Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 20 August 2011 11:08

የ..ንሥር ዐይን.. ከ10 ዓመት በኋላ ታተመ

Written by 
Rate this item
(2 votes)

ደራሲ ፍቅረማርቆስ ደስታ የዛሬ 10 ዓመት አሳትሞት የነበረውን ..የንስር ዐይን.. የተሰኘ ም ልብወለድ መጽሐፍ ለሁለተኛ ጊዜ አሳትሞ ለገበያ አቀረበ፡፡ በማህሌት አሳታሚነት የታተመው ይሄ መጽሐፍ በ35 ብር እየተሸጠ ነው፡፡ የኬምስትሪ መምህር የነበረው ደራሲ ፍቅረ ማርቆስ፤ ..ከቡስካ በስተጀርባ..፣ ..ኢቫንጋዲ..፣ ..የዘርሲዎች ፍቅር.. እና ..አቻሜ.. በተሰኙት የልብወለድ ሥራዎቹ እንዲሁም  Land of The Yello Bull በተሰኘው የከቡስካ በስተጀርባ ትርጉም መጽሐፍ እንዲሁም፡፡ በሌላ በኩል የኦሾ መጽሐፍ በቴዎድሮስ ካሬ እና በይልቃል አያሌው ..የመኖር ጥበብ.. በሚል ርዕስ ለንባብ በቃ፡፡ የመጽሐፉ ዋጋ 27 ብር እንደሆነ ታውቋል፡፡
..የራስ ምታት.. ነገ ይመረቃል
በአቶ አስመሮም ወልደጊዮርጊስ የተጻፈው ..የራስ ምታት.. የሳይንስ ልቦለድ መጽሐፍ ነገ ከቀኑ 10 ሰዓት ተኩል በሩሲያ ሳይንስ እና ባህል ማዕከል እንደሚመረቅ የኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር አስታወቀ፡፡ማህበር ከዚህም ሌላ በተመሳሳይ ስፍራ ትናንትና የሥነ ጽሑፍ ምሽት አቅርቧል፡፡ በምሽቱ አንጋፋና ወጣት ፀሐፍት ሥራዎቻቸውን አቅርበዋል፡፡

Read 7426 times