Saturday, 20 August 2011 10:39

የአዳማ ከተማ ግብር ከፋዮች ተረብሸዋል

Written by  መንግስተ አበበ
Rate this item
(0 votes)

በአዳማ ከተማ ቀደም ሲል የደረጃ ሐ ቁርጥ ግብር ከፋይ የነበሩ ነጋዴዎች፣ ዘንድሮ ..ደረጃ ሀ ሆናችኋል..     መባላቸው እጅግ አስጨንቋቸዋል፡፡
ሌላው ጭንቀታቸው ደግሞ፣ ምን     ያህል እንደተወሰነባቸው ያለማወቃቸው ነው፡፡ ግብር ወደሚከፍሉበት መ/ቤት ሄደው ምን ያህል እንደተወሰነባቸው ሲጠይቁ ..ደረጃ ሀ ስለሆናችሁ ምን ያህል እንደምትከፍሉ የሚነገራችሁ ከመስከረም በኋላ ነው.. በመባላቸው ..ምን ያህል ይሆን የተጫነብኝ?.. በሚል ስጋት እየተረበሹ መሆናቸውን ይናገራሉ፡፡

አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የካፊቴሪያ ባለቤት፣ ..ዘንድሮ በአዲስ አበባም ሆነ በሌሎች ከተሞች ኅብረተሰቡ በተጣለበት የግብር ጫና ሲያማርር አይተናል፤ ሰምተናል፡፡ በአዳማ ከተማ ያለው የግብር አሰባሰብ ግን ከሁሉም የኦሮሚያ ከተሞች በጣም ይለያል፡፡ ደረጃ ሐ የነበረውን ሰው፤ ..ደረጃ ሀ ሆነሃል.. ብሎ መወሰን ምን ይባላል? የግብር ክፍያ ደረጃ የሚወስነው በዓመታዊ የሽያጭ መጠን እንጂ በቤቱ አስፋልት ዳር መሆን አይመስለኝም፡፡ በአንድ ጊዜ ሁለት ደረጃ አሸጋግሮ ሰውዬው በእውኑ ቀርቶ በህልሙ እንኳ ቆጥሮት የማያውቀውን ገንዘብ ክፈል ማለት ተጨባጩን ሁኔታ ያላገናዘበ ጭፍን አሠራር ከማለት ውጭ ምን ይባላል?.. ሲሉ በምሬት ተናግረዋል፡፡
የከተማዋ ገቢዎች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተሾመ ቀነኒ፤ ግምቱ የተሠራው በኮሚቴ ስለሆነ ቅሬታ ያለው ሰው በሕግ በተቀመጠው መሠረት ለይግባኝ ሰሚ ቦርድ ማቅረብ ይችላል ብለዋል፡፡
ያነጋገርናቸው የአዳማ ከተማ ነዋሪዎች በሙሉ ስማቸው እንዳይጠቀስ ስለፈለጉ የንግዳቸውን ዓይነት እየጠቀሰን እንቀጥል፡፡
የአራት ልጆች እናት የሆኑት ሴት በሻይ ቤት ንግድ ነው የሚተዳደሩት፡፡ በኪራይ ቤት ሻይ፣ ቡናና ጭማቂ (ጁስ) ይሸጣሉ፡፡ በረንዳ ላይ ደግሞ ፓስቴ ይጠብሳሉ፡፡ 70ሺ ብር መጠየቃቸው እጅግ እንደከበዳቸው ይናገራሉ፡፡ ..እንኳን 70ሺ ብር ልከፍል ቀርቶ እየተንቀሳቀስኩበት ያለው ካፒታል እዚህ ግባ የሚባል አይደለም፡፡ ሥራ ከጀመርኩ አንስቶ የተጠየኩትን ያህል ብር ቆጥሬ እንኳ አላውቅም፡፡ ቤት ተከራይቼ የራሴንና የዘመድ ልጆች እያሳደግሁና እያስተማርኩ፣ እንዲሁም ለሠራተኞች እየከፈልኩ የማገኛት ከእጅ ወደ አፍ ናት፡፡
..ላለፉት አራት ዓመታት 2800 ብር ስከፍል ነው የቆየሁት፡፡ አሁንም ያንኑ ልክፈል እያልኩ አይደለም፡፡ ከወቅቱና መንግሥት ከነደፈው የልማት ስትራቴጂ አኳያ ሁለትና ሦስት እጥፍ ብጠየቅ በማለት ራሴን እያዘጋጀሁ ነበር፡፡ አሁን የተጠየኩት ገንዘብ ግን እጅግ የሚከብድ ነው፡፡ የሚሆን አይደለም፡፡ ንግድ ፈቃዴን ለመመለስ አስቤ ነበር፡፡ ሕጉ፣ ንግድ ፈቃድ የሚመለሰው የተጠየቀውን ገንዘብ ከፍላችሁ ነው ስለሚል አልቻልኩም፡፡ byቀበሌãÒCN ሰብስበውን አንችልም ከብዶናል ብለናቸዋል፡፡
ለበላይ አመልክተን እንነግራችኋለን ተብለን ነበር፡፡ ደረጃ ሀ ስለሆናችሁ የእናንተ ጉዳይ ከመስከረም በኋላ ይታያል አሉን፡፡ እኔ ምን እንደማደርግ ግራ ገብቶኛል፡፡ ልጆቼን ምን አበላለሁ? በሚል ሐሳብና ጭንቀት ብቻ ሆኛለሁ፡፡ እንግዲህ መንግሥት የሚያደርገው ነገር ይኖራል ብዬ እየጠበኩ ነው.. በማለት ተስፋቸውን መንግሥት ላይ መጣላቸውን ገልዋል፡፡
በዓመት 178ሺ ብር በስምንት ወር ደግሞ 18 ሺህ ብር እንዲከፍሉ የተጠየቁት በካፊቴሪያ ሥራ የተሰማሩ የአራት ልጆች እናት ሲሆኑ ሥራውን ከጀመሩ ዓመት አልሞላቸውም - ገና 8 ወራቸው ስለሆነ አስገራሚ ነገር እንዳጋጠማቸው ይናገራሉ፡፡
የሚሰጡት አገልግሎት ትኩስ ነገር፣ ለስላሳ፣ ፉልና ዳቦ መሸጥ ነው፡፡ ሌላ ምግብ እንደማይሰሩ ይናገራሉ፡፡ 10 ፉል ማቅረቢያ ሳህን፣ ምግብ ማብሰያ፣ ጣሪያው በሁለት ቆርቆሮ የተከደነና ዙሪያውን በሸራ የተጋረደ ቤት ብቻ እንዳላቸው ገልዋል፡፡ ገማቾች የዕለት ገቢያቸውን ሲጠይቋቸው 120 ብር ማለታቸውን በትክክል ያስታውሳሉ፡፡ የሠሩበትን ግብር በመክፈል የዜግነት ግዴታቸውን ለመወጣት ወደ ግብር ሰብሳቢው መ/ቤት ሄደው፣ የሚከፍሉትን እንዲነግሯቸው ሲጠይቁ መ/ቤቱ፣ ..ደረጃዎ ወደ ሀ ተሸጋግሯል፤ እናንተ የምትከፍሉት ከመስከረም በኋላ ነው.. እንዳላቸው ገልዋል፡፡
ገንዘቡን ለማዘጋጀት እንዲረዳቸው ምን ያህል እንደተወሰነባቸው ቢጠይቁም፣ ..ራሷን ስታ ልትወድቅ ትችላለች.. ብለው በመገመት ሠራተኞቹ ሊነግሯቸው አልፈቀዱም፡፡ ነገር ግን እሳቸው ..ይነገረኝ.. ብለው አጥብቀው በመጠየቃቸው የዓመት ሽያጫቸው ከአንድ ሚሊዮን 700ሺ ብር በላይ ስለሆነ፣ በዓመት 178 ሺህ ብር የሚከፍሉ ቢሆንም ዓመት ስላልሞላቸው፣ የስምንት ወር የሚከፍሉት 118ሺ ብር እንደሆነ ነገሯቸው፡፡ በዚህ ጊዜ ሠራተኛዋ የተሳሳተች መስላቸው ..እሙዬ እየነገርሽኝ ያለው የእኔን ሳይሆን የሌላ ሰው ነው.. አሏት፡፡ ሠራተኛዋም እርግጠኛ በመሆን ስማቸውን፣ የንግድ ቤታቸውን ስም፣ አሳየቻቸውና የነገረቻቸው የራሳቸው መሆኑን ተረዱ፡፡
በዚህ ተገርመው ..የዕለት ሽያጫችን ምን ያህል ቢሆን ነው እንዲህ የሆነው?.. በማለት ጠየቁ፡፡ ምግብ k2500 እስከ 3000 ብር፣ ለስላሳ 700 ብር ገደማ፣ ትኩስ ነገር 800 ብር ገደማ፣ በአጠቃላይ ሥራ ሲጀምሩ ሜኑ ላይ ያሰፈሩት፣ ነገር ግን ያልሰሩበትን ሁሉ ደምረው የዕለት ሽያጫቸው፣ k3800 እስከ 4500 ብር መሆኑን እንደነገሯቸው ገልዋል፡፡ ..ይኼ ግምት ተሳስቷል፡፡ እኔ በቀን እንኳን ይህን ያህል ሩቡንም አልሸጥም.. አሏቸው፡፡
..ግድ የለም፤ ያመኑትን ይክፈሉና የቀሪውን ግማሽ አሲዘው ይግባኙን ይጠይቁ.. መባላቸውን ጠቅሰው ..እኛ እስካሁን ስንሠራ በቀን ከ400 እና ከ700 ብር በላይ ሸጠን አናውቅም፡፡ ያለው አጠቃላይ ንብረትም ከ20 እና ከ25ሺ ብር አይበልጥም፡፡ እኔ የተጠየኩትን ያህል ቀርቶ ሩቡንም መክፈል አልችልም፡፡ አሠራሩም ትክክል አይደለም፡፡ መንግሥት እርምት ያደርጋል ብዬ እየተጠባበኩ ነው.. በማለት አስረድተዋል፡፡
የዕለት ገቢውን ከ150 እስከ 200 ብር ያስመዘገበው ባለመስተዋት ቤት፣ የዕለት ገቢው k3500 ብር በላይ መገመቱን ተናግሯል፡፡ ..እኔ አምና የከፈልኩት 1700 ብር ነው፡፡ አሁን ብዙ የልማት ፕሮጀክቶች ተቀይሰዋል፡፡ ማንኛውም ሰው አገሩ ተጐሳቅላና ደህይታ ማየት አይፈልግም፡፡
አድጋና ተሻሽላ ሲያያት ደስ ይለዋል፡፡ ስለዚህ ከበፊቱ ሦስትና አራት ፐርሰንት ጨምሮ ቢከፍል ምንም አይደለም፡፡ ነገር ግን አንድን ሰው ከአቅሙ በላይ መጠየቅ ከየት ያመጣል ተብሎ ነው? ይሄ አግባብነት ያለው አሠራር አይደለም፡፡ መንግሥት እኮ እንደ አባት ስለሆነ ማመዛዘን አለበት.. በማለት ገልል፡፡
ደካማ ፎቶ ቤት ያለው ጐልማሳ፣ ብዙ ጊዜ ፎቶ የሚነሳ ሰው ስለማይመጣና የሥራ ውጥረት ስለሌለበት ብቻውን መሆን ስለሚሰለቸው ሻይ ቤት ሄዶ ይቀመጣል፡፡ ፎቶግራፍ የሚነሳ ሰው ሲመጣ ከሻይ ቤት ተጠርቶ ነው የሚያነሳው፡፡ ታዲያ ስንት ተወሰንብህ አልኩት፡፡ ስቱዲዮ ተብሎ 86ሺ ብር ክፈል እንደተባለ ነገረኝ፡፡ ..አምና የከፈልኩት 998 ብር ነበር፤ የቀን ገቢዬ ከ50 እስከ 60 ብር ነው እያልኳቸው የቀን ገቢዬን 2,000 ብር ብለው 86 ሺህ ብር ክፈል አሉኝ፡፡ ቀበሌ ሄጄ እንዴት እንደዚህ ይሆናል፡፡ መጥታችሁ እዩልኝ ብዬ ነበር፡፡ እንመጣለን ብለውኝ እስካሁን አልመጡም፡፡ ኑሮ ራሱ ግራ እያጋባን ነው፡፡ አስተያየት አድርገው ከቀነሱልኝ እከፍላለሁ፤ 86ሺ ብር ግን በፍም የማይሞከር ነው.. ብሏል፡፡
..ከልጆቼ ተለይቼ ገጠር ለገጠር ፎዴ (ጨርቅ) መነገዱ ስለሰለቸኝ ከልጆቼ ጋር ልሁን ብዬ ይህችን የተዘጋጁ ልብሶች (ቡቲክ) መሸጫ ከፈትኩ.. ያሉት የጫት ተራው ነጋዴ፤ ፈቃድ ካወጡ ገና ሰባት ወራቸው ቢሆንም 20ሺ ብር እንደተወሰነባቸው ይናገራሉ፡፡ ያለው ልብስ ምን ያህል ቢሆን ነው በማለት ሂሳብ ሲያደርጉ 18ሺ ብር ገደማ እንደሆነ ገልዋል፡፡bxnSt¾ ኪዮስክ የተለያዩ ሸቀጣ ሸቀጦች የሚቸረችረው ወጣት ባለፉት ሁለት ዓመታት የተወሰነበትን ግብር ቢከፍልም ውዝፍ አለብህ እንደተባለ ይናገራል፡፡
አሁን ባለው ሁኔታ ከአቅም በላይ ስለሆነበት ሥራው እንደማያዋጣው የጠቀሰው ወጣቱ፤ ..በ2001 ዓ.ም. 670 ብር፣ አምና ደግሞ 1080 ብር ያህል ለመገበሬ ደረሰኝ አለኝ፡፡ አሁን ግን የሁለት ዓመት ውዝፍ k5000 ብር በላይ፣ k3000 ብር በላይ ደግሞ የዚህ ዓመት ግብር ብለው k8400 ብር በላይ ክፈል ብለውኛል፡፡
እኔ ይህን ያህል ገንዘብ ለመክፈል አቅም የለኝም፡፡ ሥራ ባቆም ደግሞ በእኔ ስር የሚተዳደሩ ቤተሰቦቼ ከፍተኛ ችግር ላይ ይወድቃሉ፡፡ የማደርገው ግራ ገብቶኝ ጭንቀት ላይ ነኝ.. በማለት ላጋጠመው ችግር መፍትሔ ማጣቱን ተናግሯል፡፡ አቶ ተሾመ በከተማዋ እስካሁን ድረስ አራት ጊዜ የቀን ገቢ ግብር መካሄዱን ጠቅሰው፣ ላለፉት አራት ዓመታት (እስከ 2003 ድረስ ይሠራ የነበረው በ1999 ዓ.ም ግምት እንደሆነ ገልፀዋል፡፡ የቀን ገቢ ጥናት የተካሄደው በኮሚቴ እንደሆነ የጠቀሱት አቶ ተሾመ፤ የኮሚቴው ሥልጣን የቀን ገቢን ገማቾች ያቀረቡለትን ግምት አይቶ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በ1999 ዓ.ም ደረጃ ሐ የነበረ ግብር ከፋይ፣ ከአራት ዓመት በኋላ ባለበት አይቆይም፡፡
በደረጃ ሐ የተመደቡት ገቢያቸው በዓመት 100ሺህ የሆኑት ናቸው፡፡ ከአራት ዓመት በፊት 100ሺህ የነበረ ግብር ከፋይ ከአራት ዓመት በኋላ እዚያው አይቆይም፡፡ ወደ ደረጃ ለ (ከ100ሺህ እስከ 500ሺህ ለ ወይም ወደ ደረጃ ሀ(ከ500ሺህ በላይ ሊያድግ ይችላል፡፡ የግብር ከፋዮች ቅሬታ፣ ከአራት ዓመት በኋላም ለምን በአምናው መጠን አንከፍልም? የሚል ነው፡፡ ያለ አግባብ ተመድቦብኛል የሚል ሰው የይግባኝ ሰሚ ቦርድ ስላለ ቅሬታውን እዚያ ማቅረብ ይችላል፡፡ በዚህም ያልረካ ሰው ቅሬታውን ለመደበኛ ፍ/ቤት ማቅረብ ይችላል ብለዋል፡፡

Read 4802 times