በመዋዕል ታደሰ ተፎ የተዘጋጀው ..የሸረሪት ድር.. የአማርኛ ፊልም ነገ ከቀኑ 8 ሰዓት በዋነኝነት በሐርመኒ ሆቴል የሚመረቅ ሲሆን በአዲስ አበባ ፊልም ቤቶችና በሌሎች ከተሞች በተመሳሳይ ዕለት እንደሚመረቅ ተገለፀ፡፡ የ100 ደቂቃ ልብ አንጠልጣይ ፊልሙን ሰርቶ ለማጠናቀቅ ሁለት ዓመት እንደፈጀ አዘጋጆቹ ተናግረዋል፡፡ አሸባሪነትን ብጡ በማድረግ በተሰራው ፊልም አርቲስት ችሮታው ከልካይ፣ እንቁስላሴ ወ/አገኘሁ፣ አልማዝ ኃይሌ፣ ጃንክሎዝ ሮዜል፣ ሰብለ ተፈራ፣ ታጠቅ መለሰና ሌሎችም ተውነዋል፡፡