በአዲስ አኩስቲክ ፕሮጀክት የተሰራው አዲሱ አልበም ትውስታ ለሁለት ዓመታት ዝግጅት ሲደረግበት ቆይቷል ያለው የዴይሊ ቴሌግራፍ ቅኝት ዋጋው 20.40 ዩሮ መሆኑን አመልክቷል፡፡ በ50ዎቹ እና 60ዎቹ የተሠሩ ታዋቂና ተወዳጅ ሙዚቃዎች እንደገና በዘመናዊና በባህላዊ የሙዚቃ መሣሪያዎችና ቅኝቶች የተዘጋጁበት አልበም በአስደናቂ የጥራት ደረጃ መሠራቱን ..ዘ ጋርዲያን.. ዘግቧል፡፡ የአዲስ አኩስቲክ ፕሮጀክትን ጊታሪስቱ እና የአኮርዲዮን መሣሪያ ተጫዋች ግሩም መዝሙር መስርቶታል፡፡ በትውስታ አልበም ላይ በሙዚቃ ቅንብር ግሩም መዝሙር ንቁ ተሳትፎ ያደረገ ሲሆን ሄኖክ ተመስገን በደብል ቤዝ ጊታር፣ ናትናኤል ተሰማ በድራም፣ አየለ ማሞ በማንዶሊን፣ መሰለ ለገሠ በከበሮ ተጫወችነት ከተሳተፉት መካከል ይገኙበታል፡፡