Saturday, 27 August 2011 13:55

ዓለምን የቀየረ ዝነኛ ተጓዥ

Written by  ጥላሁን አክሊሉ
Rate this item
(0 votes)

ክፍል ሁለት
ኢብን ባቱታ ከተወለደበት ሞሮኮ ተነስቶ የሰሃራ በረሃን አቋርጦ ቻይና ድረስ ሲዘለቅ በሄደበት ቦታ ሁሉ ሰላምን፣ ፍቅርን፣ አንድነትን፣ መተሳሰብንና መከባበርን ሰብኳል፡፡ የታይም መጽሔት ኤዲተር ሚካኤል ኢሊዮት ..አሁን ዓለማችን በትራንስፖርት፣ በንግድ፣ በባህል፣ በስፖርት፣ በኢንተርኔትና በሌሎች ዘርፎች ወደ አንድ መንደርነት ተቀይራለች ብለን ከምንለው በላይ ኢብን ባቱታ ዓለምን አቀራርቧት ነበር፡፡ በመሆኑም ኢብን ባቱታ የሞሮኮ ዜጋ ብቻ ሳይሆን ዓለም አቀፍ ሰው ነው.. በማለት ተናግሯል፡፡ ይህ የሆነው ከ650 ዓመት በፊት ነው፡፡

በነገራችን ላይ ባለፈው ሳምንት እትማችን ላይ ኢብን ባቱታ በ1940 ተወለደ የሚለው በስህተት በመሆኑ በ1304 ተብሎ ይስተካከል፤ ወደ መካና ኮንስታንቲኖፖል ያደረጋቸው ጉዞዎቹም በ1326 እና በ1330 ነው፡፡
በሌላም በኩል ኢብን ባቱታ ለሰው ልጆች ሰብዓዊ መብትና ክብር አጥብቆ የሚከራከር ሲሆን፣ ጥቃቶችን ይቃወም ነበር፡፡ በተለይ በማል ዴቪስ ሴቶች በባርነት ሲሸጡና ሲለወጡ እንዲሁም ተገቢ ያልሆነ ግፍ ሲፈምባቸው በማየቱ ስህተት መሆኑን አስተምሯል፡፡
በእንግሊዝ ሊቨርፑል ዩኒቨርስቲ የፖለቲካ ፕሮፌሰር የሆኑት ኢያን ሩድ ሲናገሩ፤ ..ኢብን ባቱታ በደረሰባቸው ቦታዎች ሁሉ ሕዝቡ በደስታ የሚቀበለው ከመሆኑም በላይ ማረፊያና አገልጋይ የሆኑ ወንዶችና ሴቶች ይመደብለት ነበር፤ በአንድ አገር ላይ ቆይታውን ጨርሶ ሊጓዝ ሲልም እስከተወሰነ መንገድ ድረስ የሚሸኙት ሰዎች ይሰጠው ነበር.. ብለዋል፡፡
ኢብን ባቱታ 120 ሺህ ኪሎ ሜትር በ30 ዓመታት ውስጥ ሲጓዝ፣ በሕይወቱ በርካታ አስገራሚና አስደናቂ ነገሮችን እንደተመለከተ በጉዞ ማስታወሻው መጽሐፍ ላይ ገልል፡፡
በጉዞው ወቅት አደገኛ ነገሮች እንዳጋጠሙትም ገልል፡፡ ወደ እስያ ሲሄድ ያጋጠሙትን የባህር ላይ ዘራፊዎች በጥበብ ያመለጠበት እንዲሁም በተለያየ ስፍራዎች ሽፍቶችን ተደብቆ እንዴት እንዳመለጣቸው ይናገራል፡፡ በዚያን ዘመን በካይሮ ከተማ ወጣ ብሎ በሚገኝ ቦታ በየዓመቱ ከ20ሺ በላይ ሰዎች በሽፍቶች ይገደሉ ነበር፤ ነገር ግን ኢብን ባቱታ ይህንን ቦታ በጥንቃቄ አልፎታል፡፡ ከእርሱ በፊትም ሆነ በኋላ የነበሩ አንዳንድ ተጓዦች ሕይወታቸው በሽፍቶች ጠፍቷል፡፡
በራስ የመተማመን መንፈስ፣ እምነት፣ ናት፣ አዎንታዊ አስተሳሰብ፣ ስለወደፊቱ ጊዜ ብሩህ አመለካከት መያዝ (optimist) እና ቁርጠኛ በመሆን ፍም ሊሞከር ይቅርና ሊታሰብ የማይችለውን ጉዞ ያደረገው ኢብን ባቱታ፤ ድንበር የማይገድበው ተጓዥ ነበር፡፡ በጉዞው ወቅት ያየውንና ያጋጠመውን ነገር በደንብ በማስተዋል እና በመጠየቅ ሳይረዳ አያልፍም ነበር፡፡ ይህም በሄደባቸው አገሮች ሁሉ የሰዎችን ባህል፣ አኗኗር፣ ልማድና ታሪካዊ ቦታዎች በደንብ እንዲረዳ አስችሎታል፡፡ በእስልምና ቅዱስ የሚባሉ ስፍራዎችንና ሌሎች ታሪካዊ ቦታዎችንም ሲመለከት ሪሂላ ብሎ በሚጠራው በጉዞ መጽሐፉ ላይ ያሰፍራል፡፡ ኢብን ባቱታ ሃይማኖታዊና ታሪካዊ ቦታዎችን በመጽሐፉ ላይ በማስፈሩ Religious anthropologist ሊባልም ይገባል በማለት አንዳንድ ምሁራን ተናግረዋል፡፡
ኢብን ባቱታ በተለያየ አገሮች ስላያቸው ጠንቋዮችና አስማተኞችም ጠቅሷል፡፡ በኢንዲያን ውቅያኖስ ሪፐብሊክ አካባቢ ደግሞ ልክ በሮማውያን ዘመን እንደነበረው የታሰሩ ወንጀለኞች ከአደገኛ እንስሳት ጋር በባዶ እጅ እንዲታገሉ ሲደረግ ተመልክቷል፡፡ ለምሳሌ በማልዴቪስ አንድ ሰው ከዝሆን ጋር ሲታገል፣ ዝሆኑ ሰውየውን ሰባብሮ ሲገድለው አይቷል፡፡ በወቅቱ በአንዳንድ አገሮች ዜጎች ለንጉሳቸው ክብር ሲሉ ራሳቸውን መስዋዕት ሲያደርጉም አስተውሏል፡፡ በአፍሪካዊቷ አገር ማሊ አንድ ግለሰብ ለንጉሱ መስዋዕት ለማቅረብ ሲል አንገቱን በካራ ቆርጦ መጣሉን ባቱታ ገልል፡፡
ይሁን እንጂ እነዚህ ሁሉ ድርጊቶች ኢብን ባቱታን አስቆጥተውታል፡፡ ቆርጦ ከተነሳበት ዓላማ ጋር የሚጻረር ከመሆኑ ባሻገር ለሰው ልጅ የሚሰጠው ዝቅተኛ ክብር አሳዝኖታል፡፡ ባቱታ እነዚህን አሳዛኝ ጉዳዮች ዝም ብሎ አልተመለከተም፡፡ በሄደበት ቦታ ሁሉ ለወራትና ለዓመታት እንዲቆይ የሚያደርገውም የእርሱን የላቀ እውቀትና ሰብዕና ለሰዎች በማሳወቅ ብሩህ አእምሮ እንዲኖራቸው ለማድረግ ነው፡፡ ይህም በብዙ ስፍራዎች ለውጥ እንዲያመጣ አስችሎታል፡፡
በአሜሪካ ሳንፎርድ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ ተመራማሪ የሆኑት ማርክ ስቱዋርት ..ኢብና ባቱታ በዓለም ላይ ለራሳቸው ሳይሆን ለሌሎች ኖረው ካለፉ ጥቂት ሰዎች ውስጥ አንዱ ነው፡፡ በ14ኛው ክ/ዘመን ቢኖርም ጥልቅ የሆኑት አስተሳሰቡና አርቆ አስተዋይነቱ እስከ ዘመናችን የሚሻገር ነው፡፡ ከምንም በላይ ደግሞ ያለውን ችሎታ ለሌሎች ለማካፈል ሲል ህይወቱን አደጋ ላይ የሚጥሉ ጉዞዎችን ማድረጉ ነው፡፡ ኢብን ባቱታ ዛሬ ካሉ ቱሪስቶች በጣም የላቀ ነው፡፡ በእውነት ከኢብን ባቱታ ዘመን በኋላ አሁን ያለችው ዓለማችን ምን አላት ምንስ አጥታለች? ብለን መመርመር አለብን.. በማለት ተናግረዋል፡፡
ኢብን ባቱታ ምንም እንኳን በተፈጥሮ ትሁትና ጥሩ ሰው ቢሆንም የተለያዩ አገራት መሪዎች ባላቸው የተዛባ አስተሳሰብ ተግሳጽ ሰጥቷቸዋል፡፡ ለምሳሌ በማሊ ውስጥ ንጉሱ ኢብን ባቱታን በመጥፎ አይን ያየው ከመሆኑ በላይ መጠለያ ሊሠጠው አልፈቀደም ነበር፡፡
በዚህን ጊዜ ባቱታ ንጉሱን መጥፎ መንፈስ አለብህ ብሎ ሲናገረው፣ ንጉሱም ኢብን ባቱታ በሕዝቡ ዘንድ ያለውን ተወዳጅነት ያውቅ ስለነበረ መኖሪያ ቤት ሰጥቶታል፡፡
ወደ ሕንድ በሄደበት ወቅት ደግሞ በወንጀለኞች ላይ የሚፈፀሙ ግድያዎችን ወንጀለኞቹ 33.000 ጊዜ እንዲሰግዱና እንዲለቀቁ በማለት፣ የሞት ቅጣቱን በፀሎት ለውጦላቸዋል፡፡
ከ5ኛው መቶ ክ/ዘመን አንስቶ እስከ 10ኛው ክ/ዘመን የነበረው ጊዜ የጨለማው ዘመን (The darkest age) እየተባለ የሚታወቅ ሲሆን በዚህም ዘመን ሰዎች አእምሯቸውን በመጠቀም በፈጠራና በማኅበራዊ ዕድገቶች ላይ ከማተኮር ይልቅ ጭፍን አስተሳሰቦችና እምነቶች የተንሰራፉበት ነበር፡፡ ከተለያዩ የፍልስፍናና እና የታሪክ አስተምህሮቶችም ይልቅ ጨለምተኝነት ነገሰ፡፡ በዚህ ዘመን ታዋቂ የነበሩት የሮማ፣ የግሪክ፣ የኮንስታንትኖፕል እንዲሁም የአክሱም መንግስት ስልጣኔ ሳይቀር ተንኮታኮቱ፡፡
ነገር ግን ከጨለማው ዘመን በኋላ የህዳሴ ዘመን (The Renaisance period) ሲተካ ወደ ኋላ ቀርቶ የነበረው የዓለም ስልጣኔ እንደገና ማበብ ጀመረ፡፡ የምህንድስና ጥበብ፣ የሂሳብ፣ የአርክቴክት፣ የኪነጥበብና የፍልስፍና ጥበቦች በዓለም መድረክ ላይ እንደገና ብቅ አሉ፡፡
በህዳሴ ዘመን ዓለምአቀፍ አስተሳሰቦችና ግንዛቤዎች እንደገና ማቆጥቆጥ ጀመሩ፤ መካከለኛው ክ/ዘመን ተብሎ በሚታወቀው በዚህ ዘመን የእምነት ነፃነቶችና ተቃውሞዎችም ተስፋፍተዋል፡፡
በክርስትና እምነት ውስጥ ለዘመናት የበላይነትን ይዛ የቆየችው የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ላይ ማርቲን ሉተር ኪንግ ለመጀመሪያ ጊዜ ተቃውሞ በማሰማት ራሱን ከቤተክርስቲያኒቱ አግልሏል፡፡ ከህዳሴ ዘመን አስቀድሞ ኃያላን መሆን የጀመሩት ሙስሊሞች ህዳሴው ዘንም በእነርሱ ወርቃማ ዘመን እንደነበር ይናገራል፡፡ ሙስሊሞች በስልጣኔያቸው ከሌላው ዓለም ልቀው የነበረበት ዘመን ነበር፡፡
በተጨማሪም ሙስሊሞች ከምዕራባዊያን በላይ ኃያላን ነበሩ፡፡ ሙስሊሞች ራሳቸውን ዓለምአቀፍ ማኅበረሰብ አድርገው ይመለከቱ ነበር፡፡ ከሞሮኮ ተነስቶ ጠቅላላ የሙስሊም አገሮችን በመዞር እስከ ሕንድና ቻይና ድረስ የዘለቀው ዝነኛው ተጓዥ ሃጂ ኢብን ባቱታ፤ የሙስሊሞችን አንድነትና ሕብረት የበለጠ አጠናክሮታል፡፡ ሙስሊሞች ሃይማኖታቸውን፣ ባህላቸውንና ልማዶቻቸውን አጥብቀው እንዲይዙ ያስተምር የነበረ ሲሆን፣ መልካም እሴቶቻቸውንም ሙስሊም ላልሆኑት ማኅበረሰቦች እንዲያጋሩ ይናገር ነበር፡፡
ኢብን ባቱታ ለሙስሊም አገሮች ያስተዋወቃቸው ምግቦች ዛሬም ድረስ በብዙ አገሮች ይዘወተራሉ፡፡ ለምሣሌ በቤሩት በየዓመቱ በሚከበረው የምግብና የሬስቶራንት ኢንዱስትሪ ትሬድ ፌስቲቫል ላይ የምግብ ባለሙያዎች (ሼፍ) ምርጥ ምርጥ ምግቦችን ለጐብኝዎች ያቀርባሉ፡፡ ከሁሉም ጣፋጭ ምግብ እንደሆነ የሚገለፀው ደግሞ ..ሃሪሳ.. የተባለው ምግብ ሲሆን ይህም በብዙ የምግብ ባለሙያዎች በፌስቲቫሉ ይቀርባል፡፡ ይህ ምግብ ከስጋ፣ ከስንዴ እና ከቅመማ ቅመም ጋር ተደባልቆ የሚዘጋጅ ነው፡፡ የዚህ ምግብ ፈጣሪ ደግሞ ኢብን ባቱታ ነው፡፡
የምግብ አዘገጃጀት መጽሐፍ ደራሲና የምግብ አመጣጥ ታሪክ ምሁር ክላውዲያ ሮዳን ሲናገሩ ..ሃሪሳ የሙስሊም አለም ጣፋጭ ምግብ በመሆን የተጀመረ ቢሆንም ከመካከለኛው ክ/ዘመን ጀምሮ አይሁዶች ይመገቡት ነበር፡፡ በ20ኛው ክ/ዘመን ደግሞ የኢራቅ አይሁዶች፣ ሙስሊም የምግብ ባለሙያ በመቅጠር ከስንዴና ከስጋ ጋር በመደባለቅ ያበስሉላቸው ነበር፡፡ የየመን አይሁዳዊያን ደግሞ አሁን ድረስ ይህንን ምግብ ይመገባሉ.. ብለዋል፡፡ ሮዳን አያይዘው ሲገል፣ በሶሪያና በፓኪስታን በጣም ተወዳጅ ምግብ እንደሆነና፣ የምስራቃዊያን ክርስቲያን ሕዝቦችም እንደሚወዱት ተናግረዋል፡፡ ይህን ምግብ በኢራቅና በሊባኖስ የሚገኙ ሺአይት ሙስሊሞች ደግሞ ሰማዕት ሆኖ ለሞተው የነብዩ መሐመድ የልጅ ልጅ ለሆነው ኢማም ሁሴን መታሰቢያነት አብስለው ይመገባሉ፡፡ በተጨማሪም በሊባኖስና በአንዳንድ ቦታዎች ..አሹራ.. ለተባለው የሺአይቶች በዓል ቀን ይበላል፡፡
ኢብን ባቱታ የቻይና ጉዞውን ካጠናቀቀ በኋላ እ.ኤ.አ በ1348 ወደ ሞሮኮ እየተጓዘ እያለ ሁለተኛውን የሃጂ ጉዞውን እግረ መንገዱን ወደ መካ አደረገ፡፡ በወቅቱ መካከለኛውን ምስራቅና አውሮፓን ያጥለቀለቀው የሳምባ ምች ወረርሽኝ በሽታ ስለነበር፣ በበሽታው የተያዙ ሰዎችንም አክሞ አድኗል፡፡ በሽታው የአውሮፓን 1/3ኛ ሕዝብ ከጨረሰ በኋላ ጋብ አለ፡፡ ከበሽታው መጥፋት በኋላም ኢብን ባቱታ የ30 ዓመት ጉዞውን አጠናቆ እ.ኤ.አ በ1354 ወደ አገሩ ሞሮኮ ገባ፡፡
እርሱ መካ እያለም እናቱ ሞሮኮ ውስጥ በወረርሽኙ ሞተው ነበር የደረሰው፡፡ እስከ ሕይወቱ ሕልፈት ድረስም በጉዞው ወቅት ያጋጠሙትንና የሚያስታውሳቸውን ነገሮች ሁሉ በሪሂላ (በጉዞ መጽሐፍ) ላይ አስፍሯል፡፡ ከተለያዩ አገሮች ያገኛቸውን ስጦታዎች በመኖሪያ ቤቱ አሰባስቧል፡፡ ኢብን ባቱታ ከ650 ዓመት በፊት ቢኖርም እስከዘመናችን የሚዘልቅ አሻራውን ጥሎ አልፏል፡፡
ዝነኛው ተጓዥ፣ የሃይማኖት አስተማሪ፣ የስነምግባር ሊቅ፣ yGlÖÆላይz¤>N ፈር ቀዳጅ፣ የሕግ ሰው፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች፣ ሪሊጂየስ አንትሮፖሎጂስት፣ በማህበራዊና ልማዳዊ እሴቶች ላይ ተጽእኖ ፈጣሪ፣ ትሁትና የዋህ እንዲሁም ሰላማዊ ሰው በመሆን በተወለደ በ73 ዓመቱ ሞሮኮ ውስጥ አረፈ፡፡

 

Read 6384 times Last modified on Saturday, 27 August 2011 13:59