ርዕሰ አንቀፅ

Rate this item
(5 votes)
ኤዞፕ ከፃፈልን ተረቶች መካከል አንዱ እንዲህ ይላል፡- ከዕለታት አንድ ቀን ብዙ ጥንቸሎች ተሰብስበው ይመካከራሉ፡፡ አንደኛ ጥንቸል - “ጐበዝ እኔ ኑሮ መሮኛል፡፡ በየአቅጣጫው ጠላት እኛ ላይ እያነጣጠረ መግቢያ መውጪያ አሳጣን፡፡ በየጊዜው መደበቅ፣ ከሰው መሸሽ በጣም ነው ያስጠላኝ” አለች፡፡ ሁለተኛዋ ጥንቸል -…
Rate this item
(5 votes)
ከነአያ አንበሶ በታች ያሉት የዱር አራዊት ሁሉ ተሰብስበው ትልቅ ግብዣ ተደረገና ዳንሱ፣ ጭፈራው፣ ዳንኪራው ቀለጠ! ደራ!ከደናሾቹ መካከል ጥንቸል ተነስታ፤ “ዝም ብለን ከምንደንስ እንወዳደርና ምርጥ ዳንሰኛው ይለይ!” አለችና ሃሳብ አቀረበች፡፡ በሃሳቡዋ ሁሉም ተስማሙና ጭፈራው ቀጠለ፡፡ ሁሉም በተራ በተራ ወደ መድረክ እየወጣ…
Rate this item
(7 votes)
ከክርስቶስ ልደት በፊት በሶስተኛው ክፍለ ዘመን የነበረ ኩንግ ሲ የተባለ አንድ ንጉስ በቻይና ይኖር ነበር፡፡ ንጉስ አሳ በጣም ይወድ የነበረ መሪ ነበር ይባላል፡፡ የአገሩ ህዝብ በሞላ አሳ ይገዛና እጅ መንሻ ያቀርብለታል፡፡ ንጉሱ ኩንግ ሲዩ ግን ስጦታውን አልቀበልም፤ይላል፡፡ ይህንን ያየው ታናሽ…
Rate this item
(10 votes)
ከዕለታት አንድ ቀን የዱር አራዊት አያ አንበሶ ከበሽታቸው መዳናቸውን ምክንያት በማድረግ ድግስ እንዲደገስ ተስማሙ፡፡ አያ አንበሶም ፈቀዱ፡፡ በቅደም - ተከተል ባለሟሎቹ ስማቸው ተዘረዘረ ተፃፈና ጮክ ተብሎ ተነበበ፡፡ “አንደኛ - ነብሮ” ተባለ፡፡ ተጨበጨበ፡፡ “ሁለተኛ - አያ ዝሆን” ተባለ፡፡ ተጨበጨበ፡፡ “ሦስተኛ -…
Rate this item
(11 votes)
አንዲት የቆቅ ልጅ የስንዴ እሸት ትርክክ ብሎ በስሎ በሚገኝበት እርሻ አጠገብ ወጥመድ ተጠምዶ አይታ እናቷን “እናቴ ሆይ እሸት አምሮኝ ነበር፤ ከዚህ ማሣ ገብቼ እንዳልበላ ወጥመድ እንዳይዘኝ ሰጋሁ ምን ይሻለኛል?” ስትል ጠየቀቻት፡፡ እናቷም፤ “ተይ ልጄ ይቅርብሽ ትያዣለሽ አይሆንም” ብላ መከረቻት፡፡ ልጅቷ…
Rate this item
(6 votes)
የምድር አውሬ ሁሉ መነገጃና መሰባሰቢያ አንድ ገበያ ነበር ይባላል፡፡ ከዕለታት አንድ ቀን አውሬ ሁሉ እገበያ ሲውል፤ አያ ጅቦ ቀርቶ ኖሯል፡፡ ማታ ሁሉም ከገበያ ሲመለስ ከጎሬው ብቅ ይልና መንገድ ዳር ይቀመጣል፡፡ ዝንጀሮ ስትመለስ ያገኛትና ገበያው እንዴት እንደዋለ ይጠይቃታል፡፡ “እቸኩላለሁ ጦጢት ከኋላ…