Print this page
Saturday, 20 August 2011 10:32

ስሜት አእምሮ አለው

Written by  ሌሊሣ ግርማ
Rate this item
(3 votes)

...ስለምን እንጻፍ?... (ባለጽፍስ?)... ልጻፍ ወይንስ ቁጭ ብዬ ወሬ ላውራ?... ሳንቲም - ድብ አድርጌ ልወስን፡፡... አንበሳ/ሰው... ሰው ከወጣ፤ ስለ ሰው እጽፋለሁ፤ አንበሳ ከወጣ፤ ስለ አንበሳ... አንበሳ የድሮው የሀገሬ ሰው ነበር፡፡ ...ሳንቲሙ በአንበሳም በሰውም በኩል መውደቁ እንዳይታይ ቀዳዳው ውስጥ ገብቶ ተቀረቀረ፡፡ ለማይሆን ቁማር ሳንቲሜን ማጣቴ ቆጨኝ... መንገድ ላይ ለለመነችኝ አይነ-ስውር ብሰጣት ይሻለኝ ነበር፡፡...
ቆጨኝ፤ ለነገሩ የቁጭት ትውልድ ተብለናል፤ በሚዲያ፡፡ የቁጭት ትውልድን በቁጩ ሚዲያ... ከማስታወቂያ በኋላ እንመለስበታለን...፡፡
...ግዴለም ሳንቲሙ በመጥፋቱ ቢቆጨኝም ራሴ የመረጥኩትን በመጻፍ መናናት እችላለሁ፡፡ እምናናው ስለ ሰው በመጻፍ ነው፡፡

ስለሰው የተገነዘብኩትን ከተንሳፋፊ ስሜት ወደ ተጨባጭ እውቀት በመቀየር፡፡
...ሰውን በሙሉ አንድ ያደረገው ነገር ሀሳብ ሳይሆን አካል ነው፡፡ የአካል ዋና መገለጫ ተመሳሳይ ባህሪ፤ በተወሰነ ዓይነት የማይቀየር ደንብ/ህግ ተገዢ የሆነ የማንነታችንን መገለጫ፡- አካል ብለን መጥራት እንችላለን፡፡ any ability, habit, or skill, any pattern of ordered behavior governed by a ‘code’ of fixed rules.
...ሰውን ከማሰብ አቅሙ ይልቅ በአጠቃላይ የስሜት ተመሳሳይነቱ ነው አንድ የሚያደርገው፤ ተብሎ ሲታሰብ ቆይቷል፡፡ ግን አስተሳሰቡ ራሱ ስሜታዋ እና ስህተት ያለው እንደሆነ ለማሳየት እሞክራለሁ፡፡ አንድ ሰው አፍንጫው ቢመታ መድማቱ ወይም መሰበሩ አሊያም ዓይኑ ማልቀሱ ግልጽ ነው፡፡ ሙቀት ቢሰማው የሚያደርጋቸው ነገሮች ተመሳሳይ ናቸው፡፡ ግን ይህ የስሜት ሳይሆን reflex (ደመ-ነብስ) ትርጉም ነው፡፡
የፎቅ ደረጃዎች ሲሠሩ ለሰው እግር የተመጠኑ ተደርገው ነው፤ የሰው ሁሉ አረማመድ በእግር እስከሆነ ድረስ ተመሳሳይ ናቸው፡፡ ለአፍሪካዊ እና ለአውሮፓዊ የተለያየ ደረጃ የለም፡፡ የአካል ባህሪያቸው አንድ ያደርጋቸዋል፡፡ ሰውን አንድ የሚያደርገው ነገር በመጀመሪያ ደረጃ አካል ነው፡፡
ተራው ሰው በአማካኝ የሚቆይበት የእድሜ ልክ ይታወቃል፡፡ ተራው ሸረሪት ከ3 እስከ 12 በሚደርሱ መወጠሪያዎች በማያያዝ ነው ድሩን የሚያደራው፡፡ ነገር ግን ሸረሪቱ እንደሚኖርበት የአካባቢ ሁኔታ የተወሰኑ ጫናዎችን መቋቋሚያ ተጨማሪ ማሻሻያ ያደርጋል፡፡... መጀመሪያ ሸረሪት እስከሆነ ድረስ የሚገዛበት የበላይ ህግ አለ፤ በመቀጠል ለበላይ ህጉ የሚገዛ እንደ አካባቢው ሁኔታ እና ባህሪ የሚሻሻል ህግ አለ፡፡ ሸረሪት ድር መሥራት የበላይ ህጉ ከሆነ፤ ሰው ደግሞ ሰው እስከሆነ ምግብ መጠለያ እና ልብስ ያስፈልገዋል፤ በህጉ፡፡ ለሰው ልጆች፤ የበላይ ህጉ በህይወት መኖር ነው፡፡ በመቀጠል ለመኖሩ ትርጉም መስጠት፡፡ ለህይወቱ ትርጉም አለመስጠቱ በህይወት የመኖሩን ቀዳሚ ህግ ሊያስጥሰው ይችላል፡፡ ስሜት በህይወት ለመቆየትም ለቆይታ ግብ ለማግኘትም ያገለግላል፡፡ ስሜት ግን ምንም የማይጨበጥ ጉም ተደርጐ እንደሚታሰበው አይደለም፡፡ ስሜት ደመ ነብስ እስካልሆነ ድረስ በውስጡ በተለያየ ሬሾ አአምሮ አለበት፡፡
በሙዝ ልጣጭ ላይ የተራመደ ሰው አዳልጦት ይወድቃል፡፡ ይህ የእግሩ አፈጣጠር እና የመሬት ስበት ጋር ያለው ውል ነው፡፡ በሰው አካል እና በመሬት አካል መሐል ያለ ግራቪቲ የሚባል ውል፡፡ አንዱ ሰው ሙዝ ልጣጭ አዳልጦት የሚንሳፈፍ ሌላው ደግሞ ሊወድቅ አይችልም፡፡ ለሁሉም ሁለት እግር ያለው ሰው ሁኔታው አንድ ነው፡፡ ይወድቃል ወይ ተንገዳግዶ ከመውደቅ ይተርፋል፡፡ ማድረግ ለማይችለው ወይም ለሚችለው እንደ ሀሳቡ ፍላጐት ሊያድር ይችላል፡፡
ከወደቀ በኋላ የሚሰማውም ስሜት ማንም ሌላ ሰው በተመሳሳይ ሁኔታ ውስጥ ሊሰማው የሚችለው ነው፡፡ ካልተሰማው ሰውነቱ የሆነ ችግር አለው፡፡
ይህ በሰውነት ተግባር እና በተፈጥሮ ህግ መሀል ባለ ትስስር ሰውነት የተገደበ ነው፡፡ ሰውነት ሰው ሊያደርግ የማይችለውን ተአምር መሥራት አይችልም፡፡ ግጭቱ የሚመጣው ወይም ..ቁጭቱ.. እዚህ ላይ ነው፡፡ ሰውነት እንደ ሜካኒካል ማሽን ማድረግ የሚችላቸው ነገሮች ውስን መሆናቸው ላይ. . .፡፡ ማድረግ በሚችለው ውስንነት እና ማድረግ በሚፈልገው ስፋት መሃል ያለው ግጭት ነው ቁጭትን የሚፈጥርለት፡፡ ግን ሰው ሰውነት (አካል) ብቻ ሳይሆን ሀሳብም አለው፡፡
The ‘mechanical encrusted on the living’ symbolizes the contrast between man’s spiritual aspirations and his all-too-solid flesh subject to the laws of physics and chemistry.
የአካል ውስንነትን ከሀሳብ አመኝነት ጋር በማጣመር ጥበብ ይወለዳል፡፡ የጥበብ ዝቅተኛው ደረጃ ቀልድ ነው፡፡ የሙዝ ልጣጩ ቀልድ፤ የአካል ብቃት የለሽነት በስህተት ተመዝኖ ሲወድቅ የሚያሳይ በዝቅተኛው እርከን ላይ ያለ የጥበብ ዓይነት ነው፡፡
አንድ ሰው፤ በጣም ቁም ነገር የሆነ ስብሰባ እየመራ ተኮፍሶ በተቀመጠበት ወንበር በድንገት ከስሩ ተሰብሮ መሬት ቢጥለው... ሳቅ ይፈጠራል፡፡ ከሳቁ በፊት ግን በተጠበቀው ውስጥ ያልተጠበቀው ሲከሰት፤ የትዕይንቱን እንቆቅልሽነት (በመረዳት) እስኪሰክን የድንጋጤ ፀጥታ ይሰፍናል፡፡ማንም ሰው ከወንበር ውጭ መቀመጥ አይችልም፡፡ ተቀምጠህበት የቆየኸው ወንበር ከስርህ ከተሰበረ፤ መውደቅህ ግልጽ ነው፡፡ ይህ ማንም ሰው እና የሰውነት አካል ላለው ፍጥረት Axiom ነው፡፡ . . .ስለዚህ የወንበሩ ክስተት በተፈጥሮው ሳይሆን አስቂኝ የሆነው፤ በሰው አእምሮ በሰጠው ብይን ምክንያት ነው፡፡
ወንበሩ ሲሰበር ሰውዬው መውደቁ እና የወደቀው ሰው እንደአወዳደቁ ህመም ወይም ጉዳት እንደሚደርስበት ግልጽ ቢሆንም፤ ስብሰባውን ለታደመው ተመልካች ሁለት ስሜት ሊያንባርቅ ይችላል፡፡ አንድም መሳቅ አሊያም ማዘን፡፡ከአካል አቅም ውጭ መሆን ባለመቻሉ (አለመቻሉ) በገሚሶቹ ላይ ሳቅን ይፈጥራል፡፡ የተቀሩት ደግሞ አለመቻሉ ሀዘንን ይጭርባቸዋል፡፡ ...የተፈጠረውም ሆነ የተጫረው ስሜት ነው፡፡ comic or tragic… አስቂኝ እና አሳዛኘ የሚለው ምዘና ከግለሰቡ የመገንዘብ ወይም የማገናዘብ ሁኔታ የሚመነጭ ነው፡፡ ...በመሳቅ እና በማዘን በተከፈለው ተመልካች ውስጥ ሀኪም የሚገኝ ከሆነ ደግሞ፤ በመገረም እና በማዘን መሀልም ሆኖ ጉዳቱ ምን እንደሆነ የመረዳት ጉጉቱ ከፍ ያለ፣ ከሳቅም ሆነ ሀዘን ውጭ የሆነ ተግባር የመወጣት ግዴታዊ ስሜት ሊሰማው ይችላል፡፡የወንበሩ መሰበር እና የስብሰባው መሪ መውደቅን እንደ ትዕይንት ከወሰድነው፤ የትዕይንቱ ጭብጥ- ..ስትንጠራራ ከሰው በላይ ብትመስልም ከመውደቅ አታመልጥም፤ ትወድቃለህ፣ ትጐዳለህ.. የሚል ነው፡፡ ይህ ጭብጥ ማሳቅ ወይም ማሳዘን ወይም መስተሃልያዊ መሰላሰል ውስጥ የሚከት ስሜት የመፍጠር አቅም አለው፡፡የግሪኩ ኢካረስ በአፈ ታሪኩ ውስጥ የገጠመው ፍዳ በሙዝ ልጣጭ መውደቅ ጋር ተመሳሳይ ነበር፡፡ ግን የሱ አወዳደቅ እና ነገረ ሀሳቡ የቀረበበት መንገድ፤ በኢካረስ አወዳደቅ እንድንስቅ ከማድረግ ይልቅ፤ እንደ ምሳሌያዊ አስተምሮት እንድንቀበለው ያስገድደናል፡፡ ኢካረስ ወደ ሰማይ ለመውጣት በሰም የተሠራ ክንፍ፣ አድርጐ መብረሩ spiritual aspiration ወይም ሀሳብን የሚገልጽ ሲሆን፤ የሰም ክንፉ በፀሐይ ንዳድ ቀልጦ መፈጥፈጡ ደግሞ፤ ..አፈር ነህና ወደ አፈር ትመለሳለህ.. የሚለውን ጭብጥ የሚያስረግጥ ነው፡፡ ...ወድቆ መሞቱ ከማሳቅ ይበልጥ ያሳዝናል፡፡ ከመሳቅ ይበልጥ የራስን መጨረሻ በማገናዘብ እና በመመሰል ውስጥ ተመልካቹን እንዲመሰጥ ÃdRgêL፡፡T‰jÄþ ከኮሜዲ የበለጠ የስሜት ጥልቀት እንዳለው የሚነገረው፤ ከስሜትነቱ ባሻገር ተመልካቹ ራሱን በትዕይንቱ ቦታ መስሎ መመሰጥን ስለሚፈጥር ነው፡፡ በአጭሩ ስሜት እና አእምሮ በአንድ ላይ ስብሰባ የሚቀመጡበት በመሆኑ ምክንያት ነው፡፡ ስሜት ብቻውን ሲሆን ውጫዊ ግፊት (stimulation) የተሰጠ ምላሽ ነው፡፡ የአእምሮ ምዘና በብዛት ሲታከልበት የጠበቀ፣ የጠለቀ ይሆናል፡፡
“put into a formula, we could say that the ratio A:I where ‘A’ stands for crude emotion, and ‘I’ for intellectual stimulation in the higher forms of comedy, satire, and irony, the message is couched in implicit and oblique terms, the jock gradually assumes the character of an epigram or riddle, the witticism becomes a challenge to our wits:”
ተኮርኩሮ መሳቅ እና አስቂኝ ትዕይንት ተመልክቶ መሳቅ የተለያዩ ናቸው፡፡ ተኮርኩሮ መሳቅ በርበሬ ዓይን ውስጥ ሲገባ እንደማልቀስ ሁለቱም (ደመ-ነብስ) reflex ናቸው፡፡ በመዶሻ ጉልበት ሲመታ እግር እንደመወዛወዙ... አእምሮ ወይም ሀሳብ ያልተቀላቀለበት የአካል ውጤት ናቸው፡፡ ..ንፁህ ስሜት.. የሚባለው ነገር ምናልባት ይሄን ሁኔታ ገላጭ ነው፡፡ በስሜት ማወቅ በአእምሮ ማወቅ ማለት ነው፡፡ መሳቅ ግን ቀልድ ሰምተን ሲሆን የአእምሮ ትርጉም ተሳትፎ ይታከልበታል፡፡ አሳዛኝ ነገርም ወደ እንባ ሲወስደን የአእምሮ ምዘና በተሰማን ስሜት አማካኝ ሆኖ ይገለጻል፡፡ ስሜትም ከስሜት ህዋሳት (የነርቭ ሌጣ መልዕክት) የበለጠ ትርጉም ይኖራቸዋል፡፡ ትርጉሙም ለተርጓሚው ባለ ስሜት ..ግኝት.. ሆኖታል፡፡
ግኝት ከኮሚክ አጋጣሚ እስከ catharsis በተለያየ ደረጃ ሆኖ ሊገለጽ ይችላል፡፡ ከሳቅ እስከ ለቅሶ፡፡... ሳቅም እንደ ለቅሶ ካጋጠመው ግኝት በኋላ የስሜት ውጥረት ግልግሉን ይፋ የሚያደርግባቸው ..ሰውነታዊ.. ዘዴዎች ናቸው፡፡ ስሜት እና ሀሳብ ተነጣጥለው የሚገኙበት ግዛት ከሰው አካል ውጭ እንጂ ውስጥ ኖሮ አያውቅም፡፡ግኝት የሚለው ቃል የአእምሮ የሀሳብ ተሳትፎን በአካል ይዘት ውስጥ ያካተተ የመረዳት ወይም የመገለጥ ሁነት ነው፡፡ ሁነቱ የሰው ልጆች ንብረት ነው፡፡ የመገለጥ (ግኝት) ደረጃ from the trivial to the exalted የተለያየ ቢሆንም፤ ሰው እስከተሆነ ድረስ በሰውነት ውስጥ የገቡ የስሜት መልዕክቶች፣ ከአእምሮ ጋር ተቀናጅተው እንደ ግኝት ለባለቤቱ ይገለጻሉ፡፡ ይህም መገለጥ ጥበብ ተብሎ ይጠራል፡፡ የእውቀት መጀመሪያ ጥበብ ነው፡፡ የጥበብ መጀመሪያ ሳቅ ነው፡፡  
የሰው ልጅ የእርካታ ረሀብተኛ ነው፡፡ የአካል እና የሀሳብ ረሀቦቹ የማይታገስ ፈላጊ እና የፍላጐት ባሪያ አድርገውታል፡፡ የአእምሮ የመረዳት ፍላጐት፣ ከሰውነት የምግብ እና የመጠለያ ፍላጐት ያላነሰ የእርካታ ፍለጋ እንዲያደርግ ይነዱታል፡፡ ጥበብ የዚህ የአእምሮ እከኩ መፈተጊያ መንገድ ነው፡፡ መፈተጉ ትክክለኛ ያሳከከው ቦታ ሲሆን ግኝት (discovery) ተወልዷል፡፡ የግኝትን መወለድ የውጥረቱን መርገብ መጀመሪያ የሚገልው ሳቅ ነው፡፡ ሳቅ የግኝት መወለድን የሚገልጽ የብስራት ጥሩንባ ነው፡፡     
“The sudden bisociation of an idea or even with two habitually incompatible matrices will produce a comic effect, provided that the narrative, the semantic pipeline, carries the right kind of emotional tension. When the pipe is punctured, and our expectations are fooled, the now redundant tension quashes out in laughter…”
A. Koestler

Read 6877 times