Saturday, 20 August 2011 11:00

ከድርሰቱ በላይ የሆነ ..ድርሰት.. ያላቸው ገ-ባሕርያት የበዙበት ..ተልሚድ..

Written by  ተስፋሁን tesfahung@gmail.com
Rate this item
(2 votes)

ሁለተኛ ሥራን ማሳመር እንደ ኢትዮጵያውያን አርቲስቶች የከበዳቸው ይኖራል ብዬ አላስብም፡፡ በማንኛውም ጥበባዊ ሥራ (ሙዚቃ፣ ድርሰት፣ ፊልም...) በመጀመሪያ ሥራቸው ጥሩ ሠራችሁ የተባሉ ሁሉ በቀጣዩ ሥራ ለምን መቀመቅ እንደሚወርዱ አይገባኝም፡፡ (ይህ አባባል የማይመለከታቸው ውስን ደራሲያን፣ ዘፋኞችና የፊልም ባለሙያዎች አሉ፡፡) ለማንም እንደሚገባው፣ በመጀመሪያ ሥራ ብዙ ተቀባይነት ማግኘት ለቀጣይ የበለጠ አደራ መሸከም ነው፡፡ ይህን አደራ ለመወጣት ደግሞ ከመጀመሪያውም በበለጠ መሥራት ያስፈልጋል፡፡ እኛ አገር የተያዘው ግን በመጀመሪያው ተቀባይነት ያገኘ ሰው ይበልጥ ቸልተኛ እየሆነ ይሄዳል፡፡ ይህን መግቢያ ማለት ያስፈለገኝ በይስማዕከ መጽሐፍ ዙሪያ የታዘብኩትን ለማጋራት በማሰቤ ነው፡፡

ይስማዕከ ወርቁ በቅርቡ ..ተልሚድ.. የተባለ መጽሐፉን አስነብቦናል፡፡ ለብዙዎቻችን እንግዳ የሆነ ቃል እንደ ርዕስ በመጠቀም አሁንም ይስማዕከ መጽሐፉ ስለምን የሚያወራ ይሆን የሚል ጉጉት እንዲያድርብን ለማድረግ ችሏል፡፡ ራሱ በሚሠራቸው ሽፋን ዲዛይኖችም ትኩረት መሳብ መቻሉን ቀጥሎበታል፡፡ የገ-ባሕርያት ለየት ያለ ስያሜም እንደ ወትሮው ባይሆንም ዠንመርቂ እና ተልሚድ በሚሉት ተጠቅሟል፡፡ ከምንም በላይ ደግሞ ያስቀመጣት ዳጎስ ያለች ስም መጽሐፉን እንድንጠብቀው አድርጎናል፡፡ ከቁጥር አንዱ የአሜሪካ የደህንነት ተቋም ያለ ችግር ሰው ይዞ እስከመውጣት ድረስ ለገ-ባሕርያቱ የሚጨነቀው ይስማዕከ፣ በ..ተልሚድ.. ግን ያለወትሮው ሁለቱን ለሞት አንዷን ለዘለቄታዊ እብደት በመዳረግ ጨክኖባቸዋል፡፡ ነገር ግን በመግቢያው ከ..ዴርቶጋዳ.. እና ..ራማቶሓራ.. የተለየ ነገር ይዞ መቅረቡን ቢነግረንም፤ አሁንም ስለላ፣ ሳይንሳዊ ግኝት፣ በውጭ አገር የስለላ ተቋም የተቀጠሩ እና በጥብቅ የሚጠበቁ ኢትዮጵያውያን\ ሳያሳምኑ የሚያልቁ ተዓምራዊ ክስተቶች፣ ወዘተ የተሞላ በመሆኑ ልዩነት አለው ማለት አይቻልም፡፡
mc½M ስምን ለተደጋጋሚ ሽያጭ በማቅረብ የኢትዮጵያን ገበያ ያህል የደራ ያለ አይመስለኝም፡፡ በሌሎች አገራት በአንድ ጉዳይ ስሙን የተከለ በቀጣዩ ቢጠቀምም ለሦስተኛ ደረጃ ግን ሊያውለው አይችልም፡፡ ይህ ስጋትም ስላለ ማንኛውም በመጀመሪያ ሥራው ላይ ጥሩ ተቀባይነት ያገኘ ቀጣዩን ይበልጥ እየተጠነቀቀ፣ ይበልጥ እያሰማመረው ይሄዳል፡፡ ለዚህ ጥሩ ምሳሌ የሚመስለኝ የይስማዕከ ቀደምት ሥራዎች አያት የሆነው ዳን ብራውን ነው፡፡ ዳን ብራውን እውቅናው በጨመረ ቁጥር ይበልጥ እንደወይን እየበሰለ የሚሄድ ደራሲ ነው፡፡ ይስማዕከ ግን ከዚህ በተቃራኒው የቁልቁለት ጉዞውን አሁንም ቀጥሎበታል፡፡ ደግነቱ እንኳን ላሁኑ ለቀጣዩም ሊተርፍ የሚችል ስም በምንም ይሁን በምን ቋጥሯል፡፡ (በተሻለ ነገር ካላዳበራት ነጥፋ እስክታልቅ ድረስ ብዙ ጊዜ ይኖረው ይሆናል፡፡)
ይስማዕከ ስለሂስ ያለውን መረር ያለ አቋም በመግቢያው በራሱ አንደበት፣ መጽሐፉ ውስጥ ደግሞ በገ-ባሕርያቱ አንደበት አሳይቶናል፡፡ በመግቢያው ላይ መጽሐፉ ከ..ዴርቶጋዳ.. እና ..ራማቶሓራ.. በፊት የተጻፈ ቢሆንም ለማብሰል በማሰብ ብዙ ጊዜ እንዳቆየው ገልጾ፤ በጊዜ ብዛት በደንብ እንዳበሰለው ያስረዳናል፡፡ ነገር ግን |[መጽሐፉN] እንክት ብሎ በስሏል ማለቴ አይደለም፤ ሆኖም ይህችን በትህትና ብልም በዚህች ቀዳዳ ልግባ የሚልን አላስገባም፡፡ እንዲህች ባለች የትህትና ቀዳዳ የሚገቡ፣ ቢችሉ መልሰን እንሥራህ የሚሉ ደፋሮች አይታጡም፡፡ ያገኘኝ ሁሉ እንደ እርጥብ ጭቃ ጠፍጥፎ በራሱ አምሳል እንዲሠራኝ የምፈቅድ አይደለሁም.. ይላል፡፡ በተጨማሪም፤ ..የመቅለል እና የማቃለል ዘመን መጣ፤ የመቅለልና የመቀለል ዘመንም ተከተለው.. በማለት ከመጽሐፉ ታሪክ ጋር ብዙም የሰመረ ግንኙነት የሌለው ዓረፍተ-ነገር ሰንቅሮ ለሚተቹት ሁሉ ማስጠንቀቂያ ነገር ትቶ ያልፋል፡፡
በዋና ገ-ባሕርዩ ተልሚድ እና ሌሎች ..ደራሲ ነን ባይ.. ገ-ባሕርያት ግጭት አስታኮ ደግሞ ..የኢትዮጵያ ጋዜጦች በትንሽ ፍርፋሪ መልአክ blùŸ ብትላቸው ዐይናቸውን አያሹም፡፡ ...የጋዜጣ ውዳሴም ሆነ የጋዜጣ ኩሳሴ ማንንም ምንም አላረገም፤ እንደውም ጋዜጣ ካቀሰሰው ጋዜጣ ያኮሰሰው የተነባቢነት እድል ሳያገኝ አይቀርም.. (ገጽ 78-79) በማለት ያጣጥላል፡፡ አጠቃላይ መንፈሱ እብሪት የተጠናወተው ደራሲ፤ ገና ከበሩ ..ሕይወት እንዲህ ትቀጥላለች፤ ያልፈለገ አለመቀጠል ይችላል.. ስላለን ገብተን የተበሳጨን ካለን ያለቦታችን ለመግባታችን ከመቆጨት ያለፈ ምንም እድል ያለን አይመስልም፡፡
መቼም ሂስ ማለት ጠፍጥፈን እንሥራህ ማለት እንዳልሆነ ማንም ያውቀዋል፡፡ ሂሱ አለአግባብ የተሰጠ ነው ተብሎ ከታመነ ምላሽ መስጠት ነው፤ ካልሆነም በሂሱ መታረም፡፡ አለበለዚያ ግን ገበያ ላይ መጽሐፍ እያዋሉ እንዳትነኩኝ የሚሉት እብሪት ለወግም አይመችም፡፡ (ቢያንስ ለመግዛት ያወጣሁትን 40 ብርና የፈጀብኝን ጊዜ ያህል ከማጉረምረም ማን ያግደኛል?) ለዚህም ነው በሂስ ላይ ቢያጉረመርምም ..ውዳሴ ካገጠጠው፣ ሂስ የወቀጠው ደራሲ ታላቅ የመሆን እድል አለው.. ያላት ነገር ከሁሉም ሚዛን ደፍታብኝ ነው ይህን ለመጻፍ የወደድሁት፡፡ ጽሑፌንም የደራሲውን ቀመር በመከተል አንድ ማንኪያ ሙገሳ፣ ሦስት ማንኪያ ወቀሳ አድርጌ አቀርበዋለሁ፡፡      
አንድ ማንኪያ ሙገሳ
ይስማዕከ በአንድ መጽሐፍ ላይ አንድ ታሪክ ብቻ ይዞ ምንችክ ባለማለት ችሎታው አሁንም ጥሩ ነገር አሳይቷል ማለት ይቻላል፡፡ የኮንትሮባንዲስቱ ዠንመረቂ፣ ከርታታው ተልሚድ፣ አስገራሚው አያ በሽመሉ፣ የደይ በሽታና የእናቷ ሁኔታ እንዲሁም የብጡል ታሪክ ራሳቸውን ችለው መቆም የሚችሉ ተደራራቢ ታሪኮች ናቸው፡፡ ከገጽ ወደ ገጽ በተዟዟርን ቁጥር አንዴ ያንዱን ሌላ ጊዜ ደግሞ የሌላውን እያፈራረቀ መውሰዱ ጥሩ ሊባል የሚችል ችሎታ ነው፡፡ የቋንቋ ፍሰቱ እና የቃላት አጠቃቀሙንም ሳያደንቁ ማለፍ ተገቢ አልመሰለኝም፡፡ በግሌ፣ ገሰረት (ሆዳም)፣ የንግሊላ (ወደ ኋላ መውደቅ)፣ እሟቀሊጦ (መና መቅረት)፣... ዓይነት ድሮ የተለያየኋቸውን መደበኛ አማርኛ እንኳን የማይመስለኝን ቃላት ማግኘት መቻሌ ጥሩ መሆኑን እንድመሰክር አድርጎኛል፡፡
በአገር ላይ ከባድ ጥፋት እያደረሰ ስላለው የኮንትሮባንድ ንግድ ላይ አተኩሮ መጻፉም ሌላው ይበል ሊባል የሚገባው ነገር ነው፡፡ በጉዳዩ ላይም የተቻለውን ያህል ጥናት አድርጎ መውጫ መግቢያቸውን፣ መንገዳቸውን እና ስልታቸውን ባካተተ መልኩ የተብራራ የቦታ እና ሁኔታ ትንታኔ ለማቅረብ መሞከሩም ተጨማሪ ጥንካሬው ነው፡፡ (ምንም እንኳን አሁን ላይ ሆኖ ሲታይ ከባቡሩ ሥራ ማቆም ጋር ተያይዞ አብዛኛው ነገር ጊዜ ያለፈበት ቢሆንም፡፡) በሚገልጻቸው አካባቢዎች ላይ ያደረጋቸው የማስተዋወቅ ሚናዎችም አገራችንን እንድናውቅ ከመገፋፋት አንጻር በጐ ሚና ሊወጡ ይችላሉ፡፡ ከአዲስ አበባ እስከ ድሬዳዋ ባለው መስመር ያሉ ከተሞች ገለጻ እና የድሬዳዋዎቹ ዋሻዎች ማብራሪያ ከዚህ ውስጥ ይካተታሉ፡፡
በሌሎች ጉዳዮች ላይም በቂ ሊባል ባይችልም ጥናቶችን አድርጎ መሥራቱ ሊጠቀስ ይችላል፡፡ የሻንግኻይ መንገዶች፣ የሆቴል እና ባንክ ስሞች፣ የጃፓንኛ ምልልሶች፣ ወዘተ የመሳሰሉትን እንደ ጥንካሬ ልንወስድለት እንችላለን፡፡ (እነዚህ ነገሮች ግን አንዳንዶች እንደሚያስቡት ያን ያህል ድቤ የሚመታላቸው ጉዳዮች አይደሉም፡፡ በዘመነ ቴክኖሎጂ ጃፓንኛውን በ..ጎግል-ትራንስሌተር..፣ የሻንኻይን መንገዶችም በጎግል ኧርዝ በቀላሉ መሥራት ይቻላል፡፡) ሥነ-ጽሑፍን በሳይንሳዊ እውቀቶችና መረጃዎች ለማዳበር የሚያደርገው ጥረትም መልካም ሊባል የሚችል ነው፡፡ በ..ተልሚድ.. የተካተቱ የተለያዩ በሽታ ስሞች ማብራሪያዎች ለዚህ እንደ አብነት ሊነሳ ይችላል፡፡
ሦስት ማንኪያ ወቀሳ
እርግጥ ነው፣ ይስማዕከ በ..ተልሚድ.. እንደ ..ራማቶሓራ.. ከአገር አቀፍ የደህንነት ተቋም ፊት ለፊት ሻይ ቡና የሚባልበት ካፌ አያስነብበንም፤ ራዳር ውስጥ የማትገባው ዴር-33 በሄሊኮፕተር ስትመታ አያሳየንም፤ ሙሉ የፊት ቀዶ ጥገና ማድረግ የሚችሉት ሃኪሞች እጅን መጠገን ሲያቅታቸው አይነግረንም፡፡ ነገር ግን አሁንም በጥንቃቄ ሊወገዱ፣ በእጅ ብዛት ሊታረቁ፣ በጊዜ መውሰድ ሊበስሉ፣ በጥንቃቄ ሊፈወሱ፣ በማማከር ሊቃኑ የሚችሉ በርካታ ሕጾች ሞልተውታል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ ጎላ ጎላ ብለው የታዩኝን ብቻ መርጬ አቀርባለሁ፡፡
የመጀመሪያው አሁንም እንደ ..ራማቶሓራ.. የሚከተላቸው ምክንያት የለሽ አካሄዶች እና ውል የለሽ የታሪክ እጥፋቶች ናቸው፡፡ ልቦለዱ የገሃዱ ዓለም ነብራቅ ከመሆኑ አንጻር ሊሆኑ የማይችሉ ነገሮችን እንኳን ሲያቀርብ አዋዝቶ እና አስማምቶ መሆን መቻል አለበት፡፡ ከዚህ አንጻር አሁንም ደራሲው በዋል ፈሰስ የሆኑ ትዕይንቶችን ከማቅረብ ሊቆጠብ አልቻለም፡፡ ለምሳሌ፡- ኤም ኤስ ኤስ የተባለውን የቻይና የስለላ ድርጅት እንደዛ አግዝፎ፣ ከሲአይኤ እና ሞሳድም በላይ እንደሆነ አድርጎ ካቀረበው በኋላ ብጡልን የሚይዝበት መላ ማሳጣቱን መግለጽ እንችላለን፡፡ በዚያ ላይ ብጡል በአገሪቱ ደረጃ በጣም ጥብቅ ሊባል የሚችል ሚስጥር ለብቻው ጠቅልሎ የያዘ ከመሆኑ አንጻር፤ ጉዳዩን ስንመዝነው ፉርሽ ይሆንብናል፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ ዠንመረቂ እና ብጡል ስለዋነኛው ሚስጥር እየተወያዩ እንደሆነ የሚያውቀው ሚስተር ሉ ሚስጥሩን እንዲጨርሱ የሚያስችላቸውን ተጨማሪ አምስት ደቂቃ ሊሰጣቸው አይችልም፡፡
በመቀጠል ድርጅቱ ብጡል በጠፋበት አምስት ደቂቃ በማይሆን ቅጽበት ፖስተሮችን በየአደባባዩ ግድግዳዎች መለጠፉ (ፖስተር ዲዛይን አድርጎ፣ ማተሚያ ቤት ገብቶ አሳትሞ፣ መንገድ ላይ ወስዶ ለመስቀል አምስት ደቂቃ በቂ ሲሆን መቼስ ለጉድ ነው፡፡)፣ ለሚጠቁሙ ግለሰቦች ሽልማት እንደሚሰጥ ማሳወቁ (አንዲት አደባባይ እንኳን ያልተሻገረን ተጠርጣሪ ለመያዝ ታክቶት ካልሆነ በስተቀር አቅቶት ሽልማት ይሰጣል ማለት መቼስ ዘበት ነው፡፡) አለ የተባለበት ቦታ ሁሉ ተካልቦ መድረስ የቻለ ቢሆንም ተጠርጣሪን ከመያዝ አንጻር ቁልፍ የሚባሉትን ባቡር ጣቢያ እና አውሮፕላን ጣቢያዎች መቆጣጠር አለመቻሉ ቅሽምና ነው፡፡ ብጡል ያጠለቀው ቻይናዊ ፊት እስከ አየር ማረፊያው በሰላም ሊያደርሰው ይችላል ተብሎ ሊታሰብ ቢችልም፤ አውሮፕላን መሳፈር የከተማ ታክሲ የመሳፈር ያህል ቀላል አይደለምና በቀላሉ በፓስፖርት ሊያዝ እንደሚችል ለማንም እንቆቅልሽ xYdlM””ብጡልን ለማስመለጥ የተጠቀመበት ዘዴም ቢሆን ለወሬ እንኳን የማይመች ነው፡፡ አንድ ወንጀለኛ መጥቶ እዚህ መሆኔን ጠቁሙና ተሸለሙ ሲል እመኑ ቢባል እንኳን ስልክ መደወል እንጂ አልጋ ወደ ማከራየት ይሄዳሉ ብሎ ማሰብ ግራ ነው፡፡ ጃፓናዊቷ አስተናጋጅም ብትሆን ይህ በእግር በፈረስ የሚፈለግ ወንጀለኛ ነብሰ-ገዳይ ይሁን አደንዛዥ ዕ አዘዋዋሪ፣ ሳታውቅ አምናው ይዛ ለመውጣት ሽር ጉድ ማለቷ ሳያንሰን አምስት ደቂቃ በማይሞላ ቅጽበት፣ አርቲፊሻል ፊት እና ሽጉጥ ይዛ ከተፍ ስትል፤ ቻይና አገር ሽጉጥ እንደ ከረሜላ በየሱፐር ማርኬቱ የሚሸጥ መስሎ ይታየናል፡፡ በተጨማሪም አስተናጋጇ አንዴ ገራገር፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ ሽጉጧን መዥርጣ የምታስፈራራ ጀግና፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ ለሕጻን እንኳን በማይሆን የቂል ሽንገላ የምትታለል ሆና መቀረ፣ ወጣቱ ደራሲ አሁንም የገ-ባሕርይ አሳሳል ችግር ያለው መሆኑን አመላካች ነው፡፡ (ለሌሎች ያለው ሙያዊ ያልሆነ ንቀትም እንዲሁ፡፡) በአጠቃላይ በመሃሉ የተከሰተችው ጃፓናዊት ለታሪኩ ውበት ሳይሆን ድርቀት ናት ማለት ይቻላል፡፡ (ወግ አጥባቂ ያልሆነችው ደይ ከሚያፈቅራት እና ከምታፈቅረው ተልሚድ ጋር ወሲብ በመፈም /መንገር እንኳን ሳያስፈልጋት/ ከመኖር ይልቅ ለመሞት መምረጥም ቢሆን ታሪኩን አሳዛኝ ፍጻሜ በመስጠት እንዲታወስ ለማድረግ ብቸኛ እድል ለመስጠት ካልሆነ በስተቀር በምንም ምክንያት ሊብራራ የሚችል አይደለም””)አንድ ታሪክ ላይ ምንችክ አለማለቱ መልካም ቢሆንም፤ በተልሚድ መጽሐፍ ውስጥ ሦስት እና አራት ራሳቸውን ችለው መቆም የሚችሉ ታሪኮች በመኖራቸው ለገጽ ፍጆታ ሲባል እንዲህ ተድበስብሶ ታልፏል፡፡ ከላይ በሙገሳው ክፍል ድርብርብ ታሪኮችን መፍጠሩ መልካም እንደሆነ ብገልጽም፣ ድርብርብ ታሪኮቹ በየቦታው እየተንጠባጠቡ መቅረት ግን ከፍተኛ ችግር ነው፡፡ ለምሳሌ፡- አገራዊ ምስጢር የያዙ እንደሆነ በተደጋጋሚ የተነገረን አያ በሽመሉ ጉዳይ እስከመጨረሻው ቢያሳስበኝም እንዳሳሰበኝ እንዲቀር ከማድረግ የዘለለ ሚና አልተወጣም፡፡ (እኔ በግሌ እኚሀን ሰውዬ ቢያጎላቸው እመኝ ነበር፡፡) ጎልታ የነበረችው አናኒያ በአንዴ ደብዝዛ ትጠፋለች፤ “Chapters of My Life” ሳይጻፍ ያልቃል፤ ...(ስለዚህ ጉዳይ ከጓደኛዬ ጋር ስንጨዋወት ..ከመጽሐፉ አጠቃላይ ድርሰት ይልቅ yገ-ባሕርያቱ ድርሰት ይሻል ነበር.. አለኝ፡፡ ሀሳቡ ስለተመቸኝ የጽሑፌ ርዕስ አደረኩት፡፡ እውነትም ደራሲው ከሚደርስ ይልቅ ገ-ባሕርያቱ የጀመሩትን ድርሰት እንዲጨርሱ ሰፊ ጊዜ እና ቦታ ሰጥቶ ቢተዋቸው ይሻል ነበር፡፡)
የይስማዕከ ገ-ባሕርያት አሳሳል ምንጊዜም አንድ እንከን የማያጣው ነው፡፡ በ..ተልሚድ.. ላይም ይህ ነገር ቀጥሏል፡፡ ለምሳሌ፡- የ484.5 ሚሊዮን ብር ንግድ የሚያካሂደው እና በሁሉም ረገድ አድራጊ ፈጣሪ የሆነው ዠንመረቂ፣ በአገሪቱ አሉ ከሚባሉት በጣት የሚቆጠሩ ባለሀብቶች ውስጥ በግምባር ቀደምትነት የሚጠራ ዠንመረቂ፣ ከቤተ-መንግሥት እስከ ሆስፒታል ሁሉንም ለማድረግ ምንም የማይሳነው ዠነመረቂ፤ ከቻይናው ኤምኤስኤስ ቁልፍ ሰው ጋር ጥብቅ ግንኙነት ያለው ዠንመረቂ፤ ...ግቢው ውስጥ የሚገቡ ሁለት ሰዎች (አንዲት ሴትና አንድ ቀኝ እጁ በቅርቡ የተቆረጠበት ቁስለኛ) ሲገቡ ..በወላዲቱ!.. በሚል አንድ ነፍጥ እንኳን ያላነገበ ተራ ዘበኛ የሚጠበቅ ነው፤ የቤት መሥሪያ መሬት ለማግኘት አቅቶት የተልሚድ እናት ጋር የሚርመጠመጥ ነው፤ ለማብሰያነት የሚጠቀመው እንጨት በመሆኑ ኩሽናው በጭስ የጠገበ ነው፡፡ ጨካኙ ዠንመረቂ ከመሃሉ ደግነት ሰፈኖበት ያፈናቀላትን አሮጊት ግቢው ውስጥ ያዘመመ ቤት ሠርቶ ያስጠጋቸዋል፤ እንደገና ደግሞ መርካቶ ገብቶ፣ ከሕዝብ ጋር ተጋፍቶ በሸረበው ሴራ ወደ ኤርትራ እንዲጋዙ ያደርጋል፡፡ በመጨረሻ ነገር ሊገነግንበት የሚችለውን ተልሚድን ባልታወቀ ምክንያት ግቢው ውስጥ እንዲኖር ያደርገዋል፡፡ ሁልጊዜም በኮንትሮባንድ ንግድ ላይ የሚሳተፈው ጠንቃቃው ዠንመረቂ፤ ተልሚድ ..እስር ቤት ብገባ ደስ ይለኛል.. ስላለው ብቻ ሚስቴን ግደልልኝ የሚል ቃል ያመልጠዋል፡፡ ይህን ለማጣፋት የሄደው መንገድ ደግሞ በመኪና ማስገጨት ነው፤ ግን ባለሽጉጦቹ ነብሰ-ገዳዮች በሽጉጥ ግንባሩን ማለት አይቀላቸውም ነበር? እሺ መጀመሪያ በመኪና ቢያቅዱ እንኳን ሳይሳካ ሲቀር ለምን አልተኮሱም? ሆን ተብሎ በታቀደ የመኪና ግጭትስ ቀኝ እጅ ብቻ ተነጥሎ የሚገጨው በምን ተዓምር ይሆን?
..ተልሚድ.. እውነታዎችን ከልቦለድ ጋር አጣምሮ ከመያዙ አንጻር በተለይ ለእውነታዎቹ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልገው ነበር፡፡ ነገር ግን ብዙ ቦታዎች ላይ ግድፈቶች ይበዙበታል፡፡ ለምሳሌ፡- የድሬዳዋ መገኛ ..90083 ኬክሮስ የሚባል ጂኦግራፊያዊ አድራሻ የሰሜን ዋልታ ጫፍ ላይ የሚገኝ ቦታ አድራሻ እንደሆነ ማንም አንባቢ 900 የምትለውን ብቻ አይቶ ሊያውቅ ይችላል፤ ዘጠና ዲግሪ ኬክሮስ ሰሜን ዋልታ ጫፍ ስለሆነ፡፡ 90083 ኬክሮስ የሚባል ጂኦግራፊያዊ ልኬትም ሊኖር አይችልም፡፡ ምክንያቱም ከዲግሪ በኋላ ያለው ቁጥር ከስድሳ በላይ ሊሆን ስለማይችል፡፡ 90083 ማለት ዘጠኝ ሰዓት ከ83 ደቂቃ እንደ ማለት ነው፡፡ 41080 የሚለውም እንዲሁ፡፡) በተጨማሪም ጥር 26 ቀን 1995 ዓ/ም አዲስ አበባ ውስጥ የአፍሪካ ኅብረት ስብሰባ አልተካሄደም፡፡ (ለመጀመሪያ ጊዜ የአፍሪካ ኅብረት ስብሰባ አዲስ አበባ የተካሄደው ይስማዕከ ካለው ጊዜ ከአንድ ዓመት ከመንፈቅ በኋላ፤ ሰኔ 29 ቀን 1996 ዓ/ም ነበር፡፡)..
የተልሚድ ታሪክ ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ ድረስ (የምልሰት ተረኮችን ግምት ውስጥ ሳናስገባ) አንድ ሳምንት እንኳን አይሞላም፡፡ (ተልሚድ አንድ ቀን ሆስፒታል ያድራል፣ አንድ ቀን ደብረዘይት፣ ሦስት ቀን ድሬዳዋ፣ በማግስቱ አዲስ አበባ ላይ ታሪኩ ይጠናቀቃል፡፡) ነገር ግን (ለመገረም እንዘጋጅ) በዚህች አጭር ጊዜ ውስጥ ከቻይና የተጫነው መርከብ ጅቡቲ ደርሷል፡፡ (ኧረ! ንብረቱ አዲስ አበባም ገብቷል! ከቻይና በአውሮፕላን የመጣው ብጡልና በመርከብ የመጣው የኮንትሮባንድ ንብረት እኩል ይደርሳሉ፡፡) በዚህ ተመሳሳይ ጊዜ ውስጥም ደይ እናቷን መለየት ያቅታታል፡፡
እናቷ ምንም ያህል ተጎሳቆለች፣ ተጎዳች ብለን ልናስብ ብንችል እንኳን፤ የሰው አካላዊ (physiological) ሁኔታ በሳምንት ውስጥ ልጅ እናትን መለየት እስኪቸግራት የሚበላሽ ነው ተብሎ አይታሰብም፡፡ በመጨረሻ፣ መቼም ደራሲው ከሚማረው ትምህርት አንጻር ስለኬሚካሎች ብዙ እውቀት ሊኖረው እንደሚችል ይታሰባል፡፡ ነገር ግን ተልሚድን መርዝ ጠጥቶ እየሞተ አንቆ መያዝ የሚችል፤ ምንም ድምጽ ሳያሰማ መፈንገል የማይሳነው አድርጎ ማቅረቡ ድንግርግር አድርጎኛል፡፡ ምንስ ቢሆን ነፍስ ሲወጣ በውስን እርምጃዎች እርቀት ያለ ሰው እንኳን ሳይሰማ ሊሆን ይችላል እንዴ?
በአጠቃላይ ተልሚድን ከጀማሪ እንኳን የማልጠብቀው ዓይነት ሆኖ ነው ያገኘሁት፡፡ (ለነገሩ የመጀመሪያው ነው፡፡ ግን ወይ ማብሰል ወይም መተው ነበረበት ብዬ አምናለሁ፡፡) ያለፉት ሁለት መጽሐፍቱ ምንም አላስደስተኝ ሲሉ ጊዜ ምናልባት የገነባው ስም በስህተት እንዳይሆን በመስጋት፣ ..ዴርቶጋዳ..ን ከለስኩት፡፡
ጥሩ ነው፤ ከዳን ብራውን ጋር ካለው መቀራረብ በስተቀር፡፡ (ይህንንም ምናልባት የነሸጠኝ (inspire ያደረገኝ) በሚል ዳን ብራውንን ቢጠቅሰው ኖሮ ሊቀር የሚችል ነበር፡፡) ታዲያ ይህ ሰው ለምን ቁልቁል መንደርደር አበዛ? የሚል ጥያቄ መጣብኝ፡፡ ለጊዜው ያገኘሁት መልስ አንድ ነው፤ ባለሙያን አለማማከር፡፡ የሁለቱም መጻሕፍት ችግር ለአንባቢ ከመድረሳቸው በፊት ..በጥበብ ወጌሻ.. አለመታሸታቸው ነው፡፡ የ..ዴርቶጋዳ.. መግቢያ በኢትዮጵያ ሥነ-ጽሑፍ ጥሩ አሻራ ያላቸውን ሰዎች በማመስገን የተሞላ ነው፡፡
ስብሀት ገ/እግዚአብሔር፣ የሻው ተሰማ፣ በእውቀቱ ስዩም፣ እንዳለጌታ ከበደ ... ሁሉም ገንቢ አስተያየት እንደሰጡት ጠቅሶ አመስግኗቸዋል፡፡ በ..ተልሚድ.. ግን ምስጋና የተቸረው አንድ አካል ብቻ ነው፤ ባዶ ወረቀት፡፡ (ለነገሩ ያለማንም ቡራኬ ብዙ ሺህ ኮፒ መሸጥ የሚችል ሐፊ፤ ለምን ያማክር!)

 

Read 5320 times Last modified on Saturday, 20 August 2011 11:03