ርዕሰ አንቀፅ

Rate this item
(10 votes)
ዓለም በሁለት ተከፍላ በነበረ ዘመን ማለትም በካፒታሊስትና በሶሻሊስት ጐራ፤ ይወራ የነበረ አንድ ውጋውግ (witticism) አለ፡፡ ድሮ አንድ ጊዜ በፖላንድ አገር ከፍተኛ የሥጋ ዕጥረት ተፈጠረ፡፡ ህዝቡ አማረረ፡፡ ጋዜጦች፣ ሬዲዮ፣ ቴሌቪዥን፣ ወሬው የሥጋ ዕጥረት ነገር ሆነ (ያው እንደኛው አገር)፡፡ ልዩ ልዩ ዓለም…
Rate this item
(14 votes)
ከዕለታት አንድ ቀን ሁለት የድርጅት አሰሪዎች ስለሰራተኞቻቸው ዳተኝነት ይወያያሉ፡፡ አንደኛው፡- “እኔ መቼም እንደሚገባኝ፤ እኔ ድርጅት ውስጥ እንዳለው እንደ አቶ እገሌ ደደብ፣ ደንቆሮ ሰራተኛ በዓለም ቢዞሩ አይገኝም ባይ ነኝ፡፡”ሁለተኛው፤ “ለምን እንዲህ አልክ? ምን አጥፍቶ አግኝተኸው ነው?” አለው፡፡ “ይህን ዳተኛው ቆይ ልጥራውና…
Rate this item
(9 votes)
በዓለም ላይ “የመርፊ ህግ” በመባል የሚታወቅ ህግ አለ፡፡ የምንሠራው ሥራ ሁሉ ስህተት ይሆናል ብሎ የማመን አዝማሚያ ነው፡፡ ስለዚህ ጉዳይ የሚተረክ አንድ ተረት አለ፡፡ ከዕለታት አንድ ቀን አንድ ሰው፤ በአንድ በጣም በራበው ጠዋት፤ ቁርስ አስቀርቦ መብላት ጀመረ፡፡ ዳቦውን ሁለት ላይ ከፈለና…
Rate this item
(6 votes)
ጥንት ዱሮ አያ ቋቴ የሚባሉ ብልህ ሰው ነበሩ ይባላል፡፡ የአያ ቋቴ መታወቂያ ሰው እህል ለመዝራት ገና መሬቱን ሳያለሰልስ እሳቸው እርሻ መጀመራቸው ነው፡፡ “አያ ቋቴ?” ይላቸዋል አንዱ፡፡ “አቤት” ይላሉ“ምነው እንዲህ ተጣደፉ? በጊዜ እርሻ ጀመሩ?”“በጊዜ ቋቴን (የዱቄት እቃዬን) ልሞላ ነዋ” ይላሉ፡፡ “መሬቱ…
Rate this item
(5 votes)
ከዕለታት አንድ ቀን አንድ አዋቂ ነኝ ባይ ሰው ወደገበያ ቦታ ይሄድና “ዕጣ - ፈንታችሁን እነግራችኋለሁና ማወቅ የምትፈልጉ ተሰብሰቡ” ይላል፡፡ ሰው ባንድ ጊዜ ይሰበሰባል፡፡ ለመጀመሪያው ሰውዬ፤ “ምን እንድረዳህ ትፈልጋለህ?” ሲል ይጠይቀዋል፡፡ ይህ ሰውዬ አለባበሱ ለየት ያለ ነው፡፡ በጣም ደማቅ አረንጔዴ ካፖርትና…
Rate this item
(6 votes)
አንዳንድ ዕውነተኛ ታሪክ ሲቆይ ተረት ይመስላል፡፡ የሚከተለው ትርክት እንዲያ ያለ ጠባይ አለው:-ሰውየው እሥረኛ ነበሩ አሉ፡፡ በጥንት ዘመን፡፡ ዚቀኛ ናቸው - ነገር አዋቂ፡፡ እሥረኞች “የሻማ” የሚሉት ፈሊጥ አላቸው፡፡ የኢኮኖሚ እርዳታ ነው አንዱ፡፡ የመዝናኛ ጥያቄ ነው ሁለተኛው፡፡ ጠያቂው እሥረኛ - በምን ታሠሩ?…