ልብ-ወለድ
ውዴ፤ እጥረቴና ማነሴ ከእይታህ ሳይሰውረኝ እንደ ንስር ከፍ ብለህ በትህትና ሰማይ ላይ በአንክሮ ያስተዋልከኝ፣ የማታው ጽልመት ሳይጋርድህ፣ ከሺ ቆነጃጅቶች መሃል እኔን ነጥለህ በብርሃን ልብህ ያየኽኝ፣ ሞገስ አልባ ደቃቃው ሰውነቴ ከእይታህ ሳያጎለኝ፣ ሰው ለመቅረብ ያፈረ የተርበተበተና በማነስ ትእቢት፣ በመዋረድ ሃፈረት በብቸኝነት…
Read 1194 times
Published in
ልብ-ወለድ
የልባችን አፈር ላይ የበቀለው የታሪክ አበባ አንድ ቀን ውሃ ሳናጠጣው፣ ፀሃይ ሳናስነካው ይደርቅና ዛሬም በትላንት ከፈን ተገንዞ እንቡጥ ፅጌረዳነቱ በጠወለጉ ቅጠሎች ይገለፃል። ያቺ የጠወለገች ቅጠል ህይወትን የምናይባት ብርሃን የነበረች ናት... የፍቅርን “ሀሁ” የቆጠርንባት፣ የሃዘንን ህመም ያየንባት፣ ጉድፋችንን መመልከቻ መስታወት ነበረች።ያቺ…
Read 1200 times
Published in
ልብ-ወለድ
ቀጭን! ጠይም! መካከለኛ ቁመና እና አሳዛኝ የፊት ገፅታ ያላት አስተናጋጅ ገና ከመቀመጣችን መጥታ በትህትና “ምን ልታዘዝ” አለችን፤ ገና ፊቷን ሳየው የሆነ የሐዘን በትር በላዬ ላይ ያረፈብኝ ይመስል አመመኝ፤ ሴት አስተናጋጆች ለሴት መታዘዝ የማይመቻቸው እስኪመስለኝ ድረስ ጥሩ ፊት አሳይተውኝ አያውቁም፤ ካየሁት…
Read 1370 times
Published in
ልብ-ወለድ
አይመስላትም ነበር። እዚያ ዳር ተቀምጣ የምትለምን ልጅ ውብ ከሆነ ፍቅር የወጣች... አይመስላትም ነበር። እነዚያ ጀግና ወንዳዶች ውብቷን ፍለጋ የሚዳክሩ... በጠወለገ ውበቷም እንደሚቀልዱ፣ ያደነቁት ቅናታቸውን መሆኑን አይመስላትም ነበር። ... ፍቅራቸው ከማስመሰል ጭቃ የተላቆጠ ... አይመስላትም ነበር። ሰዎች ማታለልን እንደ ዳዊት እንዲሚደግሙ፣…
Read 1161 times
Published in
ልብ-ወለድ
ከመድከሙ የተነሣ ፊቱ ተጨማድዷል፤ ፊቱም ከመጨማደዱ የተነሣ የግንባሩ ሰምበሮች የተፈተለ ጅራፍ አስመስለውታል። ታክቷል፤ የተጓዘው መንገድ ተጫውቶበት፣ ሰውነቱ ሁሉ ዝሏል፡፡ መኝታ ፍለጋ የሚያንቀዋልላቸው ዐይኖቹ አንድ ግቢ ላይ አረፉ፡፡ በግቢው ውስጥ አንድ አሮጌ የጭቃ ፎቅ ይታያል፡፡ ከሥረኛው ወለል በላይ ሁለት ወለሎች አሉት፡፡…
Read 1150 times
Published in
ልብ-ወለድ
..ሦስት ቀን ሲቀረው....በከፊል ሰመመንና በከፊል ንቃት ውስጥ ባለች መስመር ላይ ሰውነቴ ተንጠልጥላ ባፍንጫዬ የምትገባውን የትራስና ብርድልብስ መአዛ በማለዳ አጣጥማለሁ። እንዲሁ በእንዲሁ ሰአት ሁሌም እንደማደርገው፣ አሁንም አሁንም አስባለሁ። ከአልጋው ላይ የሚመጣው የሚሸተኝ ጠረን የፀጉሯ ቅባት ይሆን? ወይስ ሰውነቷን የምትቀባው ሽቶ? ወይስ....…
Read 1283 times
Published in
ልብ-ወለድ