Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Print this page
Saturday, 17 September 2011 09:50

..በሃበሻ ጀብዱ.. ላይ ውይይት

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

የሚዩዚክ ሜይ ዴይ ኢትዮጵያ የመፃህፍት ንባብና የውይይት ክለብ አዶልፍ ፓርለሳክ በፃፈውና ተጫነ ጀብሬ መኮንን በተረጎመው ..የሀበሻ ጀብዱ.. መሐፍ ላይ ሊወያይ ነው፡፡ ነገ ከቀኑ 8 ሰዓት በአምስት ኪሎው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተመዘክር አዳራሽ ውይይት መነሻ ሀሳብ በማቅረብ የሚያወያዩት ደራሲ አበረ አዳሙ ናቸው፡፡   
የከያኒዎች የቲቢ ውይይት

የኪነጥበባት ባለሙያዎች እና ጋዜጠኞች ዛሬ የቲቢ በሽታን አስመልክቶ የግማሽ ቀን የፓናል ውይይም በግሎባል ሆቴል ከጧቱ 2፡30 ጀምሮ ያካሂዳሉ፡፡ ..በቀላል ጥንቃቄ ሕይወትን ማዳን.. በሚል መርህ የሚካሄደውን ውይይት ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር፣ እና ቲቢ ኬር ኢትዮጵያ ከቲቢ ሚዲያ ፎረም ጋር በመተባበር ያዘጋጁት ሲሆን የቲቢ አምባሳደር አርቲስት ፍቃዱ ተክለማርያምና የሚነስቴሩ የሕዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ አህመድ ኢማኖ ይመሩታል፡፡ አምባሳደር ፍቃዱ ትያትርና ሲኒማ ቤቶች እንዲሁም ዲኤስ ቲቢ ቤቶች ቲቢን አስመልክቶ ቅስቀሳ እንዲደረግባቸው ..መዝናናትን ሲያስቡ ለደንበኞች ጤናም ይጨነቁ.. በሚል ተጨማሪ መርህ እንደሚያሳስብ፣ አርቲስቶች ሙያዊ አስተዋኦ እንዲያደርጉ እንደሚጋብዝና ሕብረተሰቡ መስኮቶች በመክፈት የቲቢን ስርጭት ለመግታት የበኩሉን ሚና እንዲወጣ ይጠይቃል፡፡

Read 4130 times

Latest from