Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Print this page
Saturday, 01 December 2012 14:21

ሻኪራ በቀድሞ ፍቅረኛዋና ማናጀሯ ተከሰሰች

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

ታዋቂዋ የላቲን አሜሪካ ድምፃዊት ሻኪራ፤ የቀድሞ ፍቅረኛዋና ማናጀሯ አንቶኒዮ ዴ ላ ሩዋ የ100 ሚሊዮን ዶላር ክስ እንደመሠረተባት ሲቢኤስ ኒውስ ዘገበ፡፡ ድምፃዊቷ በ2008 እ.ኤ.አ ላይ ላይቭ ኔሽን ከተባለ የኮንሰርት ፕሮሞተር ጋር ለ10 ዓመታት የሚቆይ የ300 ሚሊዮን ዶላር ውል እንድትፈራረም ዋናውን ሚና የተጫወትኩት እኔ ብሆንም የሚገባኝ ክፍያ አልተሰጠኝም ብሏል-ከሳሿ፡፡
አንቶኒዮ ዴ ላሩዋ በኒውዮርክ ለሚገኝ ፍርድ ቤት ባስገባው የክስ ማመልከቻ፤ ሻኪራ ከምታገኘው ትርፍ ልትከፍለኝ ቃል የገባችውን ገንዘብ ከልክላኛለች ሲል ከሷታል፡፡ በሙሉ ስሟ ሻኪራ ኢዛቤል ሜባራክ ሪፖል ተብላ የምትጠራው ኮሎምቢያዊቷ፤ የቀድሞው የአርጀንቲና ፕሬዝዳንት ልጅ ከሆነው ከዚህ ማናጀሯ ጋር ለ10 ዓመታት የዘለቀ የፍቅር ግንኙነት እንደነበራት ይታወቃል፡፡

እንደማናጀሩ ክስ የፍቅር ግንኙነታቸው ከተቋረጠ በኋላ፤ ከእሷ ሊያገኝ ይገባው የነበረውን ክፍያ ከልክላዋለች፡፡ የ35 ዓመቷ ሻኪራ ከሁለት ዓመት በፊት ከላ ሩዋ ጋር የነበራትን የፍቅር ግንኙነት ያቋረጠች ሲሆን ከባርሴሎናው እግር ኳስ ተጫዋች ጄራርድ ፒኬ ጋር የጦፈ ፍቅር እንደያዛት ይታወቃል፡፡ ሻኪራ ከዚሁ ፍቅረኛዋ ያረገዘችውን የመጀመርያ ልጇን ለመውለድ የመጨረሻ ወራቶቿ ላይ ትገኛለች፡፡ ስምንት ጊዜ የላቲን አሜሪካ ግራሚ አዋርድን እንዲሁም ለ28 ጊዜያት የቢልቦርድ ላቲን አዋርድን ያሸነፈችው አርቲስቷ፤ በመላው አለም 50 ሚሊዮን ያህል የአልበሞቿን ቅጂዎች በመሸጥ በላቲን ሙዚቃ ታሪክ የላቀ ስኬት አስመዝግባለች፡፡ ስምንተኛውን አልበሟን በመስራት ላይ የምትገኘው ሻኪራ፤ ከላቲን ሙዚቀኛነቷ ባሻገር በፖፕ ሙዚቃዎቿም ተወዳጅ ናት፡፡ ሻኪራ በዘፈን ደራሲነት እና በፕሮዱዩሰርነት ከ200 ሚሊዮን ዶላር በላይ በማካበት ተሳክቶላታል፡፡

 

Read 5766 times Last modified on Saturday, 01 December 2012 14:27

Latest from