Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62

ኪነ-ጥበባዊ ዜና

Monday, 05 March 2012 13:38

“መልቲ” ቴአትር ዛሬ ይመረቃል

Written by
Rate this item
(0 votes)
በመልቲ የትያትር ቡድን ተደርሶ በስንታየሁ ፋቡላ የተዘጋጀው “መልቲ” ኮሜዲ ትያትር ዛሬ ከቀኑ 11፡30 ይመረቃል፡፡ በአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት ቴአርትና ባህል አዳራሽ በሚመረቀው ቴአትር ላይ አቤል ሰሎሞን፣ ኤልሻዳይ ከበደ፣ ዳንኤል ሰዒድ፣ ንፁእህት ታዬ እና ምትኩ በቀለ ተውነዋል፡፡
Rate this item
(1 Vote)
በደመወዝ ጎሽሜ የተፃፈው “ሦስተኛው ኪዳን” መፅሐፍ ሐሙስ ምሽት እንደሚመረቅ ብስራት ፕሮሞሽን አስታወቀ፡፡ በመጪው ሐሙስ ከቀኑ 11 ሰዓት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ድህረምረቃ አዳራሽ ይመረቃል፤ መፅሐፉ፡፡ ደሞዝ ጎሽሜ በተለያዩ ጋዜጦችና መፅሔቶች ያቀርባቸው በነበሩ ፅሑፎች ይታወቃል፡፡
Rate this item
(0 votes)
የሚዩዚክ ሜይደይ ኢትዮጵያ የመፃሕፍት ንባብ እና የውይይት ክበብ ነገ ከቀኑ 8 ሰዓት በአምስት ኪሎ በሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተመዘክር አዳራሽ ከውጭ ሀገር ቋንቋዎት ወደ አማርኛ በሚተረጎሙ የፍልስፍና መፃሕፍት ለአንባቢያን ምን ጠቀሜታ ይሰጣሉ በሚል ርእስ ጉዳይ ዙርያ ውይይት እንደሚካሄድ አስታወቀ፡፡
Rate this item
(0 votes)
ባለፈው ሳምንት በተካሄደው የኦስካር ሽልማት ስነስርዓት ከአሜሪካ ውጭ የተሰሩ ፊልሞች ዋና ዋናዎቹን ሽልማቶች እንደወሰዱ ሎስ አንጀለስ ታይምስ ገለፀ፡፡ የፈረንሳይ፤ የፓኪስታን፤ የኢራንና የኳታር የፊልም ባለሙያዎችና ፊልም ሰሪዎች የኦስካር ተሸላሚ ሆነዋል፡፡ በፈረንሳይ የፊልም ባለሙያዎች የተሰራው ድምፅ አልባው ፊልም “ዘ አርቲስት” አምስት ዋና…
Rate this item
(0 votes)
በአሜሪካ ልዩ የባህር ሃይል ወታደሮች “ኔቪ ሲልስ” የተተወነው “አክት ኦፍ ቫሎር” የተሰኘው ፊልም 24.7 ሚሊዮን ዶላር ሳምንታዊ ገቢ በማስመዝገብ ቦክስ ኦፊስን መምራት ጀመረ፡፡ በእውነተኛ የአሜሪካ ባህር ሃይል ወታደሮች ላይ ተመስርቶ ለቀረፃው 13 ሚሊየን ለማስተዋወቅ 30 ሚሊየን ዶላር የወጣበት የተሰራው ፊልም…
Rate this item
(0 votes)
ለመጥፎ ፊልም ስራዎችና ባለሙያዎቻቸው በሚሰጠው የራዚ አዋርድ ላይ በ11 ዘርፎች ለሽልማት በመታጨት አዳም ሳንድለር ሪከርዱን እንደያዘ ሎስአንጀለስ ታይምስ ዘገበ፡፡ ባለፈው የፈረንጆች ዓመት በሰራቸው ሶስት ፊልሞች በመሪ ተዋናይነት፤ በፕሮድዩሰርነትና በፊልም ድርሰት ፀሃፊነት የተሳተፈው ኮሜድያኑ አዳም ሳንድለር፤ የዓመቱ መጥፎ ፊልሞችና የዓመቱ መጥፎ…