Saturday, 20 August 2011 10:58

ስብሐታዊ የፖለቲካ አቋቋምና ወረብ

Written by  ዓለማየሁ ገላጋይ
Rate this item
(2 votes)

..ብዕር ሲያመልጥ ራስ ሲመለጥ አይታወቅም.. አለ ሲግመንድ ፍሮይድ (Slip of tangue) በአብዮተኞቹ የስብሐት ..ጢያራ.. መሬት እንዲያርፍ ተገደደ፡፡ ደበበ እሸቱና ስብሐት ደርግ ህፈት ቤት ለደርግ (የተመረጡ) አባላት እንዲያስረዱ ተጠሩ፡፡ ደበበ መጀመሪያ አስረዳ ሲባል ወደ ስብሐት እየጠቆመ ..የፃፈው እሱ ነው.. አለ፡፡
ከትልቁ አፈወርቅ (አፈወርቅ ገብረኢየሱስ) እስከ ትንሹ አፈወርቅ (ተስፋዬ ገብረአብ) ድረስ፤ ደራሲዎቻችንን ከነ ፖለቲካዊ አቋቋማቸው የመታሰቢያ ምስል ቀረፃ አካሂደናል፡፡ የአራት እትም ..የፎቶ.. ማሰባሰብ ጥረታችንን በዛሬው ሁፋችን እና እናጠቃልለዋለን ይሄን ሁፍ ማጠቃለያ ያደረግነው መሐላ ካላፈረስን በስተቀር በዚህ ርእስ ዳግመኛ አለመመለሳችንን ዋቢ አድርገን እንጂ፤ ..የፎቶ አልበሙ.. ሞልቶብን ማስቀመጫ በመታጣቱ አይደለም፡፡ እውር ጥጃ እንደዋለበት መስክ አልፈን-አልፈን ከመቦጨቅ በቀር ርእሰ ጉዳዩን አጥርተን እንዳልመደመድን ልቦናችን ያውቃል፡፡

የደራሲዎቻችን ፖለቲካዊ ..ከፍ-ዝቅ.. እኛ አሁን ቁጭ ብለን ከምንመዝንበት ሁኔታ የተለየ እንደነበር መገመት አዳጋች አይሆንም፡፡ እንደ ጃርት ገና ሲቀርቡት እሾኩ ኩፍ ከሚለው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ጋር እንኳን አገርግሮ ተለማምጦም መኖር ብዙ ፈተና እንዳለበት ይገባናል፡፡ ይሁንና ከዚያው ጋር ..ዞር-ዞር ያለ ደራሲ ለአፉ ሊጥ፣ ለወገቡ ፍልጥ.. አለማጣቱን በትውስታ መዳሰስ የወግ መሆኑን ልብ ልንለው ግድ ይለናል፡፡
እስከ ዛሬ ያየናቸው ደራሲዎቻችን በፖለቲካ ክህነት ወደ ..መገናኛ ድንኳኑ.. እንዲገቡ የተፈቀደላቸው ናቸው፡፡ ግማሾቹ ክብራቸውን፣ አንዳንዶቹም ህይወታቸውን በመሰዊያው ላይ አቅርበዋል፡፡ እነዚህ ብቻ አይደሉም፡፡ የፖለቲካ ..መርገምት.. በመፍራት ..ቡራኬውን.. የሚሸሹ ደራሲዎችም ነበሩ፡፡ እንደ መሬት የማንንም መፈንጨት ታግሰው ያለ ተፈጥሯቸው መኖራቸውን አንድ ህፀ አድርገን ለመቃኘት ስንነሳ ቅድሚያ አእምሯችን ላይ የሚመጣው ደራሲ ስብሐት ገብረእግዚአብሔር ነው፡፡
ደራሲ ስብሐት ገብረእግዚአብሔር የብሩንዲያውያኑን ተረት በህይወቱ የተረጐመ የመጀመሪያው ሰው ነው ማለት ይቻላል፡፡ ..የንጉሱን ውሻ ሳይ መጀመሪያ ሰላምታ የምሰጠው እኔ ነኝ.. ይላሉ ብሩንዲያውያኑ፡፡ ስብሐትም እንደዚያው ከንጉስ-ንጉስ ሳይመርጥ ዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው ሰው ..ውሻ.. ሰላምታ ሳይነፍግ ቆይቷል፡፡ ከሦስት ዓመት በፊት ..ዕንቁ.. መሔት ላይ እንዲህ ብሏል፡፡
..በእኛ አባባል ልንገርሽ እናቴን ያገባ ሁሉ አባቴ ነው ማንም ይንገስ ፖሊስን ፍርድ ቤትን እስከተቆጣጠረ ድረስ ንጉስ ነው፡፡ በእኔ እምነት ከንጉስ ጋር ምን አጣላኝ  እርግጥ ነው ሰርቼ ለመብላት መለማመጥ አይኖርብኝም፡፡ እዚህ መሃል ኢህአፓ ምናምን የሚሆኑት እኮ ወይ በወጣትነት ማለት እንዲህ መሆን አለበት፣ እንዲያ የሚሉ ናቸው፡፡ ያን ጉልበት አፍሰው ድል የሚያደርጉ አሉ፡፡ እንደ ቼ ጉቬራ ነብሶች አያለሁ፡፡ ኢህአፓ አለ፣ ኢሠፓ አለ፣ መሐል ቤት አቃጣሪዎች አሉ፤ ግን እዚያ ውስጥ ካልገባሽበት አይነኩሽም፡፡ ተመስገን እያልን ሰርተን ነው የምንገባው፡፡..
ስብሐታዊው የፖለቲካ አቋቋምና ወረብ በዚህ ንፍ የተቃኘ ነው፡፡ ያም ሆኖ ላይ ላዩን የሚከንፈው የምናገባኝ ..ጢያራ.. አንዳንዴ በቴክኒክ ብልሽት ምክንያት የተፋፋመ የፖለቲካ ትንቅንቅ መካከል ይጥለዋል፡፡ በአብዮቱ ፍንዳታ ዘመን ላይ ነው፡፡ ደበበ እሸቱ በዋና አዘጋጅነት ለሚመራው ..ቁምነገር.. መሔት አንድ መጣጥፍ ይፋል፡፡ ርእሱ ..የአብዮት አያቶች.. የሚል ነበር፡፡ የስብሐትን ..ጢያራ.. ሞተሯ እንዲነክስ ያደረጋት አረፍተነገር እንዲህ ይላል፡፡
..እንደምንሰማው በሰማየ ሰማያት ከሊቃነ መላእክት ሁሉ በላይ የነበረው ሳጥናኤል የመጀመሪያ አብዮታዊ ነው፡፡ ግን የአብዮቱን አንዱን ግማሽ ማለትም እምቢታቸውን ብቻ እንደፈፀመ እነ ቅዱስ ሚካኤል በጦር ድል ስለመቱት ተይዞ ከሰማየ ሰማያት ተወረወረ፣ ሰባት ቀን ከሰባት ሌሊት ሙሉ ሲወድቅ ሰንብቶ ሲኦል ውስጥ በእሳት ሰንሰለት ታሰረ..
..ብዕር ሲያመልጥ ራስ ሲመለጥ አይታወቅም.. አለ ሲግመንድ ፍሮይድ (Slip of tongue) በአብዮተኞቹ የስብሐት ..ጢያራ.. መሬት እንዲያርፍ ተገደደ፡፡ ደበበ እሸቱና ስብሐት ደርግ ህፈት ቤት ለደርግ (የተመረጡ) አባላት እንዲያስረዱ ተጠሩ፡፡ ደበበ መጀመሪያ አስረዳ ሲባል ወደ ስብሐት እየጠቆመ ..የፃፈው እሱ ነው.. አለ፡፡  
ስሉስ ወደ ስብሐት ዞረ ..እንዴት ሴጣን አብዮተኛ ነው ትላለህ.. ስብሐት ..የፃፍኩት . . ... ብሎ ማስረዳት ይጀምራል፡፡ የተናገረው ፍልስፍናዊ ትብትብ መካከል ..ማርክስ፣ ኤንግልስ.. የሚል ስም ስለጨመረበት ብቻ ጠያቂዎቹ ግራ ተጋቡ፡፡ ..አልገባንም.. እንዳይሉ ዋንኞቹ አብዮተኞች እንዴት ሳይገባቸዉ qr) ሊባሉ ነው፡፡ እርስ በእርስ ተያይተው ..በሉ እንዳይለምዳችሁ አሁን ሂዱ.. አሏቸው፡፡
ደበበ ..እጅግ ደንግጬ ስለነበር የሰማሁትን ማመን አቃተኝ.. ይላል፡፡ ደበበ ከስብሐት ቀድሞ ከክፍሉ ይወጣል፡፡ ስብሐት ተከትሎት በመውጣት በሩን ከዘጋው በኋላ ዳግም በመክፈት ንቅላቱን አስግጐ ..ግንኮ አሁን የነገርኳችሁ ውሸትም ሊሆን ይችላል.. አለ፡፡ ..ኑ - ኑ - ኑ.. ሦስት ወር ሊታሰሩ ወይም ሊገደሉ ይችሉ እንደነበርም ነው ደበበ የተናገረው፡፡ ስብሐት ብዕሩን ካለዳጠው በስተቀር አውቆ ወደ ፖለቲካው ..ንፍቀ ክበብ.. ውልፊት እንደማይል እራሱ ስለራሱ የመሰከረው ነው፡፡ ግድ ከሆነበት በአብዮቱ ..ሎጂስቲክ.. ውስጥ ገብቶ ..የፍጆታ.. አቅርቦት ሥራ ቢሰራ ይመርጣል፡፡ ለምሳሌ የካርል ማርክስ ..ካፒታል.. ተተርጉሞ ለአብዮተኞቹ ሲቀርብ የአርትኦቱን ሥራ እንዲያከናውኑ ስብሐትና ሌሎች አራት ሰዎች ታዘዙ፡፡
.. . . .Â ተባልኩ፤ መሄድ ነበረብኝ፡፡ የዛን ጊዜ ባርነት ውስጥ እንዳለሁ ገባኝ፡፡ ነፃ ዜጋህንማ ትችላለህ ወይ) ፈቃደኛ ነህ ወይ) ሌላም ችግር ካለብህ በምን አይነት አግዘንህ TœtÍlH) ይሉህ ነበር፡፡ እነ መንጌ ግን ደብዳቤ ብቻ ጣፉልን፡፡ በቃ ባርነት ነው አልን.. (ማስታወሻ - ገ 202)
እንዲህ ነው፤ የዚያ ዘመን ፖለቲካዊ ገለልተኝነት ባሪያ በመሆን ብቻ የሚወጡት አቀበት አይደለም፡፡ ከዚያ ዝቅ ያለው የዕቃ መጫኛ ከብትነትም ሊከተል ይችላል፡፡ ..ማንም ይንገስ.. ማለት ..ማንም ይጫነኝ.. ከማለት ዕኩል ነው፡፡ ስብሐት ገብረእግዚአብሔር ከዚያ ፎቀቅ ብሎ እስከ ሀገር ድረስ የተንጠራራ ግዴለሽነትን ያሳያል፡፡ በስብሐት ..ህገመንግሥት.. ግለሰብ የሁሉም ነገር መነሻ ነው፡፡ ከዚያ በኋላ ..ሀገር.. እና ..ህዝብ.. የተባሉ ጥቅሎች መዳረሻ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ይሄንን ስብሐት በአደባባይ ሲያውጅ ኖሯል፡፡
..አየህ ሰው ለሀገሬ ብሎ ደፋ ቀና ቢል አላምነውም፡፡ ለራሴ ብሎ ጀምሮ በቆይታ ለሀገር የሚተርፍ ከሆነ አምነዋለሁ፡፡ ለእኔ ቀርቶ ለእኛ እያሉ የሚነዙትን መፈክር አላምነውም ውሸት ነው፡፡.. ስብሐት እንዲህ ያለው ..ማስታወሻ.. ላይ ነው፡፡ ይሄንኑን አቋሙን ከአሥር አመት በኋላ ..አዲስ አድማስ.. ጋዜጣ ያለፈው ዕትም አምዱ ላይ ደግሞታል፡፡
ከህዝብ ግለሰብን የማስቀደም አቋም የኋላ ዘመን ፍልስፍናዊ መዳረሻ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ የጀርመኑ ፈላስፋ ጆርጅ ዊልሔልም ሔግል ከመሐፍ ቅዱስ አስተምህሮት ጋር የተስማማ አንድ አባባል ነበረው፡፡ ..The Whole is the true.. የሚል፡፡ የዘመኑ ሰው ሳይጐረብጠው ለብዙ ጊዜ ቆየ፡፡ በስተመጨረሻ ግን ፈረንሳዊው ደራሲ ማርሴል ፕሩለት የአመለካከቱን መንበር ገልብጦ መጣ፡፡ ..The Whole is the False.. ስብሐት ይሄንን አቋም ተቀብሎ አፍታቶታል፡፡ እዚህ ዘመን ላይ ሆነን ስንመለከተው የስብሐት አዝማሚያ፣ ተቃልሎ ይታየን ይሆናል፡፡ በዚያ በአብዮቱ ጊዜ ግን ..በቀልባሽነት.. የሚያስፈርጅ ዝንባሌ ነው፡፡ ሔግል ምንም እንኳን የሐሳባዊነት መነሾ ቢኖረውም ከሶሻሊስቶቹ አቋም ጋር የተስማማ ድምዳሜ ነው ያሳየው፡፡ ፕሩስትና መንዛሪው ስብሐት ግን በተፃራሪው ፀረ አብዮታዊነትን አንፀባርቀዋል፡፡ ..ግለኝነት.. (Individualism) ከሶሻሊስቶቹ አንፃር መደባዊ ትርጉም የሚሰጠው ነው፡፡ የግል ንብረትን ሕጋዊ አድርጐ፣ ብዝበዛን ለማስፈን ሰው በተፈጥሮው ግለኛ ነው የሚለውን አመለካከት የማራመድ ፍላጐት ነው፡፡ ስለዚህ እንዲህ ያለ አቋም መያዝ ..በኢምፔሪያሊስቶች ተላላኪነት.. ያስወነጅላል፡፡ ደግነቱ ስብሀት ይሄንን የተብላላ ሐሳቡን እንደበላ ምርጊቱን ከፍቶ ማቃመስ የጀመረው አብዮቱ ካበቃለት ከአስር ዓመታት በኋላ ነው፡፡ ያኔ ለምን አልገለውም?
..እኔ እኮ ጊዜውን አይቼ ነው የምራመደው፣ የምጽፈው፡፡ ተፈጥሮዬ እንደዛ ነው፡፡ ለምሳሌ በደርግ ጊዜ የማትጽፍባቸው ብዙ ነገሮች አሉ፡፡ ይሁን እንጂ በተወሰነ ነገር ላይ በልኩ እንድትጽፍ ይፈቀድልሃል፡፡ ሕዝቡም የእነሱን ብቻ ነው እንዲያነብ የሚፈለገው፡፡ እኔ ሞኝ አይደለሁም ሌላ ነገር የምጽፈው፡፡.. (ማስታወሻ - 237)
ሰጎናዊ ባህርይ ያለው የስብሀት ..ህገ-መንግሥት.. ፖለቲካዊ አደጋ ሲመጣ መጋፈጥን እንደ ጅል ድርጊት ይቆጥረዋል፡፡ ጭንቅላትን አሸዋ ውስጥ መቅበር ነው መፍትሔው፡፡ ስብሀት የሆዱን በሆዱ አድርጐ እንደ ስልጡን ግመል ቁመቱን ..ለጫኝው.. ሲያመጣጥን እዚህ ደርሷል ማለት ነው፡፡ ..የሰው ሆዱ የወፍ ወንዱ አይታወቅም.. ለስብሀት አኗኗር የጠቀመ ብሒል ነበር፡፡ የኋላ ኋላ ዘመን አልፎ ሽፍንፍኑ ሲገለጥ ስብሀት የሚያስበው ከማስደመምና ከማስደነቅ አልፎ እስከ ማስደንገጥም ሊደርስ ይችላል፡፡ በታህሳስ ግርግር ሰሞን ከኢትዮጵያ ውጭ ስለገጠመው እንዲህ ተርኮልን አንብበናል፡፡
..ተስፋዬ ገሠሠ የተዋናይነት ጥበብን ሺጋጎ አጠገብ በምትገኝ፣ ኤቫንስተን በምትባል ከተማ በኖርዝ ዌስተን ዩኒቨርስቲ ተማረ፡፡ ትምህርት ቤት ተዘግቶ ልጠይቀው ሄድኩና እሱ ጋ ጥቂት ቀን እንደቆየሁ በአዲስ አበባ የሃምሣ ሦስቱ የታህሳስ ግርግ ተነሳ፡፡
ተስፋዬ ሺጋጐንና የሌሎች ከተማዎችን ታላላቅ ጋዜጦች በሙሉ ሰብስቦ በጥድፊያ እያገላበጠ ሲያነብ እኔ እያላነበብኩ መሆኔን አየ፡፡
..ለምን አታነብም?..
..ምን ያደርግልኛል?.. አልኩት
በጣም ተናደደ
..አገርህ አይደለም እንዴ? አአትረባም.. . ብሎ ገላመጠኝ፡፡ ተቀየመኝ፡፡ ግን ምናልባት ከግማሽ ሰዓት በኋላ ቂሙን ረስቷል. . . ትዝ እንደሚለኝ ከሆነ.. (ኦማር ሐያም -ገጽ 6)
ስብሀት በግብርም ይኸው ነው፡፡ የአገር ጉዳይ ሲበርደውም ሲሞቀውም አይታይም፡፡ ..ድንበር የለሽ የደራሲዎች ቡድን.. ቢኖር ደስታው ወደር የሚያጣ ይመስላል፡፡ ጆሮው ለአገር፣ ዓይኑ ለድንበር አይጠመድም፡፡ አብዮቱ በፈነዳበትና የወጣቶች አመ በተፋፋመበት በዚያ ወቅት ስብሀት እንደ እንቅልፍ ልብ ተጓዥ በውስጡ አለም እየተመራ ሲንቀሳቀስ ነበር፡፡ ከወቅቱ ሁኔታ ጋር ግንኙነት የሌለው ተረት እና አጭር ልቦለድ በመጻፍ ተጠምዶም አሳልፏል፡፡ ..አምስት ስድስት ሰባት.. መድብል ውስጥ የተካተቱት ..ለጉድጓድ..፣ ..ዘር.. እና ..ተከታትለው ሽው ቢሾፍቱ.. የተጻፉት አብዮቱ አመ ሊወልድ እንዳፋፋመው በ1966 ዓ.ም. ነበር፡፡ በተመሳሳይ ..እኔ ደጀኔ..፣ ..እትዬ አለታዬ..፣ ..ፍራሽ አዳሽ.. እና ..አምስት ስድስት ሰባት.. የተጻፉት አብዮቱ የአመ አራስ ቤት እንዳለ በ1967 ዓ.ም. ነበር፡፡ በምን ዓይነት ደንዳና ልብ ከነባራዊው ዓለም እንደተናጠበና እነዚህን ታሪኮች እንደጻፈ የሚያውቀው እሱ ብቻ ነው፡፡ እዚህ ላይ ግን አንድ ነገር መጠየቅ የምንችል ይመስለናል፡፡ ለመሆኑ ስብሀት ግድ የሌለው ለሀገርና ለሕዝብ ብቻ ነው ወይስ ለራሱም ጭምር? ምክንያቱም ሀገሬው ሁሉ እንደበድን እራሱን መከላከል ሳይችል ቀርቶ፤ ዓይኖቹን እያንቀዋለለ የሚያርፍበትን ..ጥንብ አንሣ.. ይጠባበቅ የነበረበት ሁኔታ የስብሀትም ወቅታዊ እውነታ ስለነበር ነው፡፡ ታዲያ ግዴለሽነቱ ከሐገርና ከወገን አልፎ እራሱስ ላይ አልተተገበረም ትላላችሁ?

 

Read 3962 times Last modified on Saturday, 20 August 2011 11:00