Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 10 September 2011 12:03

የኔ ቢጤ

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

እኔ ላንቺ ግጥም
ቃላት ሣጠራቅም
አላዛር ከደዌው
ድኖ አገገመ
ስለዓለም ከንቱነት
ግጥም አሳተመ፡፡
ለውበትሽ ስንኝ
ፊደል አጥቼልሽ
በየመዘክሩ ስንከራተትልሽ
የእዮብ መከራ
ጭንቅ ዘመኑ አለፈ
..መታገስ ነው ደጉ!..
የሚል መጽሐፍ ፃፈ፡፡
እኔ ላንቺ ግጥም
ቃላት ሳጠራቅም
ውዲቷ አገራችን
እጅግ ተራቀቀች
በኤሌትሪክ ሽቦ
ፍቅር አስተላለፈች፡፡
ሰው ባገደመበት
ባለፈበት ስፍራ
ፍቅር አንፀባርቆ
መውደድ በአምፖል ሠራ፡፡
አንድ የተደበቀ
የተቀበረ ቃል
ድንገት ቢኖር ብዬ
ድንጋይ ስፈነቅል
የፍልስጤም ጉብል
ከእስራኤሏ ቆንጆ
ይቅር ተባብለው
ቀለሱልሽ ጐጆ፡፡
ያንቺነትሽን ምስጢር
ቅኔሽን አይቼ
እጽፍልሽ ነገር
እለው ቃል አጥቼ
ቃላት አልሳካ
ከቶ አልሰምር ብሎኝ
የነበረኝ እንኳ
ነጐደልሽ ጥሎኝ
እናም ስለማምላክ
እያልኩ እዞራለሁ
ካገር አገር እያልኩ
ቃል እለምናለሁ፡፡
ምልዕቲ ኪሮስ

Read 4365 times Last modified on Saturday, 10 September 2011 12:14