Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 03 September 2011 12:55

ሊል ዋይኔ እና ጄይ ዚ ተቃርነዋል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ኢትዮጵያዊቷ የሶል እና ጃዝ ሙዚቀኛ መክሊት ሃደሮ፤ ሰሞኑን በጉግል የሳምንቱ ምርጥ አርቲስት የተባለች ሲሆን 3ኛውን አዲስ የሙዚቃ አልበሟን እየሰራች መሆኑን ሳንፍራንሲስኮ ክሮኒል ዘገበ፡፡
ከሳምንት በፊት በአሜሪካዋ የናቫዳ ግዛት በሚገኘው ሴንተር ፎር አርትስ፣ የሙዚቃ ሥራዎቿን ያቀረበችው መክሊት፤ በድምፃዊነትና በዘፈን ግጥም ደራሲነቷ በካሊፎርንያ እየተወደሰች መሆኗንም ለማወቅ ተችሏል፡፡

በዬል ዩኒቨርስቲ በፖለቲካል ሳይንስ የተመረቀችው መክሊት፤ በ2008 ..ኢይት ሶንግስ.. ከዚያም በ2010  ..ኦን ኤ ዴይ ላይክ ዚስ.. የተባሉ ሁለት አልበሟቿን በፖርቶ ፍራንኪ ሬከርድስ አሳታሚነት ለገበያ አቅርባ በመላው አሜሪካ ከፍተኛ ተደማጭነት ማግኘቷን ዘገባው አትቷል፡፡ ..አርባ ምንጭ ኮሌክቲቭ.. በሚል በባህር ማዶ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን አርቲስቶችን በማስተባበር የሚሰራ ተቋም የመሠረተችው መክሊት ሀደሮ፤  ዘመናዊና ባህላዊ ሙዚቃን አጣምሮ በመሥራት በመላው ዓለም የኢትዮጵያ ዘፈኖች ገበያ የሚያገኙበትን ሁኔታ እያመቻቸች መሆኑ ታውቋል፡፡

 

Read 4932 times Last modified on Tuesday, 06 September 2011 14:17