Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Print this page
Saturday, 20 August 2011 11:18

የቶም ቆይታ በረጅም እቅድ ሊታይ ይገባል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

የኢትዮጵያና ሶማሊያ ጨዋታ ጦርነት፤ ሰላምና ዓለም ዋንጫን ያገናኘ ተባለ
የኢትዮጵያ  ብሔራዊ  ቡድን  በዓመቱ በዓመቱ መጨረሻና በዓዲሱ ዓመት መግቢያ ላይ 2 ቀሪ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ግጥሚያዎችን የሚያደርግ ሲሆን ለ20ኛው የዓለም ዋንጫ በቅድመ ማጣርያ ከሶማሊያ ጋር መገናኘቱ ትኩረት ሳበ፡፡ በቀሪዎቹ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ግጥሚያዎች  የማለፍ ዕድሉ የተመናመነው ብሔራዊ ቡድኑ  በተፎካካሪነት ከፍተኛ ልምድ እንደሚያገኝ ቢጠበቅም  በፌዴሬሽኑ በኩል የወዳጅነት ጨዋታዎች እንዲያገኝና በረጅም እቅድ ሊታሰብለት አለመቻሉ ይስተዋላል፡፡ አሰልጣኝ ቶም ሴንትፌይት ወደ ቤልጅየም ለዕረፍት ተጉዘው ከተመለሱ በኋላ ላለፉት 4 ሳምንታት የተጠናከረ ልምምዱን በደብረ ዘይት ሲሰራ ለቆየው ብሔራዊ ቡድኑ በምክትል አሰልጣኝነት  ሰውነት ቢሻው ተሹመዋል፡፡

ቤልጅማዊው ቶም ሴይንት ፌይት በቅርብ ጊዜ ከፊፋ መጽሔት ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ኢትዮጵያ ውጤታማ የእግር ኳስ አገር ባትባልም ለወደፊቱ ከታላቅ ቡድኖች ተርታ የምትሰለፍበት ከፍተኛ አቅም እንዳላት ተናግረዋል፡፡ አሰልጣኙ በቃለ ምልልሱ ላይ ሲናገሩ ኢትዮጵያ በአትሌቲክስ ስፖርት ከዚህ ለምሥራቅ አፍሪካና ለመላው አፍሪካ ፈር ቀዳጅና ታላቅ ስኬት ያስመዘገቡ አትሌቶችን በማፍራት እንደምትታወቅ  ገልው በአገሪቱ እግር ኳስ እጅግ ተወዳጅ ስፖርት መሆኑን በመጠቆም በረጅም ጊዜ እቅድ መሥራት ከተቻለ  ተመሳሳይ ውጤት ሊኖራት ይችላል ብለዋል፡፡
በአሰልጣኝነት ስራቸው   እስከ አፍሪካ ዋንጫው የማጣርያ ውድድር መጨረሻ እንደሚቆዩ የሚነገረው ቶም ምን ያህል ወርሃዊ ደሞዝ እየታሰበላቸው እንደሆነ በግል አልታወቀም፡፡ በኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ታሪክ 5ኛው የውጪ አገር ዜጋ አሰልጣኝ የሆኑት ቤልጅማዊው ከዚህ ቀደም ሰርቢያዊ፤ ሁለት ጀርመናዊ ፈረንሳዋአንድ ስኮትላንዳዊ አሰልጣኝ እንደቆዩት በ1 ዓመት ኮንትራታቸው ሊያበቃ እንደሚችል መገመቱ ደግሞ በረጅም እቅድ የመስራት እቅዳቸውን ያሰናክለዋል፡፡
በሌላ በኩል በ2014 እ.ኤ.አ ብራዚል ለምታስተናግደው 20ኛው የዓለም ዋንጫ ከሁለት ሳምንት በፊት በአፍሪካ ዞን በቅድመ ማጣርያ በወጣው ድልድል ኢትዮጵያ ከሶማሊያ መመደባቸው እያነጋገረ ነው፡፡ በሳምንት ጊዜ ውስጥ በሚደረጉ የደርሶ መልስ ጨዋታዎች ያሸነፈው ወደ ቀጣዩ የምድብ ማጣርያ በመግባት ደቡብ አፍሪካ ቦትስዋና እና መካከለኛው አፍሪካ ወደ የሚገኙበት ምድብ ይቀላቀላል፡፡ በዚሁ የዓለም ዋንጫ ማጣርያ ኢትዮጵያን ከሶማሊያ ያገናኘውን የቅድመ ማጣርያ ግጥሚያ እጣ ያወጣው ሮናልዶ ነበር፡፡ ጨዋታው ጦርነት፤ሰላምና የዓለም ዋንጫን ያገናኘ ብሎ የዘገበው የኢኤስፒኤንጋዜጠኛ ነው፡፡ ሁለቱ አገራት በጉርብትናቸው፤ ከ60 ዓመታት በኋላ የከፋው ረሃብ ስለገጠማቸው፤ በታሪካቸው ሁለት ጊዜ በጦርነት በመዋጋታቸው፤ ሶማሊያ በእርስ በእርስ ጦርነት ፈራርሳ ኢትዮጵያ ደግሞ ሰላም አስከባሪ በመሆን በያዙት ሚና የእግር ኳስ ግጥሚያቸውን ትኩረት እንዲስብ አድርጎታል ብሏል ዘገባው፡፡ በ2003 እኤአ በአሰልጣኝ አስራት ሃይሌ የተመራ ቡድን የሴካፋ ሻምፒዮን ከሆነ በኋላ በዓመቱ ጀርመናዊ አሰልጣኝ ተቀጥረው በተመሳሳይ ውድድር ሶማሊያ በማሸነፍ ያስመዘገበችው ስኬት ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ሞራል መነካት አስተዋኦ እንደነበረውም ያትታል፡፡
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በታሪኩ ከተመዘገቡ ክብረወሰኖች በተለይ በፈረንሳይ ቅኝ ግዛት በነበረችው ሶማሊያ ላይ የወሰደው ብልጫ የጐላ ሆኖ ይታያል፡፡ ብሄራዊ ቡድኑ የመጀመርያ ኢንተርናሽናል ጨዋታውን ከ64 ዓመታት በፊት ለማድረግ 5ለ0 ያሸነፈውና በሰፊ የግብ ልዩነት 10ለ2 ያሸነፈው በፈረንሳይ ቅኝ የነበረውን የሶማሊያ ብሄራዊ ቡድንን ነው፡፡ በዓለም ዋንጫ የ80 ዓመታት በተደረጉ 19 ዓለም ዋንጫዎች የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በ12 የዓለም ዋንጫ ማጣርያ ውድድሮች አለመግባቱ፤ በ2 ከተሳትፎ መታገዱና በተካፈለባቸው የ5 ዓለም ዋንጫ ማጣርያዎች ለማለፍ ሳይችል ቀርቷል፡፡

 

Read 4301 times Last modified on Saturday, 20 August 2011 11:24

Latest from