ልብ-ወለድ

Saturday, 15 June 2013 11:12

ቀጠሮ

Written by
Rate this item
(1 Vote)
እንደ ማሰላሰያ አስታውሳለሁ፤ ድሮም እኔ ነበርኩ፡፡አሁንም እኔ ነኝ፡፡ እንደሌሎቹ “እኔ” ብለው ራሳቸውን የሚጠሩ ድሮም አልነበርኩም፡፡ አሁንም አይደለሁ፤ ስጨርስም አልሆንም፡፡ “እና ታዲያ ምንድነው ችግሩ?” ብዬ እጠይቃለሁ፡፡ ጠያቂው እራሴ፤ መልሱን ሳልመልስ ተመልሼ ዝም እላለሁ፡፡ ከድሮውም ፀሃፊ መሆንን እፈልጋለሁ ስል የሰማኝ ማንም የለም፡፡…
Saturday, 08 June 2013 08:37

እንጀራ ፈላጊ

Written by
Rate this item
(5 votes)
ጋዜጣ አዟሪ ነኝ፡፡ ካዛንቺስ፣ ሃናን ዳቦ ቤት አካባቢ ጋዜጦችን ታቅፌ ስዞር የምውል ጋዜጣ አዟሪ፡፡ ጋዜጦችን እሸጣለሁ፡፡ ጋዜጦችን አከራያለሁ፡፡ በመደዳ ከተሰደሩት ካፌዎች በረንዳ ላይ ቁጭ ብለው ሻይ ቡና ለሚሉ ተስተናጋጆች ጋዜጦችን አቀርባለሁ፡፡ አንዳንዶች ይገዙኛል። አንዳንዶች ገለጥ ገለጥ አድርገው አንብበው ሽልንግም፣ አንድ…
Saturday, 08 June 2013 08:22

የመግደል ጥበብ

Written by
Rate this item
(4 votes)
ካለፈው የቀጠለ ምዕራፍ አራት፡ - የድብርት ቀን አንድ ቀን አመመኝ ብዬ ከትምህርት ቀርቻለሁ፡፡ ማመም ሳይሆን በቃ የዚያን ቀን እንዲሁ ደብሮኛል። ያው እናቴ ነገሮችን ያለ ምክንያት እንደማላደርግ ስለምታውቅ እንድቀር ፈቀደችልኝ፡፡ “ግን ምንህን ነው ያመመህ?” አለችኝ፤ ሻሿን እያሰረች፡፡ “እውነቱን ልንገርሽ ጆርጌ?” እናቴን…
Saturday, 01 June 2013 13:38

የመግደል ጥበብ

Written by
Rate this item
(3 votes)
ምዕራፍ አንድ፡- በሬ ከአራጁ ይውላል ‘You are a murderer whether you know it or not’ ይህን አረፍተ ነገር ያገኘሁት አንድ ለዳጄ ያዋሠኝ መፅሐፍ ላይ ነው፡፡ መፅሐፉ ለኢ-ልብ ወለድ ፀሐፊዎች እና አንባቢዎች የተፃፈ ነው፤ The Art of Non Fiction ይላል (የፅሁፌን…
Monday, 27 May 2013 14:10

ትርፍ ጣት

Written by
Rate this item
(2 votes)
ደሴ፡፡ በቀን ሃያ ሰባት፣ በዕለተ ሰንበት - እሁድ፣ በባለ አንድ አጥንቱ…ጥቅምት ወር ውስጥ፣ ባለፈው ሚሊኒየም፣ በ1990ዎቹ መጀመሪያ … መሆኑ ነው፡፡ ልክ ከንጋቱ 12፡10 ይላል… ሌሊት ቢመስልም፡፡ የደሴ ፒያሳ በህዝበ ክርስቲያን እየተጨናነቀች ነው፡፡ የመድሐኒዓለምን ቤተክርስቲያን ለመሳለም ህዝብ አዳም ይርመሰመሳል፡፡ ጉም ቢጤ…
Rate this item
(8 votes)
ሰማዩ ጨልሟል፡፡ ጨረቃ ወለል ብላ ወጥታ ደማቅ ብርሃኗን ትለግሳለች፡፡ የባህሩ ማዕበል ሲጋጭ የሚፈጥረው ድምጽ ስሜትን ያነቃል፡፡ ከእኔ ጋር ተቀምጠው የሚሄዱትን ተጓዦች በዓይኔ ቃኘሁ፡፡ ሽማግሌ ሸበቶ ቄስ የጣጣፈ ልብሳቸውን ለብሰው እየተጓዙ ልብሳቸውን አሁንም አሁንም ያስተካክላሉ፡፡ አናታቸው ላይ ያደረጉት ቆብ እንኳን ሳይቀር…