በ2012 የሆሊውድ ፊልሞች በሰሜን አሜሪካ ያስገቡት የገቢ መጠን 9.75 ቢሊዮን ዶላር መድረሱን የገለፀው ዘገባው፤ በቀሪዎቹ ሳምንታት ይሄው የገቢ ሁኔታ ከቀጠለ በ2009 እ.ኤ.አ በ10.6 ቢሊዮን ዶላር የተመዘገበውን ዓመታዊ የገቢ ሪከርድ ሊሰብር እንደሚችል ይገመታል ብሏል
በዘንድሮ የሆሊውድ ፊልሞች ገቢ በበዓላት ሰሞን ከፍተኛ መሟሟቅ እያሳየ ሲሆን እስከ 11 ቢሊዮን ዶላር ገቢ በማስመዝገብ አዲስ ክብረወሰን ሊመዘገብበት ይችላል ተባለ፡፡ ሰሞኑን ከተከበረው የ”ታንክስጊቪንግ” በዓል ጋር በተገናኘ የቦክስ ኦፊስ የአሜሪካ በታሪክ ከፍተኛው ሪከርድ የሆነ የ290 ሚሊዮን ዶላር ገቢ መመዝገቡን “ዘ ሆሊውድ ሪፖርተር” አስታውቋል፡፡