Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 10 September 2011 12:52

..የዲሞክራሲ ረሃብና እጦት እየተባባሰ ነው..

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

በ2003 ዓ.ም አጣሁት የምለው ነገር በግሌ የለም፡፡ በአገር ደረጃ ብዙ ነገሮች የታጡበት አመት ነው፤ የ2003 ብቻ ሳይሆኑ ሲንከባለሉ የመጡ ናቸው፡፡ በኑሮ ውድነቱ ምክንያት ብዙ ሰው የመብላት፣ የመኖር፣ የመልበስ አቅሙን አጥቷል፡፡ በኑሮ ውድነት ምክንያት የተፈጠረው ችግር የማህበራዊ ኢኮኖሚ እጦት የፈጠረው ነው ብዬ ነው የማስበው፡፡ ይሄ መቼም በመንግስት በኩልም ጐልቶ ታይቷል፡፡ መንግሥትም የተከተለው ፖሊሲ ነገሩን አባብሶት ነበር፡፡ የዋጋ ንረቱን ለመከላከል የተወሰደው እርምጃ ዋጋ እንዲንር እቃዎች እንዲጠፉ አድርጓል፡፡ የዲሞክራሲ እጦቱ የቀጠለ ቢሆንም ይሄ ሁኔታ ከኢትዮጵያ አልፎ የአፍሪካም እጦት እየሆነ ነው፡፡ በእርግጥ አምባገነኖች አርባና ሰላሳ አመት ገዝተው የሆኑትን እያየነው ነው፡፡

አገራችንን እንደ ህዝብ፣ እንደ መንግስት እና እንደ ተቃዋሚ ፓርቲ በሰለጠነ መልኩ በመቻቻል ልናራምዳት ስንችል፣ በሁሉም በኩል ድክመት አያለሁ፡፡ አንድ አላማ ይዘን አገሪቱን ከድህነትና ከኢኮኖሚ ችግር ለማስወጣት እየቻልን፣ ሁላችንም ባለው ዘመናዊ የአሰራር ዘዴ ሳናሻሽላት ቀርተናል፡፡ ያንን ክፍተት በሰፊው xyêlhù፡፡b2004 ዓ.ም ኢትዮጵያ ከፖለቲካ፣ ከኢኮኖሚና ከማህበራዊ ችግር እንድትወጣ እመኛለሁ፡፡ ከፍተኛ ባህልና ታሪክ ያለን ነን፤ አሁን ካለንበት አረንቋ ለመውጣት ህዝብም፣ መንግሥትም ተቋዋሚ ፓርቲም ብሔራዊ መግባባት ፈጥሮ፣ የህዝብ ሰቆቃና የድህነት አረንቋን ማስወገድ አለበት፡፡ ዲሞክራሲያዊ እጦትና ረሀብ እየተባባሰ ነው፡፡ ትንሽ የዲሞክራሲ ጭላንጭል ያየሁት በ1997 ዓ.ም ነበር፡፡ አሁን ከስሙ በስተቀር ያለ አይመስለኝም፡፡ ከ97 በኋላ ሁላችንም ፍራቻ ውስጥ የገባንበት ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡ አንድ አምባገነን ፓርቲ በጉልህ እየወጣ ነው፡፡ ከመንግስት ባሻገር የተቃዋሚ ፓርቲም ድክመት ጐልቶ የወጣበትም ዓመት ነው - 2003 ዓ.ም.፡፡ አብዛኛዎቹ ተባብሮ ከመሥራት ይልቅ ወደ መናቆርና ወደ መደባደብ የደረሱበት ነው፡፡ ስለዚህ ተቃዋሚዎች ጋርም ቁልቁል የመሄድ ነገር አያለሁ፡፡ ሚዲያውም ካለው የህግ ከለላ ማጣት አንፃር እየደከመ መጥቷል፡፡ ከ97 ጋር ሳወዳድረው የህዝቡም ተሳትፎ የቀዘቀዘ ነው፡፡ ሁሉም የሚመለከታቸው አካላት፣ (ሁላችንም የአንድ አገር ልጆች ነን) በብሔራዊ መግባባት በመተባበር ኢትዮጵያን እንደምናሳድግ ተስፋ አለን፤ ችሎታውም አለኝ፡፡ ሰው የሚኖረው በተስፋና በእምነት ስለሆነ፣ ሁላችንም ከያለንበት ያለብንን ችግር ቀርፈን፣ መንግስትም ወደ ተጨባጭ ሁኔታ ቢመጣ ጊዜው አልመሸም፡፡ የፖለቲካውን እጣ ፈንታ ለመተንበይ አስቸጋሪ ነው፤ ተስፋ ቢኖረኝም ችግሩ አሳሳቢ ነው፡፡
ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ካለበት ማህበራዊና ፖለቲካዊ ችግር እንዲወጣ፤ ባህላዊ አብዮት አካሂዶ ከአድርባይነት ከውሸት አለም ውስጥ በመውጣት አገራችንን በተጨባጭ ሁኔታ ለማሳደግ በጋራ እንድንሰራ እመኛለሁ፡፡
ኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራው
(የአንድነት ለዲሞክራሲ ፓርቲ የውጭ ግንኙነት ኃላፊ እና ም/ሊቀመንበር)

 

Read 5384 times Last modified on Saturday, 10 September 2011 13:03