ልብ-ወለድ
በእኔና በእነሱ መካከል ያለው ድልድይ ገና ጨረታ አልወጣለትም፡፡ እኔ የተፈለቀቅሁት ከገዛ ጥጥ ማሳዬ ነው፡፡ እነሱ ሊያባዝቱኝ ከንቱ ይደክማሉ፡፡ አለም ደግሞ (ቁሌታም) እንዝርት ናት፤….ለሰበቃት ጭን ምትገልጥ!....እሷ……….እኔ………..እነ’ሱ…ሥጋት ላይ ተወዝቼ እሰማለሁ እኔ…(እሷ ጆሮ ዳባ ብላለች፡፡)እነሱ መች ያርፋሉ…ቅኝቱ እንደፈረሰ ሙዚቃ ጣም አጥተው፡፡ ***ከጆሮዬ ጥግ…
Read 3594 times
Published in
ልብ-ወለድ
እሷ ይኸ ሕይወትን በጅምላ የሚያስሮጠኝ ዕድሜ፣ ቀኔን እንደ ጉልት ሽንኩርት ሲቸርችረኝ ይውልና መኖሬን ሲያዝለው፣ የድካሜን ጣመን ልወጣ እተኛለሁ፡፡ እናም የተስፋዬን ምንጣፍ ነገዬን ዘርግቼ ተኛሁ፡፡ እንደተኛሁ ሰመመን ይመስል አንዴ ሲያሸልበኝ ወዲያው እየባነንኩ ጥቂት ከቆየሁ በኋላ ድካሜ በርትቶ ዕንቅልፌ ጭልጥ አድርጐ ወሰደኝ፡፡…
Read 4766 times
Published in
ልብ-ወለድ
እንደ ማሰላሰያ አስታውሳለሁ፤ ድሮም እኔ ነበርኩ፡፡አሁንም እኔ ነኝ፡፡ እንደሌሎቹ “እኔ” ብለው ራሳቸውን የሚጠሩ ድሮም አልነበርኩም፡፡ አሁንም አይደለሁ፤ ስጨርስም አልሆንም፡፡ “እና ታዲያ ምንድነው ችግሩ?” ብዬ እጠይቃለሁ፡፡ ጠያቂው እራሴ፤ መልሱን ሳልመልስ ተመልሼ ዝም እላለሁ፡፡ ከድሮውም ፀሃፊ መሆንን እፈልጋለሁ ስል የሰማኝ ማንም የለም፡፡…
Read 3272 times
Published in
ልብ-ወለድ
ጋዜጣ አዟሪ ነኝ፡፡ ካዛንቺስ፣ ሃናን ዳቦ ቤት አካባቢ ጋዜጦችን ታቅፌ ስዞር የምውል ጋዜጣ አዟሪ፡፡ ጋዜጦችን እሸጣለሁ፡፡ ጋዜጦችን አከራያለሁ፡፡ በመደዳ ከተሰደሩት ካፌዎች በረንዳ ላይ ቁጭ ብለው ሻይ ቡና ለሚሉ ተስተናጋጆች ጋዜጦችን አቀርባለሁ፡፡ አንዳንዶች ይገዙኛል። አንዳንዶች ገለጥ ገለጥ አድርገው አንብበው ሽልንግም፣ አንድ…
Read 3293 times
Published in
ልብ-ወለድ
ካለፈው የቀጠለ ምዕራፍ አራት፡ - የድብርት ቀን አንድ ቀን አመመኝ ብዬ ከትምህርት ቀርቻለሁ፡፡ ማመም ሳይሆን በቃ የዚያን ቀን እንዲሁ ደብሮኛል። ያው እናቴ ነገሮችን ያለ ምክንያት እንደማላደርግ ስለምታውቅ እንድቀር ፈቀደችልኝ፡፡ “ግን ምንህን ነው ያመመህ?” አለችኝ፤ ሻሿን እያሰረች፡፡ “እውነቱን ልንገርሽ ጆርጌ?” እናቴን…
Read 2896 times
Published in
ልብ-ወለድ
ምዕራፍ አንድ፡- በሬ ከአራጁ ይውላል ‘You are a murderer whether you know it or not’ ይህን አረፍተ ነገር ያገኘሁት አንድ ለዳጄ ያዋሠኝ መፅሐፍ ላይ ነው፡፡ መፅሐፉ ለኢ-ልብ ወለድ ፀሐፊዎች እና አንባቢዎች የተፃፈ ነው፤ The Art of Non Fiction ይላል (የፅሁፌን…
Read 2838 times
Published in
ልብ-ወለድ