ርዕሰ አንቀፅ

Rate this item
(8 votes)
በጥንት ጊዜ አንድ ሰው ወደ ጐረቤቱ ማሳዎች ተደብቆ በመዝለቅ እህል አጭዶ ሊሰርቅና ሊወስድ ወሰነ፡፡ “ከሦስቱም ማሳዎች ትንሽ…ትንሽ አጭጄ ብወስድ አይታወቅም፡፡” በማለት ራሱን አሳመነ፡፡ “ለእኔ ግን ከሁሉም ማሳዎች የምሰበስበው ብዙ ይሆንልኛል፤” በማለት አሰበ፡፡ ስለዚህ ሰውየው ቀኑ ሲጨላልምና ደመናው ሲከብድ ያሰበውን ስርቆት…
Rate this item
(9 votes)
“ከብረው ይቆዩኝ ከብረው ባመት ወንድ ልጅ ወልደው! አምሣ ጥገቶች አሥረው…!”ከዕለታት አንድ ቀን አንድ አሳማ፤ በጐች በብዛት ወደተሰማሩበት የግጦሽ መስክ ጐራ ይላል፡፡ እረኛው “ምን ሊያደርግ መጣ” በሚል ጥርጣሬ ያስተውለዋል፡፡ አሳማው ወደ በጐቹ ለመቀላቀል ይሞክራል፡፡ እኛው ያደፍጥ ያደፍጥና ፈጥኖ ተጠግቶ አሳማውን ይይዘዋል፡፡…
Rate this item
(8 votes)
(የጐንቸ ኤትወኸተታወካኾንም፣ ቢውሪ አንቃታ ባረም፣ አንቃሸታ ቦካኾን አቤተትኾንም)ከዕለታት አንድ ቀን በአንድ ቤት ውስጥ አንድ አህያና አንድ የቤት ውሻ ይኖሩ ነበረ፡፡ አህያው እግርግም ውስጥ ይታሰራል፡፡ ብዙ መኖ በዙሪያው ይቀመጥለታል፡፡ በጣም ጠግቦ ይበላል። ጌታው ደግ በመሆኑ እንደልቡ እንዲያናፋም ይፈቀድለታል፡፡ የቤት ውሻው ደግሞ…
Rate this item
(5 votes)
(ነገር ንአጓዲኣ ትልክም፣ ታኼላ ንኣታዊኣ ተስጥም) ከእለታት አንድ የክረምት ቀን፣ አንዳች አውሎ ንፋስ በመጣ ሰዓት፤ ፈረስ፣ በሬ እና ውሻ አንዱን የሰው ልጅ እንዲያስጠልላቸውና እንዲያሳድራቸው ለመኑት፡፡ ሰውዬው መልካም ፈቃዱ ሆነ፡፡ የክረምቱ ብርድ በርዷቸዋልና ይሞቃቸው ዘንድ እሳት አነደደላቸው፡፡ የሚተኙበት ምቹ ስፍራም ሰጣቸው፡፡…
Rate this item
(9 votes)
የሃይማኖት መሪው ቡድሐ የሚሰጠን አንድ ዕንቆቅልሽ የሚከተለውን ይመስላል፡፡ አንድ ነጋዴ ሩቅ አገር ሄዶ ሲመለስ፤ ቤቱ በሽፍቶች ተዘርፎና ተቃጥሎ ይደርሳል፡፡ ከቤቱ የተረፈው ረመጥ - መካከል አንድ ተቃጥሎ የከሰለ የሰው ገላ ያያል፡፡ “ይሄ ትንሹ ልጄ መሆን አለበት” አለ፡፡ በዚህ ምክንያት ምርር ብሎ…
Rate this item
(5 votes)
(የሚከተለውን ተረት - መሰል ታሪክ ከዚህ ቀደም ትንሽ ለየት ባለ መልኩ ተርከነዋል፡፡ የሚሰማ ጠፍቶ ታሪክ ሲደገም በማየታችን ደግመን አቅርበነዋል፡፡) አንድ ፀሐፊ እንዳለው “እኔን ቅር የሚለኝ ታሪክ መደገሙ ሳይሆን፤ በበለጠ አስከፊ መልኩ መደገሙ ነው” ይላል፡፡ ዕውነት ሆነው ከመቆየት ብዛት ተረት የሚሆኑ…