Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 13 August 2011 11:04

የ..ፖፕሌሽን ሚዲያ ሴንተር.. እና የሙልጌታ ደባልቀው መፃህፍት ይመረቃሉ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

በጥናት የተመረኮዘ የሬዲዮ ድራማዎችን በማዘጋጀት የሚታወቀው ፖፕሌሽን ሚዲያ ሴንተር ..ሥነ ሁፍ ለማህበራዊ ለውጥና እድገት የፖፕሌሽን ሚዲያ ሴንተር ልምድ.. የሚል መሐፍ አዘጋጅቶ ያሳተመ ሲሆን ይሄንኑ መሐፍ በመጪው ሐሙስ ይመረቃል፡፡ በግዮን ሆቴል አዋሽ አዳራሽ በሚካሄደው የምረቃና የማስተዋወቂያ መርሃ ግብር ካሁን በፊት በተለያዩ መድበሎች ሥራዎቻቸውን ያሳተመላቸው 32 አንጋፋና ወጣት ደራስያን እንዲሁም ሌሎች እንግዶች ይገኛሉ፡፡

በሌላ በኩል ..ጋላህቲ ሰጊ.. በተሰኘው የህወሐት የትጥቅ ትግልን የሚተርክ መሐፉ የሚታወቀው ሙልጌታ ደባልቀው አዲስ መሐፍ በቅርቡ አሳትሟል፡፡
..ሓቦ-ሕገላት ተጋሩ.. በሚል ርእስ በትግርኛ የቀረበው መሐፍ ዛሬ ከቀኑ 9 ሰዓት በሒልተን ይመረቃል፡፡ ከዚሁ መሐፍ ጋር በወልደስላሴ ወልደሚካኤል በእንግሊዝኛ የተፃፈው |Terrorism in Ethiopia and The Horn of Africa የተሰኘ መሐፍ ይመረቃል፡፡ በመፃህፍቱ ምረቃ የትግራይ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ አባይ ወልዱ ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

Read 5112 times