የእኔ ሥራ ሁልጊዜ መሥራት ነው፡፡ ለእኔ የሚገባኝ በመሥራቴ ትምህርት እየተማርኩ እንዳለሁ ነው፡፡ ለሙያው ያደረኩትን አስተዋጽኦ በሚመለከት የሚያውቀው ተመልካቹ ነው፡፡ የሚደርሰኝ አስተያየት ደግሞ አበረታች ነው፡፡ ለእኔ ይሄንን ማግኘቴ በጣም ደስ የሚያሰኘኝ እና ወደ ተሻለ ነገር የሚገፋፋኝ ነው፡፡ እኔ እንደ ባለሞያ ዕድገቱን ሳይ ለምሳሌ ሔሮሺማ ደረጃውን የጠበቀ ሥራ ነው፣ ተመልካችም ጥሩ አስተያየት ይሰጠናል፡፡ ስለዚህ ሙያው ማደጉን ያሳያል፡፡ በዓለም ላይ የተከሰቱት የእርስ በርስ ጦርነት፣ ድርቅ እና የተፈጥሮ አደጋዎች አሰቃቂ ክስተቶች ናቸው፡፡ በ2004 ዓ.ም ኢትዮጵያ ሁሉም ሰው የሚደሰትባት፣ የሚጠግብባት ፍቅር እና ሠላም የሠፈነባት፤ አንድም ሰው ዳቦ አጥቶ የማይራብባት ኢትዮጵያን እመኛለሁ፡፡
መሠረት መብራቴ ተዋናይ
Published in
የሰሞኑ አጀንዳ