Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 10 September 2011 12:58

..ተቃዋሚ ፓርቲዎች እንዲሳተፉ ጥሪ እናስተላልፋለን..

Written by 
Rate this item
(0 votes)

2003 ዓ.ምን ኢህአዴግ ሲገመግመው የእድገትና የትራንስፎርሜሽን እቅዱን ለማሳካት ወደ ተግባር የተገባበት ሁኔታ የታየበት ነው፡፡ እቅዱ እንዲታወቅና ውይይት እንዲደረግበት በውጪ ያሉ ኢትዮጵያውያን ዲያስፖራዎችም ለዚህ እቅድ መሳካት የበኩላቸውን ጥረት እንዲያደርጉ ሠፊ ሥራ የተሠራበት፣ ታላቁ የህዳሴ ግድብ እንዲጀመር የተደረገበት ዓመት ነው፡፡ ድርጅታችን ኢህአዴግ የግድቡን ግንባታ ይፋ ካደረገ በኋላ ወጣት ሽማግሌ ሳይል የተነቃቃበት ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡ ሰፊ የሆነ ግለት፣ የጋራ መግባባት የተፈጠረበት መሆኑን ህዝቡ አሳይቷል፡፡ በራሳችን አቅም ታላቁ ህዳሴ ግድብን ለመስራት ማሰባችን ራሱ ትልቅ መነሳሳት የተፈጠረበት ዓመት መሆኑን ያመለክታል፡፡

ኢህአዴግ በ2002 ዓ.ም ምርጫ አሸንፎ መንግሥት ከመመስረቱ በፊት ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች መቀመጫ ቢኖራቸውም ባይኖራቸውም፣ በአጠቃላይ አገራዊ ጉዳይ ላይ በጋራ እናወያያቸዋለን ብለን ባስቀመጥናቸው ጉዳይ ላይ ግብዓት ለመሰብሰብ የሄደበት አግባብ አለ፡፡ ይሄም ኢህአዴግ ምን ያህል እንደሰፋና አሳታፊ እንደሆነ የሚያመለክት ነው፡፡
በ2003 ዓ.ም የሥራ እንቅስቃሴ አንዳንድ ያጋጠሙ እክሎች ነበሩ፡፡ ለምሳሌ ከንግዱ ጋር በተያያዘ የግብር ሥርዓትና የንግድ ሥርዓት ችግርን መሥመር ለማስያዝ ሲሞክር  ችግሮች ተፈጥረዋል፡፡ ሊቀረፉ ቢችሉም፡፡ በአጠቃላይ ግን በዓመቱ አልፎናል ብለን የምንለው ነገር የለም፡፡ በኑሮ ውድነትም ውስጥ ቢሆን ምርታማነትን እያሳደግን ነው፡፡ የገበያ ማረጋጋት ሥራ ሠርተናል፡፡
በ2003 ዓ.ም. ያስደነቀኝ መጋቢት 24 ጠ/ሚኒስትሩ ስለ ታላቁ ግድብ ከገለ በኋላ ሕፃናት የከረሜላቸውን ለግድቡ ማዋጣታቸውና፣ በትላልቅና በትናንሽ ከተሞች ከዳር እስከ ዳር የታየው የህዝብ መነሳሳት ነው፡፡ ክስተቱ ህዝቡ ምን ያህል ተቆጭቶ እንደነበር የሚያሳይ ሲሆን በዚህም በኢትዮጵያ ሕዝብ ኩራት ተሰምቶኛል፡፡ 2004 ዓ.ም በኢትዮጵያ ሰላምና ተቻችሎ መኖርን፤ ከጥላቻ ተላቀን ሁላችን ተሰባስበን ይህችን አገር ወደ ተሻለች ደረጃ ለማድረስ የተፈጠረውን ሰፊ መነሳሳት እና መግባባት መቀጠል እንዲችል የምናደርግበት ነው፡፡ በ2002 ዓ.ም ሕዝቡ ያለ ምንም ጫና ምርጫ አካሂዷል፤ ይሄ የዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ማደጉን ያሳያል፡፡ ከአምናው ዘንድሮ፣ ከዘንድሮ የሚቀጥለው ዓመት በሚል መንግሥትም ለመጪው ዓመት የበለጠ እየሰራ ነው፡፡ የተጀመረው በአንድ ጊዜ የሚያልቅ አይደለም፡፡ ጥሩ ደረጃ ደርሰዋል የተባሉት ሀገሮች እንኳን ብዙ ነገሮች ይጐድሏቸዋል፡፡ በ2004 ዓ.ም ተቃዋሚ ፓርቲዎች ተሣትፎ እንዲያደርጉ ጥሪ እናስተላልፋለን፡፡ በኢህአዴግ እምነት የፖለቲካው እጣ ፋንታ ከጥላቻና ከአመ የሚላቀቅበትና ህብረተሰቡ ያሻውን አማራጭ የሚወስንበት ይሆናል፡፡
አቶ ተመስገን ጥላሁን
(የኢህአዴግ የውጭ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ)

 

Read 4904 times Last modified on Saturday, 10 September 2011 13:02