Print this page
Saturday, 03 September 2011 12:00

ሀሳባችን ሁሉን አቀፍ ይሁን!

Written by  ጤርጢዮስ - ከቫቲካን..
Rate this item
(1 Vote)
  • ..መንግሥቱ ሁሉን ትገዛለች!..

መነሻዬን ..የዲሞክራሲ     ዳዴና ክርስትና በኢትዮጵያ.. ሲል ግራ ስሜቱን በገለልን፣     የሥነ-መለኮት ተማሪና የበዕውቀቱ ስየም ወዳጅ ነኝ ያለን ፀሐፊ ላድርግ፡፡ ለመጻፍ የተነሳው ከበዕውቀቱ ጋር ያደረገው ውይይት ምክንያት መሆኑን ቢነግረንም፣ ተነስቶ ከነገረን ቁም ነገር በላይ ግን የአማኙን ሃሳብ በማጣጣል ለበዕውቀቱ ያለውን ታማኝነት ለማንፀባረቅ መሻቱ የበለጠውን ስፍራ ይዟል፡፡ ..ዶክተር.. የሚለው ማዕረግ የብዕር ስም እስኪመስለው ድረስ፣ በተማረ ሰው አፍ እግዚአብሔርን የመፍራት ወሬ መስማቱ ግርታን የፈጠረበት ይሄ ፀሃፊ ግን የሥነ-መለኮት ተማሪ ነኝ ባይል እንዴት ጥሩ ነበር፡፡ .

.የዲሞክራሲ መብቶችና እሴቶች ከክርስትና ጋር ተቃርኖ የላቸውም፡፡.. የሚለን ፀሃፊው፤ ክርስትናን እንደ ጉዳዩ የሚቆጥርን ሰው እያደነቀ፣ ..እግዚአብሔርን እንፍራ.. የሚልን አማኝ እየነቀፈ መጻፉ በ..ዝነኛ.. ላይ ተንጠላጥሎ እወቁኝ ማለትን ጨርሶ ያልጣለ በመሆኑ እንዲህ ዓይነቱ ሰው ..አማኝ ነኝ.. ብሎ እዚህ አውድማ ላይ ባይሰለፍ እንዴት ደግ ነበር፡፡
ከክርክር ጭብጦቹ አንዱንም እንኳ ጠቅሶ ሳይነግረን ግና ..በዕውቀቱ ያቀረበው ሙግት ከነባራዊ ሁኔታዎች ጋር የተዛመደ በመሆኑ ይበል የሚያሰኝ ነው፣ ዶ/ር ፍቃዱ ያቀረቡት ሃሳብ ድምር ውጤት ግን እግዚአብሔርN መፍራት በመሆኑ ለእርሳቸው የሚስማማው ሙያ ሰባኪነት ነው፡፡.. የሚለው የ..ሥነ-መለኮት.. ተማሪው፤ ይሄ ዓለም ሰውን ከፍና ዝቅ አድርጐ የሚያይበትን መነጽር እስካሁንም ያላወለቀ፣ እምነቱም እግዚአብሔርN መፍራትን ያላስቀደመ ነውና ጊዜውን በከንቱ ባያቃጥል ይሻለዋል፡፡ ለማንኛውም የፀሐፊው መነሻ የበዕውቀቱን ተገዳዳሪ ማሳነስ ስለሆነ በአፍሪካ መሪዎች ፈሪሃ እግዚአብሔር መጥፋት የአፍሪካ ችግሮች አንዱ አካል መሆኑን የመጠቆሙ ስህተት ምን እንደሆነ ትንፍሽ አላለም፡፡ በዕውቀቱን ከእውቀቱ መለየት የተነሳነው ፀሐፊ፤ ብልጣ ብልጦቹ የአፍሪካ መሪዎች የህዝቡን ፈሪሃ-እግዚአብሔር ተግነው የራሳቸውን አጀንዳ ሲፈጽሙ መኖራቸው ለበዕውቀቱ አጠቃላይ ሃሳብ እንደ ዋነኛ ግብዓት ማገልገላቸው እንኳ ገና አልተገለጠለትም፡፡
..ከበዕውቀቱ ጋር ባደረግሁት ውይይት ጭብጥ ውስጥ ያገኘሁት ሀቅ (በዕውቀቱ) ኢትዮጵያና - ኢትዮጵያዊnT በልቡ ውስጥ ትልቅ ቦታ መያዛቸውን ነው፡፡.. የሚለን የሥነ-መለኮት አጥኚ፤ በዕውቀቱ ኢትዮጵያን እስከወደደ ድረስ የፈለገውን ቢል ሊወቀስም ሊከሰስም አይገባውም ባይ ነው፡፡ ሲያሳፍር፡፡ ሀገርን በመውደድ ተገቢነት እስማማለሁ፡፡ ሀገሬንም እወዳለሁ፣ ሆኖም እምነትን የተመለከቱ ውይይቶች ላይ ከሀቁ የማፈግፈጊያ ስልት ሲደረግ በፍም አይመቸኝም፡፡ እግዚአብሔር አገሬንና ሕዝቤን በነገር ሁሉ እንዲባርክ ብመኝም ዜግነቱን ኢትዮጵያዊ የማስመሰል የትኛውም ጥረት ግን ሊሆን ስለማይችል አልቀበለውም፡፡ ምናልባትም በዕውቀቱን ወዳለማመንና ወደተሳሳተ ድምዳሜ የመራው እንዲህ ዓይነቱ የነገር አገላለፃችን ሊሆን ይችላል፡፡
ለ..ሥነ-መለኮቱ.. ሰው ፍንጭ ለመስጠትም ሰርክ በበዕውቀቱ ብዕር የሚብጠለጠለው እግዚአብሔር# የኢትዮጵያ ነገሥታትን ገታ የተላበሰ፣ የህዝቧን ባህል የወረሰ ነው፡፡ ሞራላዊነቱም ሆነ ኢ-ሞራላዊነቱ የሚመዘነው በእነርሱ ጠባይ ነው፡፡ ይሄ እግዜር ደግሞ ላይጠቅማት የተጠጋችው፣ ከድህነቷ ያወጣት ዘንድ ያልቻለ አቅመ ቢስ አሊያም ለነጋ ጠባ ተማኖዋ መልስ የነፈጋት ጨካኝ ነው፡፡ ..አለ.. ብላ ከሥሩ አትጠፋም እንጂ በህጐቹ ተብትቦ ወደ ኋላ ያስቀራት፣ በድህነት ቀንበር ትማቅቅ ዘንድ የተዋት እሱ ነው፡፡ በእውቀቱ ይህንን እግዜር እያነሳ የሚጥለው ህዝቦቿ ስለሚጠሩት እንጂ ለእርሱ ህላዌው እውነት ስለሆነ አይደለም፡፡ ይህን በማለቴ ዝናውን ከፍ እንደማደርግለት ባውቅም የእኛ ..ኒቼ.. ይሰኝ ዘንድ መታተሩን፣ እግዚአብሔርN መፍራት ገንዘቡ ያላደረገ እንዲህ ያለ የሥነ-መለኮት አጥኚ ሲያገኝም በለስ እንደቀናው አዳኝ እንዲሆን መግለጽ ይገባኛል፡፡ አገርን መውደድ የሰብዓዊ ህይወት አንዱና ጠንካራ መገለጫ እንደሆነ አውቃለሁ፡፡ ወንጌልን ያህል ትልቅ የምሥራች ለዓለም ሁሉ ያደርሱ ዘንድ መለኮታዊ ተልዕኮ የተሰጣቸው የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት እንኳ የተፈተኑበት ጽኑ ስሜት ይኸው እንደነበር አንብቤያለሁ፡፡ ሆኖም እግዚአብሔርን ከተፈጥሮ በላይ፣ ከህይወት በላይ አድርጐ የሚያሳይ መንፈሳዊነት ደካማ ነው፡፡ ተገቢ ባልሆነ መንገድ ስሜቱን ጥልቅ የሚያደርግ ሰውም በስውርም ሆነ በግልጽ ሰብአዊ ሁኔታን ብቻ አግዝፎ ያያልና መሳቱ ግድ ይላል፡፡ ዴቪድ ኩክ ..ክርስቲያን ኮንፍሮንትስ.. በሚለው መጽሐፉ ክርስትናን እየተፋለሙ ከነበሩትና ካሉት የአስተሳሰብ ሥርዓቶች መካከል ሂውማኒዝምን፣ ኮሚዩኒዝምን፣ ማቴሪያሊዝምንና ኤግዚስቴንሺያሊዝምን ያነሳ ሲሆን በተለይም ..ሂውማኒስት.. የሆኑ ሰዎችን ማራኪና አሳሳች ባህሪ አስመልክቶ ..ሰዎች ለሰብአዊው ዓለም እጅግ የሚቆረቆሩ፣ ነጋ ጠባም ይሄንኑ በማብሰልሰል የተጠመዱ መሆናቸው ቢማርኩንም ነገር ግን ፍልስፍናቸው ሰውን የሁሉም ነገር መለኪያ አድርጐ የሚወስድ፣ የአምላክና የግብረ-ገብ ፈጣሪው እንኳ ሰው ራሱ እንደሆነ ስለሚቆጥር ያሳስታል፡፡.. “Man is standard for everything, he makes God, Morality and everything else.” ይላሉ ይለናል፡፡ እኔም የሥነ-መለኮት አጥኚው ልብ ሊለው የሚገባው ይኸው ቢሆን ደስ ይለኛል፡፡
የእምነትን ሁሉን አቀፍ ገታ ለማጤን
ይህን ርዕሰ ጉዳይ በዚህ መልኩ ማቅረቤ ከላይ ከተነሱት ሀሳቦች ጋር ተያይዞ ስለ እምነት ያለንን ግንዛቤ ከቀበሌያዊ የሀሳብ ቁርቁስ አሻግረን ስለምንጩ ለማጤን ያግዘን እንደሆን በማለት ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ እንደ ምሳሌ የወሰድኩት በአዲስ አድማሷ የአማኝ አላማኝ ሙግት በአመዛኙ ሁለቱም ጎራዎች ማጣቀሻ የሚያደርጉትን ክርስቲያናዊ አስተሳሰብ ይሆናል፡፡
በአርል ኤ ኬን ተጽፎ በስሜነህ ተክሉ ..ክርስትና በዘመናት ሂደት.. በሚል ርዕስ በሸጋ አማርኛ ተተርጉሞ የቀረበልን የታሪክ መጽሐፍ የክርስትና እምነትን የትናንት ጉዞ ይተርካል፡፡ ..ከክርስትና እምነት አስተምህሮ ጋር ከልጅነቴ አንስቶ ብተዋወቅም ነፍስ አውቄ በዩኒቨርሲቲ ትምህርቴን እስከምከታተልበት ጊዜ ድረስ ግን ለነፍሴ ጥያቄ መልስ ሆኖ ታይቶኝ አያውቅም ነበር፡፡.. የሚለን የመጽሐፉ ተርጓሚ፤ ብርሃኑን ከጨለማው ለመለየት እስኪሳነው መቸገሩን፣ በገዛ አመጻው መጨነቁንና ከዚህ ያወጣኝ ብሎ የሚያስበውን እግዚአብሔር በአመክንዮ ቀመር ለመረዳት ያደረገው ጥረት ያለመሳካቱን፣ ሆኖም ያ ናፍቆቱ በፍቅር ምላሽ ተተክቶ እግዚአብሔርN መውደድ እንጂ ምንነቱን በዕውቀት ለመጨበጥ መሻት ብቻውን ፋይዳ እንደሌለው ተረድቶ ..እፎይ.. ማለቱን ይነግረናል፡፡ ..እፎይ.. ብሎ ግን ቁጭ አላለም፡፡ እግዚአብሔር ፍቅር ቢሆንም ግና ታሪካዊ መገለጫዎችም አሉትና መጻሕፍትን ሲያገላብጥ ያገኘውን አነቃቂ ታሪክ በመተርጐም እኛም እናነብ ዘንድ ምክንያት ሆነልን፡፡
መጽሐፉ ክርስትና ..ሀ.. ብሎ ከጀመረበት ዘመናት ብዙም ሳይርቅ ከ5-590 ያሉትን ወቅቶች ይሸፍናል፡፡ ጊዜያቱ ደግሞ ክርስትናን ከትውልዶች አፈ-ታሪክና ከግብፃውያኑ ፍልስፍና አንጥሮ ለማውጣት ከባድ ..ፍልሚያ.. የተካሄዱባቸው መሆናቸውን ይጠቁማል፡፡ ክርስትና ..የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ልጁን ላከ፡፡.. ገላትያ 4÷4 ከሚለው መነሻ ጋር በኑ የተቆራኘ በመሆኑ፣ እግዚአብሔር ልጁን ወደ ዓለም ሲያስገባው የትኛውም ከባቢያዊ ሁኔታ በእርሱ ሊፈጽመው ያለውን ሀሳብና ተልዕኮ ለማሳካት በሚያመች ዘመን ውስጥ እንደላከው ይተርካል፡፡ የሮም ዓለም አቀፋዊ ገዢነትም ሆነ የግሪክ ፍልስፍና በየራሳቸው ስለነበራቸው ጉልህ አስተዋጽኦ ይገልጻል፡፡ ለክርስቶስ መምጣት አይሁድ ብቻ ሳይሆኑ እነዚያ ጣኦትን፣ ምስጢራዊ እምነቶችንና ንጉሳዊ አምልኮን የሚፈጽሙ ህዝቦች አምላካዊ ፈቃዱን ለማሳካት ጠቅመዋል ይላል፡፡
ዓለሙን ሁሉ በአንድ የፖለቲካ ጥላ ስር የሰበሰቡት ሮማውያን፤ የግለሰብን ክቡርነትና ፍትህን የሚያጐላ ህግ መደንገጋቸውም ሆነ የገነቧቸው ልዩ ልዩ አገራትን የሚያገናኙት መንገዶች ባይሠሩ ኖሮ የወንጌል መልዕክተኞች በሜዲትራንያን ዓለም ነጻ መተላለፊያ አያገኙም ነበር፡፡ ይሁንና bQDm-ክርስትና ዘመን የነበረው የሮማ መንግሥት ሥልጣኑን ተጨባጭ ከማድረግ ያለፈ አጀንዳ አልነበረውም፡፡ ሮም የማታውቀው ዝግጅት ለክርስትና መምጣት ታላቅ ነገር ቢሆንም ቅሉ፣ የግሪክ አዕምሮ የፈጠረው ከባቢያዊ ሁኔታም እንደዚሁ ዓይነት መልክ ነበረው የሚለን መጽሐፍ፤ የሮም ከተማ ከክርስትና ፖለቲካዊ ሜዳ ጋር ቢገናኝም ለወንጌል መስፋፋት አጋዥ የሆነው የአስተሳሰብ ሜዳ ግን የአቴንስ ነበር ይለናል፡፡ ሆራስ በቅኔዎቹ እንደጻፈው ግሪኮቹ ሮማዎቹን በባህል አሸንፈዋቸዋል፡፡   
ሮማዎች ጥሩ ጥሩ መንገዶችን፣ ትላልቅ ድልድዮችን፣ የተንጣለሉ እልፍኞችን ቢሠሩም ግሪኮች ግን የተንጣለሉ የአዕምሮ እልፍኞችን ከማፍራታቸውም በላይ ቋንቋቸው የዓለሙ መግባቢያ ሆኖ ማገልገሉን መጽሐፉ ይተርክልናል፡፡ ይህም ብቻ ሳይሆን የግሪኩ ፍልስፍና ያረጁና ያፈጁትን እምነቶች በማፈራረስ ለክርስትና መንገድ ከመጥረጉ የተነሳ የፍልስፍናውን ውስጠ ሚስጢር ያወቀ ሰው ብዙ አማልክቶችን ማምለክ ሞኝነት ስለሚሆንበት ወደ ፍልስፍና ማዞር ግድ ይለው ነበር፡፡ ይሁንና ፍልስፍና መንፈሳዊ ረሃቡን ሊያረካለት አይችልምና ያለው ዕድል ሁለት ነው፣ አንድም ተጠራጣሪ (ስኬፕቲክ) መሆን አለያም የሮማ ምስጢራዊ እምነቶች መንፈሳዊና ስሜታዊ መስህብ ስለነበራቸው እነርሱን በመከተል መጽናናትን ለማግኘት መታገል ነበር፡፡
የታሪክ መጽሐፉ ትረካውን ሲቀጥል ክርስቶስ ባረገበት ጊዜ ፍልስፍና በፕሌቶ ከደረሰበት ጫፍ ወርዶ ግለሰብ ተኮር በሆነ እንደ ስቶይክ ወይም ኢፕክሪያኒዝም ባለ ደረጃ ዝቅ ብሎ ወርዶ ነበር ይለናል፡፡ ፍልስፍና ራሱም እግዚአብሔርN ፈልጐ እንደ አዕምሮ ውጤት የሚያስቀምጥ እንጂ የፍቅር አምላክ አድርጐ የማይገልጽ ስለነበር ክርስቶስ በመጣበት ጊዜ ሰዎች ለህይወት ያላቸው አመለካከት መንፈሳዊ ዝንባሌ እንዲኖራቸው አድርጐ ነበር በማለት የዘመኑን መልክ ፍንትው አድርጐ ያሳየናል፡፡ ከዚህ የተነሳ የጊዜው የመንፈሳዊ ህይወት ክፍተት ሊሞላ የሚችለው ክርስትና ሆኖ በመገኘቱ ግሪካውያኑ ክርስትናን ዓለም ይቀበለው ዘንድ ከፍተኛ ድርሻ ነበራቸው፡፡ ጠቅለል ተደርጐ ሲገለጽም የግሪክና የሮም የፍልስፍና ሥርዓቶች የብዙ አማልክትን አምልኮ በማፍረስና የሰው አዕምሮም በገዛ አቅሙ እግዚአብሔር ላይ ለመድረስ የማይችል መሆኑን ከማሳየት አንጻር ድርሻቸው የላቀ ነበር፡፡ ከዚህ በተለየ ሁኔታ ደግሞ የአይሁድ እምነት ከሌሎች አረማውያን እምነቶች በተለየ ጤነኛ በሆነ የአንድ አምላክ መንፈሳዊ አስተሳሰብ ላይ የቆየ ሲሆን አይሁድ ከባቢሎን ምርኮ በኋላ በፍም ወደ ጣኦት አምልኮ አልተመለሱም ነበር፡፡ በማለት የክርስትና አነሳስና የማሸነፍ ባህሪ ይተርክልናል፡፡
ድል አድራጊው በፈተና ውስጥ
ከላይ በተመለከትነው ሁኔታ የሰውን መንፈሳዊ ጥማት በክርስቶስ ኢየሱስ በመስቀል ላይ የተሠራ ሥራ እያረካና የሰውን አዕምሮ እየማረከ የመጣው ክርስትና፤ መልኩ ይጠይም ዘንድ አጀንዳው ይበረዝ ዘንድ የተጉ ሾልኮ ገቢዎች ተግዳሮት ቀላል አልነበረም፡፡ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ከተካተቱት ጥቂቶቹ ደግሞ Xnç-
ኖስቲዝም- ከፍልስፍናዊ አደጋዎች ሁሉ ክፍት የነበረው ኖስቲዝም በ150 ዓ.ም. ላይ ጫፍ ደርሶ ነበር የሚለን የታሪክ መጽሐፍ፤ ፍልስፍናው ሥሩን ከአዲስ ኪዳን ዘመንና ታሪክ ላይ ዘርግቶ የሀሳቡ ማጠንጠኛ ግን የሰው ልጅ ስለ ክፋት ለማወቅ ካለው ፍላጐት ጋር በኑ ስለመቆራኘቱ ይተርካል፡፡ ሆኖም የእግዚአብሔርንና የሰውን መንገድ በሰው ጥበብ ለመረዳት ያላቸው ጉጉት ተሳክቶ ቢሆን ኖሮ ክርስትናን በጥንታዊው ዓለም ያሉ ፍልስፍናዊ ሃይማኖት የሚያደርጉት እነርሱ ነበሩ ይላል፡፡ የኖስቲኮች ዋነኛ ትምህርት ክፉን ከቁስ፣ መልካምን ደግሞ ከመንፈስ ጋር ደምሮ የመመልከት ስለነበር በእነርሱ ዓይን ሥጋ ቁሳዊና በመጨረሻ የሚወገድ በመሆኑ በጥብቅ ምናኔ ሊጠበቅ ወይም ለልቅ ሥነ-ምግባር ሊሰጥ ይችላል፡፡ ለእነርሱ የሰው መዳን በእምነት ይጀምር እንጂ ክርስቶስ ለተመረጡት ሰዎች የሚሰጠውን ልዩ ዕውቀት፣ በነፍስ የመዳን ሂደት ውስጥ የሰጠውን ስፍራ የሚይዘው ይህኛው ሀሳባቸው ነው፡፡
ማንኪያኒዝም- ይህኛው ፍልስፍና ከኖስቲሲዝም ጋር ተመሳሳይነት ያለው ቢሆንም የራሱን የተለየ የፍልስፍና ሥርዓት በዘረጋ ማኒ ወይም ማኒኮል በተባለ የሚሶፖታሚያ ሰው በሦስተኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ የማኒ የተለየ መሻት ደግሞ የዞሮአስተርያንና ሌሎች የሩቅ ምስራቅ ሃይማኖታዊ አስተሳሰቦችን በመደበላለቅ የሁለትዮሽ ፍልስፍናን ያጎለበተ ነበር የሚለን የታሪክ መጽሐፍ፤ ማኒ በሁለት ተጻራሪና ዘላለማዊ ህጎች ያምናል፣ ሰው ሁለት ተጻራሪነት ካላቸው የጨለማና ብርሃን መንግሥታት የተገኘ በመሆኑ የሰው ነፍስ ከብርሃኑ፣ አካሉ ደግሞ ከጨለማው መንግሥት ጋር ተጣብቋል ብሎ ለሚያስበው ማኒ፤ የሚያራምደው ማንኪያኒዝም ምናኔን በኑ ስለሚያበረታታ የወሲብ ፍላጐትን እንደ ክፉ፣ አለማግባትንም የተሻለ አድርጐ ስለማመኑ ይነግረናል፡፡ (ሆኖም የእነዚህ ሁሉ ትምህርቶች ኑፋቄነት በአዲስ ኪዳን ውስጥ በዝርዝር ተጽፎ መገኘቱን ልብ ይሏል፡፡)      
ኒኦፕላቶኒዝም- የዚህ ፍልስፍና መጠንሰስ ሰበቡ የአሌክሳንድሪያ ተወላጅ በሆነው አምኒየስ ላከስ (174-242 ዓ.ም.) ሲሆን ፕላቲነስም ይህን አስተምህሮ በሦስተኛው ክፍለ ዘመን ማለቂያ ላይ በሮም ያስተምር እንደነበር የታሪክ መጽሐፉ ይጠቁመናል፡፡ ኋላም ላይ የኒኦፕላቶኒዝም ሥነ-ጽሑፋዊ መሠረት ከፕሎቲንየስ ስብስብ ሥራዎች በፎርፎሪ (232-305 ዓ.ም) ተዘጋጀ ይለናል፡፡ ኒኦፕላቶኒዝም ከሁለትዮሽ ይልቅ የአንድዮሽ አፈጣጠርን ያስተምራል፡፡ ፍም ፈጣሪን የሁሉም ነገር ምንጭና ከሙላቱ ተርፎ የተፈጠረ መሆኑን ይገልጻል፡፡ የዓለማቱ የመጨረሻ ግብም ወደ መጣበት የመለኮት ጉያ ተመልሶ መግባት ነው፡፡ ማለቱን የሚነግረን መጽሐፍ፤ ሆኖም ይሄ ፍልስፍና ከሚስቲካዊ (ተማልሏዊ) ዝንባሌዎች ጋር በኑ ስለመቆራኘቱ ይገልጽልናል፡፡ ጥሞና መውሰድ ሰው እግዚአብሔርን ለማወቅና ወደተገኘበት አንድዬ ተመልሶ ለመግባት አጋዥ ኃይል እንደሆነ ይቀበላል፡፡ በዚያ ጥሞናዊ አሰላስሎ ወቅትም ሰው እግዚአብሔርን እንዴት ሊያውቀው እንደሚችል ኢፒስቲሞሎጂካል ድንበሩ (ሥነ-ዕውቀታዊ ወሰኑ) ላይ ማትኮርን፣ የሰው መንፈሳዊ ህይወት በመለኮት አካል ውስጥ የሚዋጥበትን ሥነ-ፍጥረታዊ (ሜታፊዚካል) አግባብ ወደ ማሰብ የሚያዘነብሉ ስለመሆናቸውና ቡድሂስቶችም ይሄንኑ ፈለግ የሚከተሉ ናቸው ይላል፡፡ እነዚህ ክርስቶስን ማዕከል ያላደረጉ ፍልስፍናዊ ሚስቲሲዝሞች መኖር ግን ክርስትና ውስጥ እንዲህ ዓይነት ስሜት ጨርሶ የለም ማለት አይደለም፡፡ ስለዚህ ደግሞ የታሪክ መጽሐፉ መጽሐፍ ቅዱስ ከዚህ በተለየ መልኩ ሥነ-ምግባራዊና መንፈሳዊ የሆነ ሰው፣ ከክርስቶስ ከአዳኙ ጋር በመንፈስ አንድ ይሆን ዘንድ መንፈስ ቅዱስ በውስጡ ሲያድር ከእግዚአብሔር ጋር ጥልቅ ህብረት ይኖረዋል ይላል፡፡ ይህም ሚስቲሲዝም ሊሰኝ ስለመቻሉ ይገልጻል፡፡ እንግዲህ በዚህ የታሪክ መጽሐፍ ውስጥ የተጻፈው ብዙ ነው፡፡ ድል አድራጊውን የገጠሙት ተግዳሮቶች እነዚህ ብቻ አይደሉም፡፡
መጽሐፉ የጥንቱን ፍልስፍና፣ አፈ-ታሪክና የጣኦት አምልኮ ድል እየነሳ በነበረው ክርስትና ላይ የተቃጡት ጥቃቶችና ክህደቶች እነዚህ ብቻ እንዳልነበሩ ይገልጻል፡፡ ከፍልስፍናው ባሻገር ከፍተኛ ሥነ-መለኮታዊ ስህተት የታየባቸው ሞንታኒዝም፣ ሞናርኮያኒዝም፣ ዶናቲዝም የተሰኙ አስተምህሮዎች የእግዚአብሔር ልጅ ከላይ ይዞት የመጣውን ትምህርት ለማድበስበስ ልዩ ልዩ የኑፋቄ ዘርፎችን በእርሻው ላይ ስለመበተናቸው ያወሳል፡፡ ሆኖም ግን ክርስትና በየዘመናቱ የተነሱ ብርቱ ተሟጋቾችንና ለዚህ እምነት ጥብቅና የሚቆሙ ሰዎችን አላጣም ይላል፡፡ ከነዚህም ውስጥ ጀስቲን ማርታየር እና ኢራኒየስን ይጠቅሳል፡፡ ጀስቲን ማርታየር (100-165 ዓ.ም.) ከልጅነቱ አንስቶ እውነትን ፍለጋ ሲማስን የኖር ሰው ሲሆን የስቶይክ ፍልስፍናን፣ የፕሌቶን፣ የአርስቶትልንና የፓይታጐረስ ፍልስፍናዎችን የሚያውቅ ነበር፡፡ ሆኖም ይህ ሰው አንድ ሽማግሌ እውነተኛው ፍልስፍና መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንደሚገኝ ከነገረው በኋላ ህይወቱ የተለወጠና የክርስቲያኖችን ትምህርት ቤት እስከመክፈት የደረሰ ነው፡፡ ማርታየር በመንግሥት ባለሥልጣናት በክርስቲያኖች ላይ ይደርስ የነበረውን ኢ-ፍትሃዊነት ይሞግት የነበረ ሲሆን ኢራኒየስ ደግሞ የስህተት እንቅስቃሴዎችን በሥነ-ጽሑፍ ይተችና ይሞግት ነበር፡፡   እንደ ሌልስስ ያሉትም ተሟጋቾች፣ አረማውያን ፀሐፍትና ጐረቤቶቻቸው በክርስቲያኖች ላይ የሚለጥፉትን ስድብና የሚያሳዩትን ተቃራኒ ስሜት ለመከላከል ጽሑፍን መሣሪያው ያደረገ እንደነበር የሚተርክልን የታሪክ መጽሐፍ፤ ሌሎቹም በቀጥታውና በገንቢ መልኩ ከክርስትና ሃይማኖት ጋር ሲነጻሩ የአይሁድ እምነት፣ አረማዊ ሃይማኖቶችና የመንግሥት አምልኮ ኃጢያትና ቂላቂልነት መሆናቸውን ከመግለጽ ወደ ኋላ የማይሉ፣ በክርክር ስልታቸውም ባለሥልጣናቱን እንኳ ሳይቀር የሚማርኩና ክርስትናን በአመክንዮ የሚያቀርቡ እንደነበሩ ያወሳል፡፡ ከነዚህም መካከል የፍልስፍናውን ታሪክ የሚያውቁ ስለነበሩ ብሉይ ኪዳን ከትሮጃን ጦርነቶች በፊት የነበረና በግሪክ ፍልስፍና ውስጥ የሚገኙት ሃሳቦች ሁሉ ከአይሁድ ወይም ከክርስትና የተወሰዱ ናቸው በማለት ስለመሟገታቸው፣ የክርስቶስን ጥርት ያለ ህይወት፣ ተአምራትና ስለ እርሱ የተነገሩትን ብሉይ ኪዳናዊ ትንቢቶች መፈም በመጥቀስም ክርስትና የፍልስፍና ሁሉ የበላይ ነው የሚሉ ሙግቶችን አጉልተው ያቀርቡ እንደነበር ይተነትናል፡፡ ይህንን በሰፊው ለመረዳትና ለማወቅ የሚሻ ሰውም ..ክርስትና በዘመናት ሂደት.. የሚለውን መጽሐፍ ቃኘት ቢያደርግ ጥሩ ነው፡፡ እኔ ግን ክርስትናን ከአፈ-ታሪክ፣ ከፍልስፍናና ከአገራዊ አስተሳሰብ ነጥሎ ለማየት ይጠቅመን ዘንድ ይህችው በቅታኛለች፡፡

 

Read 3942 times Last modified on Saturday, 03 September 2011 12:08