Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 10 September 2011 12:38

ተቃዋሚዎች ሰላለፈውና ሰለ አዲሱ ዓመት

Written by 
Rate this item
(0 votes)

በአጭር ጊዜ የሚታየኝ ተስፋ የለም
በ2003 አጣሁት የምለው ነገር የለም በግሌ፡፡ በአገሪቱ ግን የታጡ ብዙ ነገሮች አሉ፡፡ በደቡብ እና በደቡብ ምስራቅ የአገሪቱ ክፍሎች ድርቁ እና ረሀቡ እጅግ ተስፋፍቶ መሄዱ ያሳዝናል፡፡ መንግሥት ድርብ አሀዝ እድገት አምጥቻለሁ በሚልበት ሰዓት ይሄን ነገር መቋቋም አለመቻሉን ትልቅ ችግር እና እጦት አድርጌ አየዋለሁ፡፡ ሁለተኛው በተለይ የዋጋ ንረቱ የከተማውን ህዝብ ለረሀብ የዳረገው መሆኑ ነው፡፡ መንግስት ችግሩን መፍታት ተስኖት አንዴ የዋጋ ተመን ሌላ ጊዜ የተለያዩ ነገሮችን ሲሞክር በነጋዴውና በዜጋው ላይ ጥፋት ጉዳት አድርሷል፡፡ በአባላቶቻችን ላይ እስርና ወከባ መፈሙ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ምህዳር የባሰ መጥበቡን ያሳያል፡፡

እቺ አገር በግፍ አስተዳደር እና በከፍተኛ መከራ ያለች ስለሆነች በ2004 ዓ.ም. የፖለቲካ አስተዳደሩ እንዲሻሻልና የህግ የበላይነት እንዲሰፍን፤ ዜጐች ችግራቸውን ለመቅረፍ የሚችሉበት መንገድ እንዲፈጠር እመኛለሁ፡፡
የኢትዮጵያ የፖለቲካ እድገት ግራፉ ሲታይ ወደ ታች እየወረደ ነበር፡፡ አሁን ደግሞ በአንድ ፓርቲ በአንድ አምባገነን አገዛዝ የወደቀበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡ የአምባገነን አገዛዝ ደግሞ ህዝቦች ተሸማቀውና ተሸብረው የሚኖሩበት፤ ከእለት ወደ እለት እየተሻሻለ በመሄድ ፋንታ በጣም እየባሰበት የሚሄድ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በአገራችንም ዜጐች ያለምንም ወንጀልና ጥፋት እንዲሸማቀቁ እና ሀገሪቱ ወደ ድህነትና የፖሊስ ግዛት እየተቀየረች መሄዷ የሚያሳዝን ነው፡፡
በአጭር ጊዜ የሚታየኝ ተስፋ የለም፡፡ ዲሞክራሲ የህዝብ የትግል ውጤት ነው፡፡ ፓርቲዎች ቢኖሩም የማታ ማታ ወሳኙ ህዝብ ነው፡፡ ብቃቱ ከፍ ያለ፤ ሰብአዊ ክብሩንና ሁለንተናዊ መብቶቹን ለማረጋገጥ የሚጥር ህዝብ ነው የሚፈለገው፡፡ በኢትዮጵያ ዜሮ ላይ ከደረስን ከዚህ በኋላ ወደ ታች ይሄዳል የሚል አስተሳሰብ የለኝም፡፡ ስለዚህ ህዝቡ ሆን ብሎ አስቦ ይሄን ሁኔታ መለወጥና መቀየር እንዳለበት ይሰማኛል፡፡ ይሄ የአጭር ጊዜ እቅድ አይደለም፡፡ ያለበለዚያ በአምባገነን እና በአንድ አመራር ቀንበር ስር መኖር ምርጫው ይሆናል ማለት ነው፡፡ ህዝብ ደግሞ ሁልጊዜ ይሄንን አይመርጥም፡፡ በአዲስ አመት ለህዝብ ለሀገርም የምመኘው፣ ህዝቡ ካለበት የኑሮ አዘቅት ቅጠትና ከአምባገነን ፖለቲካዊ ሁኔታ የሚወጣበት፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ስራ አጥ ያለባት አገር እንደመሆኗ ይሄ ተለውጦ ወደ ብልግና የምናመራበት ሁኔታ እንዲፈጠር ነው፡፡
አቶ ገብሩ አስራት
(አረና ትግራይ ሊቀመንበር)

 

Read 4303 times Last modified on Friday, 16 September 2011 06:14