በብስራት ገመቹ ተፅፎ የተዘጋጀውና በራሷ ፕሮዲዩስ የተደረገው “መልሕቅ” ፊልም ሰኞ እንደሚመረቅ አዘጋጆቹ አስታወቁ፡፡ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ትያትር የሚመረቀው ፊልም ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ለሕዝብ መቅረብ ጀምሯል፡፡
በፊልሙ በ “ሰው ለሰው” የቴሌቪዥን ድራማ እስከቅርብ ጊዜ ድረስ ትተውን የነበረችው ብስራት በ “መልሕቅ” እየተወነች ሲሆን በዚሁ ድራማ የሚተውነው ዝናህብዙ ፀጋዬ፣ እንዲሁም ዳንኤል ገበየሁ፣ ኤርምያስ ሀብታሙ፣ አለባቸው መኮንን፣ መንገሻ ተሰማ፣ መክሊት ገብረየስ፣ እንድርያስ አስናቀው እና ሌሎችም ተውነዋል፡፡ የ110 ደቂቃ ፊልሙን ሠርቶ ለማጠናቀቅ 11 ወራት ፈጅቷል፡፡