Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Print this page
Saturday, 17 September 2011 09:53

ጄሎና ዲያዝ ለፊልማቸው ..ትራንስ ኢትዮጵያ..ን ፈጠሩ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ጄኒፈር ሎፔዝና ካሜሮን ዲያዝ በመሪ ተዋናይነት በሚሳተፉበት ..ዋት ቱ ኤክስፔክት ዌን ዩአር ኖት ኤክስፔክቲንግ.. የተባለ ፊልም ቀረፃ ላይ ..ትራንስ ኢትዮጵያ.. የተባለ አየር መንገድ በልቦለድ መፈጠሩን ተገለፀ፡፡ በፊልሙ አንድ ትእይንት ቀረፃ ላይ በሂውተን ካውንቲ ኤርፖርት ከሚገኙ አውሮፕላኖች አንዱ ላይ ..ትራንስ ኢትዮጵያ.. በሚል መታተሙን የሚገልፀው ዘገባው፤ በአየር ማረፊያው ደጃፍ ላይ የኢትዮጵያ ባንዲራ ተሰቅሎ ሲውለበለብ መታየቱን አመልክቷል፡፡

ከፍተኛ ሽያጭ ባስመዘገበ መሃፍ ላይ ተመስርቶ በሚሰራውና ኢትዮጵያዊ ህፃንን በጉዲፈቻ ለማሳደግ ከሚጥሩ አሜሪካዊያን ጥንዶች ጋር በተገናኘ ታሪክ የሚሰራው ፊልሙ፤ ቀረፃውን ከወር በፊት ጀምሯል፡፡ ፎኒክስ ፒክቸርስ በሚያሰራውና 2012 ከገባ በአራተኛው ወር ላይ ለእይታ በሚበቃው በዚሁ ፊልም ላይ ከጄሎና ዲያዝ በተጨማሪ ክሪስ ሮክና ብላክ አይድ ፒስ ይተውናሉ፡፡

 

Read 5725 times Last modified on Saturday, 17 September 2011 09:55

Latest from