Print this page
Saturday, 08 December 2012 13:33

የለውጥ ነገር

Written by  ነ.መ
Rate this item
(4 votes)

ምኔን ነው ምትወጂው፣ ምንሺን ነው ‘ምወደው
ተብሎ ቢጠየቅ፤
መጀመሪያም የለው፣ መደምደሚያም የለው!!
ወፍራሙ እየከሳ፣ ስሱ እየገነነ
አዲስ ያልነው ሁሉ፣ አሮጌ እየሆነ፤
አረጀ ያልነው ጉድ፣ እያደር ዘበነ!!
ፈርዶብን!!
23/2003
(ለባለበት - ሃይ ትውልድ)

ፍቅርና ወሊድ
ፍቅርና ወሲብ፣ በድመቶች ዓለም
አለው አንዳች ነገር፣ እጅግ የሚያስደምም፡፡
ነብር - መሳይ ድመት፤
ፍቅር ስትሰራ፣ ጣር ምጧን ጨርሳ
የወሊዷ ለታ፣ ስታምጥ ብትውልም፤
ድምጿን አታሰማም!!
የእኛ ግን ሌላ ነው ፡-
ለፍቅርም ማማጥ ነው
ለአንድነት ማማጥ ነው
ለወሊድ ማማጥ ነው
ለሞትም ማማጥ ነው
ጣር ነው ጅምራችን፣ ጣር ነው መጨረሻው
ለምንድን ነው አልኩኝ፣ ከድመት ያነስነው?!
2002 ዓ.ም
(ለውቡ ምጣችን)

Read 5812 times