ጋንጐች..ን ለመቆጣጠር አሜሪካ ሙሉ በሙሉ እጇን ማስገባት እንዳለባት ደጋግመው የሚናገሩት የፖሊስ ባለስልጣናት፣ በተጨማሪም ድንበሯን አጥብቃ መዝጋት እንዳለባትም ይገልፃሉ፡፡ አብዛኞቹ የአደንዛዥ እ አዘዋዋሪዎች ደጐስ ያለ ገንዘብ የሚያገኙት ወደ አሜሪካ በሚያስገቡት እ ሲሆን በርካታ ተጠቃሚ ደንበኞችም አሜሪካ ውስጥ አላቸው፡፡ በዓለም ከሚመረተው ኮኬይን ግማሽ ያህሉ የሚሸጠው አሜሪካ ውስጥ ነው፡፡ በተጨማሪም ..ናርኮ ጋንጐቹ.. ሽጉጥ፣ አውቶማቲክ ጠመንጃ፣ AK-47 እና ሌሎችን የጦር መሣሪያዎች የሚታጠቁት ከአሜሪካ በሕገ ወጥ መንገድ በመግዛት ነው፡፡
በሜክሲኮ የአደንዛዥ እ እምብርት እንደሆነችና ..ናርኮ ጋንጐች.. እንደልብ እንደ¸RmsmsùÆT በሚነገርላት  ኩሊያካን የተባለችው ከተማ ውስጥ አዘዋዋሪዎቹ፣ እስከ ጐረቤት ሲናኦላ ግዛት ድረስ እንደልባቸው ሲወጡና ሲገቡ የሚታዩ ሲሆን፤ ..ኩሊያካን ከተማን መንግስት ለእነርሱ አሳልፎ የሰጠ እስኪመስል ድረስ ሕግ አይከበርባትም.. በማለት የኩሊያካን የፖሊስ ባልደረባ ይናገራሉ፡፡ በ2008 ብቻ ወደ 600 ሰዎች በዚህች ከተማ በ..ናርኮ ጋንጐች.. ተገድለዋል፡፡
600 ሰዎች ከተገደሉ በኋላ ..ናርኮ ጋንጐች.. ይገኙበታል የተባለውን በጣም ዘመናዊ ትልቅ ቪላ የፌዴራል ፖሊሶች በመክበብ ከውጭ በኩል የተኩስ እሩምታ ሲለቁ፣ ከቪላው ውስጥም ተመሳሳይ የከባድ መሣሪያ እሩምታ ተለቀቀ፡፡ ከ30 ደቂቃ በላይ በተካሄደ ውጊያ ሰባት የፌዴራል ፖሊሶች ሲሞቱ፣ ከ..ናርኮ ጋንጐች.. በኩል ደግሞ አንድ ብቻ ሞተ፡፡ ሁኔታውን ሲከታተል የነበረ የኩሊያካን ከተማ አሳ አጥማጅ ..አዝናለሁ፣ የናርኮ ጋንጐች ኃይል ከመንግስቴ ኃይል በልጧል.. በማለት ተናግሮ ነበር፡፡bሁኔታW በጣም የተማረሩት ፕሬዝዳንት ካልዴሮ፤ 2000 የጦር ሠራዊት ወደ ኩሊያካን ላኩ፡፡ ሠራዊቱም ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ በ..ናርኮ ጋንጐች.. ላይ ጠንካራ እርምጃ ወሰደ፡፡ በሠራዊቱ የጭካኔ እርምጃ የተማረሩት ..ናርኮ ጋንጐቹ.. ፀረ-መንግስት አቋም በመያዝ የፕሬዝዳንት ካልዴሮን አስተዳደር ለመፋለም ቆርጠው ተነሱ፡፡ ይህንንም ያደረጉት ለሁለት በመከፈል ነው፡፡ አንደኛው ቡድን ጃኩዊን (በቅል ስሙ ቻፖ) በተባለ ናርኮ ጋንግ የሚመራ ..ሲናላኦ ካርቴል.. የተባለ ቡድን ሲሆን፣ ሁለተኛ ደግሞ ቀድሞ የሜክሲኮ የጦር ሠራዊት ኮማንዶ በነበረው በዚታስ የሚመራው ..ገልፍ ካርቴል.. የሚባለው ነው፡፡
የካልዴሮ መንግስት ጥቃት ከፈፀመ በኋላ በኩሊያካንና በሲናኦላ በየጊዜው የመንግስት ታጣቂዎችና ፖሊሶችን መግደል በመጀመራቸው ምክንያት በኩሊያካን የሚገኙ አንዳንድ ፖሊሶች ስራቸውን ለማቆም ተገደው ነበር፡፡ በሲናኦላ የሚገኝ አንድ የፖሊስ ኮማንደር ሲናገር፣ ..የካልዴሮ አስተዳደር በኩሊያካንና በሲናኦላ የወሰደው እርምጃ ተስፋ አስቆራጭ ነው፤ እ አዘዋዋሪዎቹ እንደገና ተጠናክረው በእኛ ላይ የበቀል እርምጃ እንዲወስዱ ነው ያደረጋቸው..  ብለዋል፡፡ የፖሊስ ኮማንደሩ ሁለት ፖሊሶች በአንድ ቀን በሲናኦላ ከተማ በ..ናርኮ ጋንጐች.. ተገድለው ከተጣሉ በኋላ ስራቸውን በፈቃዳቸው ለቀዋል፡፡ በሲናኦላ ብቻ በየዓመቱ ከአደንዛዥ እ ሽያጭ 25 ቢሊዮን ዶላር ትርፍ ይገኛል፡፡ በርካታ የአደንዛዥ እ ከበርቴዎችም የተወለዱት በዚህች ግዛት ሲሆን፣ ከፊሎቹ በኩሊያካን ሲኖሩ የተቀሩት ደግሞ በሲናኦላ ይኖራሉ፡፡ በኩሊያካን የወንጀል መሐፍ ደራሲ አልመር ሜንዴዛ ሲናገር፤ ..የትኛውም የተደራጀ የመንግስት ጦር በኩሊያካንና በሲናኦላ የሚኙ ናርኮ ጋንጐችን ሊያሸንፍ አይችልም፤ ናርኮ ጋንጐችን በተወለዱባት ቦታ ማሸነፍ የማይሞከር ነው፡፡ እጅግ በጣም አደገኞች ናቸው.. በማለት ገልፆ ነበር፡፡
በሌላ በኩል በኩሊያካንና በሲናኦላ የሚገኘው ተራው ህብረተሰብ፣ ለ..ናርኮ ጋንጐች.. ከፍተኛ ከበሬታ አለው፡፡ የተለያዩ የፋሽን ልብሶች፣ ጫማዎች እንዲሁም ፖስተሮች ሳይቀሩ ታዋቂ የሆኑትን ..ናርኮ ጋንጐች.. ምስል ይዘው ይሸጣሉ፡፡ ..ናርኮ ጋንጐች.. በዚያ አካባቢ እንደ ጀግና የሚታዩ ናቸው፡፡ በ..ናርኮ ጋንጐች.. ስም በርካታ ሙዚቃዎች ተዚመው ካሴታቸው በየሙዚቃ ቤቱ ይሸጣል፡፡ በኩሊያካን ትልቅ የከተማዋ አደባባይ ላይ ተሰቅሎ የሚገኘው ጆናታን የተባለ በፖሊስ የተገደለ የ..ናርኮ ጋንግ.. ምስል ነው፡፡ በሜክሲኮ ምንም እንኳን ከፍተኛ ቁጥር ያለው የካቶሊክ አማኝ ቢኖርም፣ በኩሊያካንና በሲናኦላ ቀደምት ጀግኖች እንደ ቅዱስ ተደርገው ይታያሉ፡፡ ለምሳሌ በ19ኛው ክ/ዘመን ይኖር የነበረውና ፀረ መንግስት አቋም የነበረው አመፀኛ ጀሰስ ማልቬርዲ በኩሊያካን ከተማ እንደ ትልቅ ጀግና የሚቆጠር ከመሆኑ ባሻገር ትልቅ የፀሎት ቤት ተሰርቶለታል፡፡በእነዚህ ከተሞች አደንዛዥ እን መጠቀም ተራና ማንኛውም ሰው በፈለገው ቦታ የሚያደርገው ነገር ሲሆን አያሌ ኩሊያካናዊያንም በዕ ምርት በልጽገዋል፡፡ ከእ አምራች ገበሬዎች አንስቶ የሆቴልና የሪል እስቴት ባለሀብቶች ድረስ የኮኬይን ትርፍን ወደ ካዝናቸው ያስገባሉ፡፡ አንዳንድ የኩሊያካን ፖሊሶችና ፖለቲከኞችም የዚህ ትርፍ ተቋዳሽ ናቸው፡፡ በአጭሩ በዚያ አካባቢ ባለሀብት ለመሆን የአደንዛዥ እ ንግድ ውስጥ መግባት የግድ ነው፡፡ በርካታ የመንግስት ባለስልጣናት እንኳን የቤተሰባቸው አባል ወይም ዘመዳቸው ከአደንዛዥ እ ጋር የሚያገናኛቸው ነገር አይታጣም””ለምሳሌ በአገሪቱ የመንግስት ሕግ አውጪ አካል ውስጥ የሚሰራው ኦስካር ፊሊክስ ሦስት ወንድሞቹ እ አዘዋዋሪዎች ናቸው፡፡ የባለቤቱ ወንድም ደግሞ ዓለምአቀፍ የእ ንግድና ዝውውር ተቆጣጣሪ ነው፡፡ የፊሊክስ ሦስት ወንድሞቹ 18 ኪሎ ግራም ኮኬይን ከሜክሲኮ ወደ አሜሪካ ይዘው ሊገቡ ሲሉ በድንበር ጠባቂ ፖሊሶች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡ 18 ኪሎግራም ኮኬይን በአሜሪካ ገበያ ግማሽ ሚሊዮን ብር ይሸጣል፡፡ ኦስካር ፊሊክስ ወንድሞቹ ለፍርድ ቀርበው ሲበየንባቸው የተወሰደባቸውን ፍርድ ተቃውሟል፡፡ የፊሊክስ የስራ ባልደረባ ወ/ሮ ዮዲቲ ዲል ሪንከን ሲናገሩ፤ ..ናርኮ ጋንጐችን ሙሉ በሙሉ ማጥፋት የሚቻለው ከናርኮ ጋንጐች ጋር ግንኙነት ያላቸውን የፖሊስ አባላት፣ የቢዝነስ ሰዎችና ፖለቲከኞች ሁሉ መያዝ ሲቻል ነው፡፡ ይህን ስናደርግም እንደ ሸረሪት ድር የተተበተበውን የናርኮ ጋንጐችን መረብ ለመበጣጠስ ያስችለናል.. ብለው ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ወ/ሮዋ ይህንን በተናገሩ በሁለተኛው ቀን መኪናቸው ውስጥ በተጠመደ ፈንጂ ሞተው ተገኝተዋል፡፡

 

Read 4218 times Last modified on Saturday, 13 August 2011 09:58