የውይይት መድረኩን አስመልክቶ የመጠይቅ ጥናት አድርገናል ያሉት አቶ በፍቃዱ፤ የውይይት ቀን መቀየር እንደማስያፈልግ፣ ሆን ብለው ሰው ለማስደሰትና ለማስከፋት ወገንተኛ ሆነው የሚመጡትን ለመፃሕፍት ንባብ ውይይት ዓላማ ብቻ እንዲመጡ እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ በተሰጡ አስተያየቶች መሠረትም ካሁን በኋላ የሚደረጉ ውይይቶች መፃሕፍት ላይ ብቻ ይሆናሉ ተብሏል፡፡
የሚዩዚክ ሜይ ዴይ ኢትዮጵያ የመፃሕፍት ንባብና የውይይት ክለብ በዘንድሮው ዓመት አስር የልቦለድ መፃሕፍት (አንዱ ትርጉም)፣ ሰባት ኢ-ልቦለድ፣ ሦስት ጥናታዊ ሑፎች እና ሁለት የግጥም መፃሕፍት በ22 ሳምንታት ለውይይት የቀረቡ ሲሆን ከውይይት መሪዎችም አለማየሁ ገላጋይ፣ አስቻለው ከበደ እና ብርሃኑ ከአንድ ጊዜ በላይ ውይይት እንደመሩ ለማወቅ ተችሏል፡፡