ልብ-ወለድ

Saturday, 29 July 2017 12:07

አዚማሙ

Written by
Rate this item
(11 votes)
«በአንድ ምሽት የተገመደዉ የወዳጅነት ትስስሮሽ፣ ለበርካታ ዓመታት ሊዘልቅ በቅቷል።»በወረቀት ላይ ፃፈዉ፤ በሚነበብ መልኩ አሰፈረዉ። ግን የ’ርሱንና የጨረቃን ወዳጅነት ቢተርክ፣ማን ያምነዋል፤ማንስ «ዕዉነት ነዉ!» ብሎ ይቀበለዋል? ግራ ገባዉ። ትዝታዉን ለማስፈር ወረቀትና ብዕር አሰናኘ፤ አሰናኝቶም ታሪኩን ይፅፍ ቀጠለ፤ የተገናኙበትን ቀን ተረከ...«ከበርካታ ዓመታት በፊት፣እኔ…
Monday, 17 July 2017 13:07

የይሁዳ ደብተር

Written by
Rate this item
(16 votes)
አስክሬኑን ሳየው አሳዘነኝ፡፡ ኩርምት ብሎ ወድቋል። ከአይኑ ሥር ቁልቁል ወደ ጉንጮቹ የወረደው እንባ መስመር ሰርቷል፡፡ ዓይኖቹ ተከድነው፣ የታች ከንፈሩ ቆሥሏል፡፡ ምናልባት በሰራው ሥራ ቁጭት፣ ነክሶት ይሆናል፡፡ እግሮቹ አካባቢ በተለይ ተረከዙ፣ ተሰነጣጥቋል። ብርድና ቁር የተፈራረቀበት ዓይነት፡፡ መንገደኛው ሁሉ አገላብጦ አይቶ ትቶታል።…
Rate this item
(14 votes)
 ...አሁንም ነጻ ነው! አላሰሩትም! ወይ ጉዱ! ካሁን በኋላስ እስከ መቼ በነጻነት መከራውን እያየ ይኖር ይሆን!ሶፒ፤ በማዲሰን አደባባይ ተጎልቶ ያለ እረፍት ይቁነጠነጣል፡፡ ክረምት መግባቱን የሚጠቁሙ ምልክቶች ይስተዋላሉ፡፡ አዕዋፍ ወደ ደቡብ አቅጣጫ እየከነፉ ነው፡፡ የቤት እመቤቶች ካፖርትና ወፍራም ሹራብ እንዲገዙላቸው ለባሎቻቸው ትሁት…
Sunday, 02 July 2017 00:00

ሽማግሌው

Written by
Rate this item
(15 votes)
(ደራሲ አዳም ረታን ጨምሮ ሌሎች ዕውቅ ጸሐፍያን ከተሳተፉበትና ዛሬ ለንባብ ከበቃው “አማሌሌ እና ሌሎች” ከተሰኘ መድበል ውስጥ ለዛሬ የሌሊሳ ግርማን እንዲህ አቅርበናል)ሀገሪቱ አድጋለች የሚባለው ለካ እውነትም በቁመት ነው!. . . ሠላሳኛው ፎቅ ላይ ነው ሼባው የሚኖረው፡፡ ዛሬ መብራት በመጥፋቱ ምክኒያት…
Sunday, 25 June 2017 00:00

ዘቢባ አሊባባ

Written by
Rate this item
(6 votes)
ከእልህ አስጨራሽ ቢሮክራሲያዊ ውጣ ውረድ በኋላ የይዞታ ማረጋገጫ ሰነዴን የምቀበልበት የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ ደርሻለሁ። ጉዳዬ ወደተመራበት ቢሮ በተስፋ ጢም ብዬ ገባሁ፡፡ፍፁም ያልጠበኩት ምላሽ ነበር የጠበቀኝ----“--አንዳንድ መረጃዎችህ የህጋዊነት ክፍተት ይታይባቸዋል---ማጣራት የሚገባን ጉዳይ ስላለ--” “መቼ ነው ተጠርቶ ጉዳዬ እልባት የሚያገኘው» ግልፍ ብዬ…
Monday, 19 June 2017 09:51

ዳልች

Written by
Rate this item
(7 votes)
 ዳልች፤ እንጢጥ ያለ ጥጋበኛ ነው፡፡ ....የሰው ማሳ ገብቶ ሰብል ሲያወድም፤ ሴት ወይም ጉብል ሊከለክለው ከመጣ፣ ቀጥ ያሉ ጆሮዎቹን ወደ ጋማው ልጎ፣ ወደ አባራሪው ይንደረደራል፡፡ . . . እንግዲህ እየጮሁ መሮጥ የአባራሪው ፋንታ ይሆናል፡፡ ደሞ ክፋቱ መንጋውን የመምራት ሀይሉ ነው፡፡ ከተከተሉት…