Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 01 December 2012 14:42

ጋዜጠኛ ብርሐኑ ሰሙ ተሸለመ

Written by 
Rate this item
(2 votes)

በአዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ በተለይ የአዲስ አበባን ታሪካዊ ስፍራዎች አመሠራረት በመዘገብ የሚታወቀው ጋዜጠኛ ብርሃኑ ሰሙ፤ በከተማው አስተዳደር ተሸለመ፡፡ አዲስ አበባ የተመሠረተችበት 125ኛ ዓመት ክብረበአል ሲጠቃለል ጋዜጠኛውን ለሽልማት ያበቁት ስለ ከተማዋ ታሪካዊ ዳራዎች ያደረጋቸው ጥናቶችና ያጠናቀራቸው ጽሑፎች እንዲሁም ያሰባሰባቸው የፎቶግራፍ መረጃዎች ናቸው፡፡ የከተማዋን ልደት አስመልክቶ ከሕዳር 11 እስከ ሕዳር 17 ቀን 2005 ዓ.ም በኤግዚቢሽን ማእከል ተዘጋጅቶ በነበረው አውደርእይ በግል ለመካፈል ጥያቄ አቅርቦ ተቀባይነት ያገኘው ብርሃኑ ሰው ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ባደረገለት ድጋፍ በአውደርእዩ ላይ በነፃ ማሳያ ቦታ ተሰጥቶት ተሳትፏል፡፡

የአዲስ አበባ 125ኛ ዓመት ሲጠናቀቅ በተደረገ የሽልማት ስነሥርአት ጋዜጠኛ ብርሃኑ ሰሙ፤ “ልዩ ተሸላሚ” በመባል ከተሸለሙ ስድስት ተቋማትና ግለሰቦች አንዱ በመሆን ግዙፍ የግርግዳ ሰዓት እና የተሳትፎ የምስክር ወረቀት ተሸልሟል፡፡ ከልዩ ተሸላሚዎቹ መካከል የሩሲያ ፌዴሬሽን መንግስትና የቦትስዋና ሪፐብሊክ መንግስት ይገኙባቸዋል፡፡ ብርሃኑ “ከእንጦጦ ሐሙስ ገበያ እስከ መርካቶ” የሚል የከተማዋን የንግድ እና ሌሎች ተቋማት ታሪክ የያዘ መጽሐፍ በ2003 ዓ.ም ለንባብ ማብቃቱ ይታወቃል፡፡

Read 4389 times Last modified on Tuesday, 04 December 2012 07:06